Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

አል-ሙዕሚኑን

external-link copy
1 : 23

قَدۡ أَفۡلَحَ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ

1.ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ተሳካላቸው):: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 23

ٱلَّذِينَ هُمۡ فِي صَلَاتِهِمۡ خَٰشِعُونَ

2. እነዚያም በስግደታቸው ውስጥ አላህን ፈሪዎች የሆኑት፤ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 23

وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَنِ ٱللَّغۡوِ مُعۡرِضُونَ

3. እነዚያም ከመጥፎ ነገር ሁሉ የራቁ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 23

وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِلزَّكَوٰةِ فَٰعِلُونَ

4. እነዚያም ዘካን በአግባቡ ሰጪዎች፤ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 23

وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ

5. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 23

إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ

6. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው ሴት ባሪያዎች ላይ ካልሆነ በቀር (ብልቶቻቸውን ጠባቂ የሆኑት)፤ እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 23

فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ

7. ከዚህ ሌላ በሆነ መንገድ (ስሜታቸዉን ሊያረኩ) የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ የአላህን ወሰን አላፊዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 23

وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ

8. እነዚያም ለአደራዎቻቸውና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች፤ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 23

وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَوَٰتِهِمۡ يُحَافِظُونَ

9. እነዚያም በስግደቶቻቸው ላይ (ሁለንተናዋን) የሚጠባበቁ የሆኑት info
التفاسير:

external-link copy
10 : 23

أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡوَٰرِثُونَ

10. እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 23

ٱلَّذِينَ يَرِثُونَ ٱلۡفِرۡدَوۡسَ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ

11. እነዚያ ፊርደውስን (ላዕላይ ገነትን) የሚወርሱ ናቸው:: እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 23

وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِن سُلَٰلَةٖ مِّن طِينٖ

12. በእርግጥ ሰውን (አደምን) ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 23

ثُمَّ جَعَلۡنَٰهُ نُطۡفَةٗ فِي قَرَارٖ مَّكِينٖ

13. ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 23

ثُمَّ خَلَقۡنَا ٱلنُّطۡفَةَ عَلَقَةٗ فَخَلَقۡنَا ٱلۡعَلَقَةَ مُضۡغَةٗ فَخَلَقۡنَا ٱلۡمُضۡغَةَ عِظَٰمٗا فَكَسَوۡنَا ٱلۡعِظَٰمَ لَحۡمٗا ثُمَّ أَنشَأۡنَٰهُ خَلۡقًا ءَاخَرَۚ فَتَبَارَكَ ٱللَّهُ أَحۡسَنُ ٱلۡخَٰلِقِينَ

14. ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም ቁራጭ ስጋ አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጭዋንም ስጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን:: አጥንቶችንም ስጋን አለበስናቸው። ከዚያም (በዉስጡ ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረት አድርገን አስገኘነው:: ከቅርፅ ሰጪዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ከሁሉ ላቀ። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 23

ثُمَّ إِنَّكُم بَعۡدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ

15. (ሰዎች ሆይ!) ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 23

ثُمَّ إِنَّكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ تُبۡعَثُونَ

16. ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ዕለት ትቀሰቀሳላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 23

وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعَ طَرَآئِقَ وَمَا كُنَّا عَنِ ٱلۡخَلۡقِ غَٰفِلِينَ

17. በእርግጥም ከበላያችሁ ሰባትን ሰማያት ፈጠርን:: ከፍጥረቶቹም ዘንጊዎች አይደለንም:: info
التفاسير: