Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Məhəmməd Sadiq.

አል ሙጠፊፊን

external-link copy
1 : 83

وَيۡلٞ لِّلۡمُطَفِّفِينَ

ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 83

ٱلَّذِينَ إِذَا ٱكۡتَالُواْ عَلَى ٱلنَّاسِ يَسۡتَوۡفُونَ

ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 83

وَإِذَا كَالُوهُمۡ أَو وَّزَنُوهُمۡ يُخۡسِرُونَ

ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 83

أَلَا يَظُنُّ أُوْلَٰٓئِكَ أَنَّهُم مَّبۡعُوثُونَ

እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
5 : 83

لِيَوۡمٍ عَظِيمٖ

በታላቁ ቀን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 83

يَوۡمَ يَقُومُ ٱلنَّاسُ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 83

كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٖ

በእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 83

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سِجِّينٞ

ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? info
التفاسير:

external-link copy
9 : 83

كِتَٰبٞ مَّرۡقُومٞ

የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 83

وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 83

ٱلَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ

ለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 83

وَمَا يُكَذِّبُ بِهِۦٓ إِلَّا كُلُّ مُعۡتَدٍ أَثِيمٍ

በእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 83

إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

አንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 83

كَلَّاۖ بَلۡۜ رَانَ عَلَىٰ قُلُوبِهِم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ

ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 83

كَلَّآ إِنَّهُمۡ عَن رَّبِّهِمۡ يَوۡمَئِذٖ لَّمَحۡجُوبُونَ

ይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 83

ثُمَّ إِنَّهُمۡ لَصَالُواْ ٱلۡجَحِيمِ

ከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 83

ثُمَّ يُقَالُ هَٰذَا ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ

ከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 83

كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡأَبۡرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ

በእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 83

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا عِلِّيُّونَ

ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? info
التفاسير:

external-link copy
20 : 83

كِتَٰبٞ مَّرۡقُومٞ

የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 83

يَشۡهَدُهُ ٱلۡمُقَرَّبُونَ

ባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 83

إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ لَفِي نَعِيمٍ

እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 83

عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ

በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 83

تَعۡرِفُ فِي وُجُوهِهِمۡ نَضۡرَةَ ٱلنَّعِيمِ

በፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
25 : 83

يُسۡقَوۡنَ مِن رَّحِيقٖ مَّخۡتُومٍ

ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 83

خِتَٰمُهُۥ مِسۡكٞۚ وَفِي ذَٰلِكَ فَلۡيَتَنَافَسِ ٱلۡمُتَنَٰفِسُونَ

ማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 83

وَمِزَاجُهُۥ مِن تَسۡنِيمٍ

መበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 83

عَيۡنٗا يَشۡرَبُ بِهَا ٱلۡمُقَرَّبُونَ

ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 83

إِنَّ ٱلَّذِينَ أَجۡرَمُواْ كَانُواْ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ يَضۡحَكُونَ

እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 83

وَإِذَا مَرُّواْ بِهِمۡ يَتَغَامَزُونَ

በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
31 : 83

وَإِذَا ٱنقَلَبُوٓاْ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمُ ٱنقَلَبُواْ فَكِهِينَ

ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
32 : 83

وَإِذَا رَأَوۡهُمۡ قَالُوٓاْ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَضَآلُّونَ

ባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 83

وَمَآ أُرۡسِلُواْ عَلَيۡهِمۡ حَٰفِظِينَ

በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 83

فَٱلۡيَوۡمَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنَ ٱلۡكُفَّارِ يَضۡحَكُونَ

ዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 83

عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ

በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
36 : 83

هَلۡ ثُوِّبَ ٱلۡكُفَّارُ مَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ

ከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡ info
التفاسير: