আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
24 : 5

قَالُواْ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّا لَن نَّدۡخُلَهَآ أَبَدٗا مَّا دَامُواْ فِيهَا فَٱذۡهَبۡ أَنتَ وَرَبُّكَ فَقَٰتِلَآ إِنَّا هَٰهُنَا قَٰعِدُونَ

24. «ሙሳ ሆይ! እነርሱ በውስጧ እስካሉ ድረስ ፈጽሞ ምንጊዜም አንገባም:: ስለዚህ አንተና ጌታህ ሂዱና ተዋጉ:: እኛ እዚህ ተቀማጮች ነን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 5

قَالَ رَبِّ إِنِّي لَآ أَمۡلِكُ إِلَّا نَفۡسِي وَأَخِيۖ فَٱفۡرُقۡ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡفَٰسِقِينَ

25. ሙሳም «ጌታዬ ሆይ! እኔ ራሴንና ወንድሜን እንጂ ማንንም ላስገድድ አልችልም። ስለዚህ በእኛና በአመጸኞቹ ሕዝቦች መካከል ተገቢ ፍርድህን ስጥ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
26 : 5

قَالَ فَإِنَّهَا مُحَرَّمَةٌ عَلَيۡهِمۡۛ أَرۡبَعِينَ سَنَةٗۛ يَتِيهُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ فَلَا تَأۡسَ عَلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡفَٰسِقِينَ

26. አላህም: «ያቺ የተቀደሰችው መሬት በእነርሱ ላይ ለአርባ አመት ያህል እርም ናት። በምድረ በዳ ይንከራተታሉ። (ሙሳ ሆይ!) በአመጸኞችም ሕዝቦች ላይ አትዘን።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 5

۞ وَٱتۡلُ عَلَيۡهِمۡ نَبَأَ ٱبۡنَيۡ ءَادَمَ بِٱلۡحَقِّ إِذۡ قَرَّبَا قُرۡبَانٗا فَتُقُبِّلَ مِنۡ أَحَدِهِمَا وَلَمۡ يُتَقَبَّلۡ مِنَ ٱلۡأٓخَرِ قَالَ لَأَقۡتُلَنَّكَۖ قَالَ إِنَّمَا يَتَقَبَّلُ ٱللَّهُ مِنَ ٱلۡمُتَّقِينَ

27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱ ላይ የአደምን ሁለት ልጆች ወሬ (ማለትም) ሁለቱም ቁርባን ባቀረቡና አላህ ከአንደኛቸው ቁርባኑን ተቀብሎ ከሌላው ባልተቀበለበት ጊዜ የሆነውን ታሪክ አንብብላቸው:: ተቀባይነት ያጣው ወንድሙን «እገድልሃለሁ።» አለው። (የተዛተበትም) አለ: «አላህ የሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆቹ ብቻ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 5

لَئِنۢ بَسَطتَ إِلَيَّ يَدَكَ لِتَقۡتُلَنِي مَآ أَنَا۠ بِبَاسِطٖ يَدِيَ إِلَيۡكَ لِأَقۡتُلَكَۖ إِنِّيٓ أَخَافُ ٱللَّهَ رَبَّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

28. «ልትገድለኝ እጅህን ወደ እኔ ብትዘረጋ እንኳን እኔ ልገድልህ እጄን ወደ አንተ የምዘረጋ አይደለሁም:: እኔ የአለማቱን ጌታ አላህን እፈራለሁና። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 5

إِنِّيٓ أُرِيدُ أَن تَبُوٓأَ بِإِثۡمِي وَإِثۡمِكَ فَتَكُونَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلنَّارِۚ وَذَٰلِكَ جَزَٰٓؤُاْ ٱلظَّٰلِمِينَ

29. «እኔ በኃጢአቴና በኃጢአትህ ወደ ጌታህ ልትመለስና ከእሳት ጓዶች አንዱ ልትሆን እሻለሁ:: ይህም የበደለኞች ቅጣት ነው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 5

فَطَوَّعَتۡ لَهُۥ نَفۡسُهُۥ قَتۡلَ أَخِيهِ فَقَتَلَهُۥ فَأَصۡبَحَ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ

30. ነፍሱም ወንድሙን መግደሉ አስቻላትና(አስዋበችለት) ገደለው። ከከሳሪዎችም ሆነ። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 5

فَبَعَثَ ٱللَّهُ غُرَابٗا يَبۡحَثُ فِي ٱلۡأَرۡضِ لِيُرِيَهُۥ كَيۡفَ يُوَٰرِي سَوۡءَةَ أَخِيهِۚ قَالَ يَٰوَيۡلَتَىٰٓ أَعَجَزۡتُ أَنۡ أَكُونَ مِثۡلَ هَٰذَا ٱلۡغُرَابِ فَأُوَٰرِيَ سَوۡءَةَ أَخِيۖ فَأَصۡبَحَ مِنَ ٱلنَّٰدِمِينَ

31. ዘንድ አላህ መሬትን የሚጭር ቁራ ላከለት የወንድሙን ሬሳ እንዴት እንደሚቀብር ሊያሳየው። «ወይኔ የወንድሜን ሬሳ እቀብር ዘንድ እንደዚህ ቁራ መሆን እንኳን አቃተኝን?» አለ። ከዚያም ከጸጸተኞች ሆነ። info
التفاسير: