Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Məhəmməd Sadiq.

Səhifənin rəqəmi:close

external-link copy
22 : 39

أَفَمَن شَرَحَ ٱللَّهُ صَدۡرَهُۥ لِلۡإِسۡلَٰمِ فَهُوَ عَلَىٰ نُورٖ مِّن رَّبِّهِۦۚ فَوَيۡلٞ لِّلۡقَٰسِيَةِ قُلُوبُهُم مِّن ذِكۡرِ ٱللَّهِۚ أُوْلَٰٓئِكَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ

አላህ ደረቱን ለእስልምና ያስፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የኾነ ሰው (ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን?) ልቦቻቸውም ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወዮላቸው፡፡ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 39

ٱللَّهُ نَزَّلَ أَحۡسَنَ ٱلۡحَدِيثِ كِتَٰبٗا مُّتَشَٰبِهٗا مَّثَانِيَ تَقۡشَعِرُّ مِنۡهُ جُلُودُ ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُمۡ ثُمَّ تَلِينُ جُلُودُهُمۡ وَقُلُوبُهُمۡ إِلَىٰ ذِكۡرِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ هُدَى ٱللَّهِ يَهۡدِي بِهِۦ مَن يَشَآءُۚ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنۡ هَادٍ

አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን፣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ፡፡ ከእርሱ (ግሣጼ) የእነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎች ይኮማተራሉ፡፡ ከዚያም ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ (ተስፋ) ማስታወስ ይለዝባሉ፡፡ ይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ የሚሻውን ሰው ይመራበታል፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 39

أَفَمَن يَتَّقِي بِوَجۡهِهِۦ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ وَقِيلَ لِلظَّٰلِمِينَ ذُوقُواْ مَا كُنتُمۡ تَكۡسِبُونَ

በትንሣኤ ቀን ክፉን ቅጣት በፊቱ የሚመክት ሰው (ከቅጣት እንደሚድን ነውን?) ለበዳዮችም «ትሠሩት የነበራችሁትን (ቅጣቱን) ቅመሱ» ይባላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
25 : 39

كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَأَتَىٰهُمُ ٱلۡعَذَابُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَشۡعُرُونَ

ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባበሉ፡፡ ቅጣቱም ከማያውቁት በኩል መጣባቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 39

فَأَذَاقَهُمُ ٱللَّهُ ٱلۡخِزۡيَ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَكۡبَرُۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ

አላህም በቅርቢቱ ሕይወት ውርደትን አቀመሳቸው፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም ትልቅ ነው፡፡ የሚያውቁ ቢኾኑ ኖሮ (አያስተባብሉም ነበር)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 39

وَلَقَدۡ ضَرَبۡنَا لِلنَّاسِ فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ مِن كُلِّ مَثَلٖ لَّعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ

በዚህም ቁርኣን ውስጥ ለሰዎች ይገሠጹ ዘንድ ከየምሳሌው ሁሉ በእርግጥ አብራራን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 39

قُرۡءَانًا عَرَبِيًّا غَيۡرَ ذِي عِوَجٖ لَّعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ

መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን (አብራራነው)፡፡ ሊጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 39

ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا رَّجُلٗا فِيهِ شُرَكَآءُ مُتَشَٰكِسُونَ وَرَجُلٗا سَلَمٗا لِّرَجُلٍ هَلۡ يَسۡتَوِيَانِ مَثَلًاۚ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

አላህ በእርሱ ተጨቃጫቂዎች የኾኑ ተጋሪዎች ያሉትን ባሪያና ለአንድ ሰው ብቻ ንጹሕ የኾነን ባሪያ (ለሚያጋራና ባንድነቱ ለሚያምን ሰው) ምሳሌ አደረገ፡፡ በምሳሌ ይስተካከላሉን? ምስጋና ለአላህ ይገባው፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 39

إِنَّكَ مَيِّتٞ وَإِنَّهُم مَّيِّتُونَ

አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
31 : 39

ثُمَّ إِنَّكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ عِندَ رَبِّكُمۡ تَخۡتَصِمُونَ

ከዚያም እናንተ በትንሣኤ ቀን እጌታችሁ ዘንድ ትከራከራላችሁ፡፡ info
التفاسير: