Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

Nummer der Seite:close

external-link copy
43 : 23

مَا تَسۡبِقُ مِنۡ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ

43. ማንኛይቱም ህዝብ ጊዜዋን አትቀድምም:: ከጊዜያቸዉም አይቆዩምም:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 23

ثُمَّ أَرۡسَلۡنَا رُسُلَنَا تَتۡرَاۖ كُلَّ مَا جَآءَ أُمَّةٗ رَّسُولُهَا كَذَّبُوهُۖ فَأَتۡبَعۡنَا بَعۡضَهُم بَعۡضٗا وَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَحَادِيثَۚ فَبُعۡدٗا لِّقَوۡمٖ لَّا يُؤۡمِنُونَ

44. ከዚያም መልዕክተኞቻችንን በተከታታይ ላክን፤ ማንኛይቱንም ህዝብ መልእክተኛዋ በመጣላት ቁጥር አስተባበሉት። ከፊላቸውንም በከፊሉ በጥፋት አስከታተልን፤ ወሬዎችም አደረግናቸው፤ ለማያምኑም ህዝቦች ከእዝነታችን መራቅ ተገባቸው። info
التفاسير:

external-link copy
45 : 23

ثُمَّ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَٰرُونَ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٍ

45. ከዚያ ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተአምራታችንና በግልጽ ማስረጃ ላክናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 23

إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ وَكَانُواْ قَوۡمًا عَالِينَ

46. ወደ ፈርዖንና ወደ ጭፍሮቹ ላክናቸው። ድሮውም የኮሩና የተንበጣረሩ ህዝቦችም ነበሩ። info
التفاسير:

external-link copy
47 : 23

فَقَالُوٓاْ أَنُؤۡمِنُ لِبَشَرَيۡنِ مِثۡلِنَا وَقَوۡمُهُمَا لَنَا عَٰبِدُونَ

47. «ህዝቦቻቸው ለኛ ተገዢዎች ሆነው ሳሉ ብጤያችን ለሆኑ ሰዎች እናምናለን?» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
48 : 23

فَكَذَّبُوهُمَا فَكَانُواْ مِنَ ٱلۡمُهۡلَكِينَ

48. አስተባበሏቸዉም፤ ከጠፊዎችም ሆኑ:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 23

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ لَعَلَّهُمۡ يَهۡتَدُونَ

49. ሙሳንም ነገዶቹ ይመሩ ዘንድ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 23

وَجَعَلۡنَا ٱبۡنَ مَرۡيَمَ وَأُمَّهُۥٓ ءَايَةٗ وَءَاوَيۡنَٰهُمَآ إِلَىٰ رَبۡوَةٖ ذَاتِ قَرَارٖ وَمَعِينٖ

50. የመርየምን ልጅ ዒሳንና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው:: የመደላደልና የምንጭ ባለቤት ወደ ሆነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 23

يَٰٓأَيُّهَا ٱلرُّسُلُ كُلُواْ مِنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَٱعۡمَلُواْ صَٰلِحًاۖ إِنِّي بِمَا تَعۡمَلُونَ عَلِيمٞ

51. እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ሁሉ ብሉ:: በጎ ስራንም ስሩ:: እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝና:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 23

وَإِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَأَنَا۠ رَبُّكُمۡ فَٱتَّقُونِ

52. ይህችም በአንድ አምላክ የማመን ህግጋት አንድ መንገድ ስትሆን ሃይማኖታችሁ ናት:: እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 23

فَتَقَطَّعُوٓاْ أَمۡرَهُم بَيۡنَهُمۡ زُبُرٗاۖ كُلُّ حِزۡبِۭ بِمَا لَدَيۡهِمۡ فَرِحُونَ

53. ከዚያም ተከታዮቻቸው ሃይማኖታቸውን በመካከላቸው ክፍልፍሎች አድርገው ቆራረጡ፤ ህዝቦች ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ሃይማኖት ተደሳቾች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
54 : 23

فَذَرۡهُمۡ فِي غَمۡرَتِهِمۡ حَتَّىٰ حِينٍ

54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እስከ ጊዜያቸዉም ድረስ በጥመታቸው ውስጥ ተዋቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
55 : 23

أَيَحۡسَبُونَ أَنَّمَا نُمِدُّهُم بِهِۦ مِن مَّالٖ وَبَنِينَ

55. ከገንዘብና ከልጆች በእርሱ የምንጨምርላቸውን ያስባሉን? info
التفاسير:

external-link copy
56 : 23

نُسَارِعُ لَهُمۡ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِۚ بَل لَّا يَشۡعُرُونَ

56. በበጎ ነገሮች የምንቻኮልላቸው እንደሆነ ያስባሉን? አይደለም፤ ይህ ሁሉ እነርሱን ለማዘናጋት መሆኑን አያውቁም። info
التفاسير:

external-link copy
57 : 23

إِنَّ ٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ خَشۡيَةِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ

57. እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ከመፍራት የተነሳ ተጨናቂዎች የሆኑት፤ info
التفاسير:

external-link copy
58 : 23

وَٱلَّذِينَ هُم بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ يُؤۡمِنُونَ

58. እነዚያም እነርሱ በጌታቸው ተዓምራት የሚያምኑት፤ info
التفاسير:

external-link copy
59 : 23

وَٱلَّذِينَ هُم بِرَبِّهِمۡ لَا يُشۡرِكُونَ

59. እነዚያም በጌታቸው የማያጋሩት፤ info
التفاسير: