আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
18 : 5

وَقَالَتِ ٱلۡيَهُودُ وَٱلنَّصَٰرَىٰ نَحۡنُ أَبۡنَٰٓؤُاْ ٱللَّهِ وَأَحِبَّٰٓؤُهُۥۚ قُلۡ فَلِمَ يُعَذِّبُكُم بِذُنُوبِكُمۖ بَلۡ أَنتُم بَشَرٞ مِّمَّنۡ خَلَقَۚ يَغۡفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُۚ وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَاۖ وَإِلَيۡهِ ٱلۡمَصِيرُ

18. አይሁድና ክርስቲያኖች «እኛ የአላህ ልጆችና ወዳጆቹ ነን።» አሉ። «ታዲያ በኃጢአቶቻችሁ ለምን ይቀጣችኋል? አይደላችሁም:: እናንተ ከፈጠራቸው መካከል የሆናችሁ ሰዎች ናችሁ:: አላህ ለሚሻው ይምራል:: የሚሻውን ይቀጣል:: የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ያለው ሁሉ ንግስናው የአላህ ብቻ ነው:: መመለሻም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 5

يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ قَدۡ جَآءَكُمۡ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمۡ عَلَىٰ فَتۡرَةٖ مِّنَ ٱلرُّسُلِ أَن تَقُولُواْ مَا جَآءَنَا مِنۢ بَشِيرٖ وَلَا نَذِيرٖۖ فَقَدۡ جَآءَكُم بَشِيرٞ وَنَذِيرٞۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

19. እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! «አብሳሪና አስፈራሪ አልመጣልንም።» እንዳትሉ መልዕክተኞቻችን በተቋረጡበት ጊዜ መመሪያዎችን የሚያብራራ ሆኖ መልዕክተኛችን ሙሐመድ በእርግጥ መጣላችሁ:: አብሳሪና አስፈራሪም በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 5

وَإِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوۡمِهِۦ يَٰقَوۡمِ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ إِذۡ جَعَلَ فِيكُمۡ أَنۢبِيَآءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكٗا وَءَاتَىٰكُم مَّا لَمۡ يُؤۡتِ أَحَدٗا مِّنَ ٱلۡعَٰلَمِينَ

20. ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን በእናንተ ላይ የዋለውን ጸጋ አስታውሱ፣ በውስጣችሁ ነብያትን ባደረገ፤ ነገስታትም ባደረጋችሁና ከአለማት ህዝብ ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ ። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 5

يَٰقَوۡمِ ٱدۡخُلُواْ ٱلۡأَرۡضَ ٱلۡمُقَدَّسَةَ ٱلَّتِي كَتَبَ ٱللَّهُ لَكُمۡ وَلَا تَرۡتَدُّواْ عَلَىٰٓ أَدۡبَارِكُمۡ فَتَنقَلِبُواْ خَٰسِرِينَ

21. ‹‹ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ:: ወደ ኋላችሁም አትመለሱ:: ከሳሪዎች ሆናችሁ ትመለሳላችሁና›› (ባሉ ጊዜ የሆነዉን አስታውስ):: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 5

قَالُواْ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّ فِيهَا قَوۡمٗا جَبَّارِينَ وَإِنَّا لَن نَّدۡخُلَهَا حَتَّىٰ يَخۡرُجُواْ مِنۡهَا فَإِن يَخۡرُجُواْ مِنۡهَا فَإِنَّا دَٰخِلُونَ

22. «ሙሳ ሆይ! በእርሷ ውስጥ ሀያላን ህዝቦች ስላሉ ከእርሷ እስከሚወጡ ድረስ ፈጽሞ አንገባትም:: ከወጡ ግን ገቢዎች ነን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
23 : 5

قَالَ رَجُلَانِ مِنَ ٱلَّذِينَ يَخَافُونَ أَنۡعَمَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمَا ٱدۡخُلُواْ عَلَيۡهِمُ ٱلۡبَابَ فَإِذَا دَخَلۡتُمُوهُ فَإِنَّكُمۡ غَٰلِبُونَۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَتَوَكَّلُوٓاْ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

23. ከእነዚያ አላህን ከሚፈሩትና አላህ ጸጋውን ከለገሰላቸው ሰዎች መካከል ሁለት ሰዎች «በእነርሱ በሀያሎቹ ላይ በሩን ግቡ:: በገባችሁ ጊዜ እናንተ አሸናፊዎች ናችሁ:: ትክክለኛ አማኞችም እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ።» አሏቸው። info
التفاسير: