Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası.

Səhifənin rəqəmi:close

external-link copy
138 : 7

وَجَٰوَزۡنَا بِبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱلۡبَحۡرَ فَأَتَوۡاْ عَلَىٰ قَوۡمٖ يَعۡكُفُونَ عَلَىٰٓ أَصۡنَامٖ لَّهُمۡۚ قَالُواْ يَٰمُوسَى ٱجۡعَل لَّنَآ إِلَٰهٗا كَمَا لَهُمۡ ءَالِهَةٞۚ قَالَ إِنَّكُمۡ قَوۡمٞ تَجۡهَلُونَ

138. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሻገርናቸው:: ለእነርሱ በሆኑ ጣኦታት መገዛት ላይ በሚዘወትሩ ህዝቦች አጠገብ አለፉም:: «ሙሳ ሆይ! ለእነርሱ ለሰዎቹ አማልክት እንዳሏቸው ሁሉ ለኛም አምላክን አድርግልን።» አሉት:: «እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
139 : 7

إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ مُتَبَّرٞ مَّا هُمۡ فِيهِ وَبَٰطِلٞ مَّا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

139. «እነዚህ እነርሱ በውስጡ ያሉበት ነገር ጠፊ ነው:: ይሰሩት የነበሩትም ብልሹ ነው።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
140 : 7

قَالَ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَبۡغِيكُمۡ إِلَٰهٗا وَهُوَ فَضَّلَكُمۡ عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ

140. «እርሱ ከዓለማት ያበለጣችሁ ሲሆን ከአላህ ሌላ የምትገዙትን አምላክ እፈልግላችኋለሁን?» አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
141 : 7

وَإِذۡ أَنجَيۡنَٰكُم مِّنۡ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ يَسُومُونَكُمۡ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ يُقَتِّلُونَ أَبۡنَآءَكُمۡ وَيَسۡتَحۡيُونَ نِسَآءَكُمۡۚ وَفِي ذَٰلِكُم بَلَآءٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَظِيمٞ

141. የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ከፈርዖንም ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ ወንዶች ልጆቻችሁንም የሚገድሉ ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲሆኑ ባዳንናችሁ ጊዜ (የሆነዉን አስታውሱ):: በዚህ ውስጥ ከጌታችሁ የሆነ ከባድ ፈተና አለበት:: info
التفاسير:

external-link copy
142 : 7

۞ وَوَٰعَدۡنَا مُوسَىٰ ثَلَٰثِينَ لَيۡلَةٗ وَأَتۡمَمۡنَٰهَا بِعَشۡرٖ فَتَمَّ مِيقَٰتُ رَبِّهِۦٓ أَرۡبَعِينَ لَيۡلَةٗۚ وَقَالَ مُوسَىٰ لِأَخِيهِ هَٰرُونَ ٱخۡلُفۡنِي فِي قَوۡمِي وَأَصۡلِحۡ وَلَا تَتَّبِعۡ سَبِيلَ ٱلۡمُفۡسِدِينَ

142. ነብዩ ሙሳን ሰላሳን ሌሊት (ሊፆምና ልናነጋግረው) ቀጠርነው:: በአስርም (ሌሊት) ሞላናት:: የጌታዉም ቀጠሮ አርባ ሌሊት ሲሆን ተፈጸመ:: ሙሳም ለወንድሙ ለሀሩን «በህዝቦቼ ላይ ተተካኝና አሳምር:: የአጥፊዎችን መንገድ አትከተል።» አለው:: info
التفاسير:

external-link copy
143 : 7

وَلَمَّا جَآءَ مُوسَىٰ لِمِيقَٰتِنَا وَكَلَّمَهُۥ رَبُّهُۥ قَالَ رَبِّ أَرِنِيٓ أَنظُرۡ إِلَيۡكَۚ قَالَ لَن تَرَىٰنِي وَلَٰكِنِ ٱنظُرۡ إِلَى ٱلۡجَبَلِ فَإِنِ ٱسۡتَقَرَّ مَكَانَهُۥ فَسَوۡفَ تَرَىٰنِيۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُۥ لِلۡجَبَلِ جَعَلَهُۥ دَكّٗا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقٗاۚ فَلَمَّآ أَفَاقَ قَالَ سُبۡحَٰنَكَ تُبۡتُ إِلَيۡكَ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

143. ሙሳ ለቀጠሮው በመጣና ጌታዉም ባነጋገረው ጊዜ፡ «ጌታዬ ሆይ! በእርግጥ ራስህን አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና።» አለ። (አላህም)፡- «እኔን በፍጹም አታየኝም:: ግን ወደ ተራራው ተመልከትና በስፍራው ከረጋ አንተም ታየኛለህ።» አለው:: ጌታዉም ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው:: ሙሳም ጮኸና ወደቀ:: በአንሰራራም ጊዜ «ጌታዬ ጥራት ይገባህ ወደ አንተ ተመለስኩ:: እኔም በጊዜያቴ የአማኞች መጀመሪያ ነኝ።» አለ። info
التفاسير: