Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Məhəmməd Sadiq.

Səhifənin rəqəmi: 199:187 close

external-link copy
80 : 9

ٱسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ أَوۡ لَا تَسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ إِن تَسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ سَبۡعِينَ مَرَّةٗ فَلَن يَغۡفِرَ ٱللَّهُ لَهُمۡۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡفَٰسِقِينَ

ለእነርሱ ምሕረትን ለምንላቸው፤ ወይም ለእነሱ ምሕረትን አትለምንላቸው (እኩል ነው)፡፡ ለእነሱ ሰባ ጊዜ ምሕረትን ብትለምንላቸው አላህ ለነሱ በፍጹም አይምርም፡፡ ይህ እነርሱ አላህና መልክተኛውን በመካዳቸው ነው፡፡ አላህም አመጸኞች ሕዝቦችን አያቀናም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
81 : 9

فَرِحَ ٱلۡمُخَلَّفُونَ بِمَقۡعَدِهِمۡ خِلَٰفَ رَسُولِ ٱللَّهِ وَكَرِهُوٓاْ أَن يُجَٰهِدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَقَالُواْ لَا تَنفِرُواْ فِي ٱلۡحَرِّۗ قُلۡ نَارُ جَهَنَّمَ أَشَدُّ حَرّٗاۚ لَّوۡ كَانُواْ يَفۡقَهُونَ

እነዚያ ከዘመቻ የቀሩት ከአላህ መልክተኛ በኋላ በመቀመጣቸው ተደሰቱ፡፡ በአላህም መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው መታገልን ጠሉ፡፡ «በሐሩር አትኺዱ» አሉም፡፡ «የገሀነም እሳት ተኳሳነቱ በጣም የበረታ ነው» በላቸው፡፡ የሚያውቁ ቢኾኑ ኖሮ (አይቀሩም ነበር)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
82 : 9

فَلۡيَضۡحَكُواْ قَلِيلٗا وَلۡيَبۡكُواْ كَثِيرٗا جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ

ጥቂትንም ይሳቁ፡፡ ይሠሩት በነበሩት ዋጋ ብዙን ያለቅሳሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
83 : 9

فَإِن رَّجَعَكَ ٱللَّهُ إِلَىٰ طَآئِفَةٖ مِّنۡهُمۡ فَٱسۡتَـٔۡذَنُوكَ لِلۡخُرُوجِ فَقُل لَّن تَخۡرُجُواْ مَعِيَ أَبَدٗا وَلَن تُقَٰتِلُواْ مَعِيَ عَدُوًّاۖ إِنَّكُمۡ رَضِيتُم بِٱلۡقُعُودِ أَوَّلَ مَرَّةٖ فَٱقۡعُدُواْ مَعَ ٱلۡخَٰلِفِينَ

ከእነሱም ወደ ኾነችው ጭፍራ አላህ ቢመልስህ (ከአንተ ጋር) ለመውጣትም ቢያስፈቅዱህ፡-«ከኔ ጋር በፍጹም አትወጡም፡፡ ከእኔም ጋር ጠላትን አትዋጉም፡፡ እናንተ በመጀመሪያ ጊዜ መቀመጥን ወዳችኋልና፡፡ ከተቀማጮቹ ጋርም ተቀመጡ» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
84 : 9

وَلَا تُصَلِّ عَلَىٰٓ أَحَدٖ مِّنۡهُم مَّاتَ أَبَدٗا وَلَا تَقُمۡ عَلَىٰ قَبۡرِهِۦٓۖ إِنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَمَاتُواْ وَهُمۡ فَٰسِقُونَ

ከእነሱም በአንድም በሞተ ሰው ላይ ፈጽሞ አትስገድ፡፡ በመቃብሩም ላይ አትቁም፡፡ እነሱ አላህንና መልክተኛውን ክደዋልና፡፡ እነሱም አመጸኞች ኾነው ሞተዋልና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
85 : 9

وَلَا تُعۡجِبۡكَ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَأَوۡلَٰدُهُمۡۚ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُعَذِّبَهُم بِهَا فِي ٱلدُّنۡيَا وَتَزۡهَقَ أَنفُسُهُمۡ وَهُمۡ كَٰفِرُونَ

ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸውም አይድነቁህ፡፡ አላህ የሚሻው በቅርቢቱ ዓለም በነሱ ሊቀጣቸውና ከሓዲዎችም ኾነው ነፍሶቻቸው እንዲወጡ ብቻ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
86 : 9

وَإِذَآ أُنزِلَتۡ سُورَةٌ أَنۡ ءَامِنُواْ بِٱللَّهِ وَجَٰهِدُواْ مَعَ رَسُولِهِ ٱسۡتَـٔۡذَنَكَ أُوْلُواْ ٱلطَّوۡلِ مِنۡهُمۡ وَقَالُواْ ذَرۡنَا نَكُن مَّعَ ٱلۡقَٰعِدِينَ

በአላህ እመኑ፡፡ ከመልክተኛውም ጋር ኾናችሁ ታገሉ፤ በማለት ምዕራፍ በተወረደች ጊዜ ከነሱ የሰፊ ሀብት ባለቤቶች የኾኑት (ለመቅረት) ፈቃድ ይጠይቁሃል፡፡ «ከተቀማጮቹ ጋርም እንኹን ተወን» ይሉሃል፡፡ info
التفاسير: