আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
104 : 5

وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ تَعَالَوۡاْ إِلَىٰ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَإِلَى ٱلرَّسُولِ قَالُواْ حَسۡبُنَا مَا وَجَدۡنَا عَلَيۡهِ ءَابَآءَنَآۚ أَوَلَوۡ كَانَ ءَابَآؤُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ شَيۡـٔٗا وَلَا يَهۡتَدُونَ

104. «አላህ ወደ አወረደውና ወደ መልዕክተኛው ኑ» በተባሉ ጊዜ «አባቶቻችንን ያገኝንበት መንገድ ይበቃናል።» ይላሉ:: አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና ወደ ቀናው መንገድ የማይመሩ ቢሆኑም ይበቃቸዋልን? info
التفاسير:

external-link copy
105 : 5

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ عَلَيۡكُمۡ أَنفُسَكُمۡۖ لَا يَضُرُّكُم مَّن ضَلَّ إِذَا ٱهۡتَدَيۡتُمۡۚ إِلَى ٱللَّهِ مَرۡجِعُكُمۡ جَمِيعٗا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

105. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ማዳን ኃላፊነቱ) በራሳችሁ ላይ ነው። ራሳችሁን ወደቀናው መንገድ ከመራችሁ የሌሎች መሳሳት እናንተን አይጎዳችሁም:: የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ነው። እናም ትሰሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል። info
التفاسير:

external-link copy
106 : 5

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ شَهَٰدَةُ بَيۡنِكُمۡ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ حِينَ ٱلۡوَصِيَّةِ ٱثۡنَانِ ذَوَا عَدۡلٖ مِّنكُمۡ أَوۡ ءَاخَرَانِ مِنۡ غَيۡرِكُمۡ إِنۡ أَنتُمۡ ضَرَبۡتُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَأَصَٰبَتۡكُم مُّصِيبَةُ ٱلۡمَوۡتِۚ تَحۡبِسُونَهُمَا مِنۢ بَعۡدِ ٱلصَّلَوٰةِ فَيُقۡسِمَانِ بِٱللَّهِ إِنِ ٱرۡتَبۡتُمۡ لَا نَشۡتَرِي بِهِۦ ثَمَنٗا وَلَوۡ كَانَ ذَا قُرۡبَىٰ وَلَا نَكۡتُمُ شَهَٰدَةَ ٱللَّهِ إِنَّآ إِذٗا لَّمِنَ ٱلۡأٓثِمِينَ

106. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አንዳችሁ ሞት በመጣበት ጊዜ በኑዛዜ ወቅት በመካከላችሁ ለምስክርነት ከናንተ መካከል ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶች የሆኑ ሰዎች፤ ወይም በምድር ብትጓዙና የሞት አደጋ ብትነካችሁ ከሌሎቻችሁ የሆኑ ሁለት ሌሎች ሰዎች መመስከር ነው:: ብትጠራጠሩም ከአስር ሶላት በኋላ አቁሟቸውና «የሚመሰክርለት ሰው የዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳን በእርሱ ዋጋን አንገዛም:: የአላህን ምስክርነት አንደብቅም:: ያን ጊዜማ ደብቀን ብንገኝ ከኃጢአተኞች ነን።» ብለው በአላህ ስም ይምላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
107 : 5

فَإِنۡ عُثِرَ عَلَىٰٓ أَنَّهُمَا ٱسۡتَحَقَّآ إِثۡمٗا فَـَٔاخَرَانِ يَقُومَانِ مَقَامَهُمَا مِنَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَحَقَّ عَلَيۡهِمُ ٱلۡأَوۡلَيَٰنِ فَيُقۡسِمَانِ بِٱللَّهِ لَشَهَٰدَتُنَآ أَحَقُّ مِن شَهَٰدَتِهِمَا وَمَا ٱعۡتَدَيۡنَآ إِنَّآ إِذٗا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

107. ሆኖም እነርሱ ኃጢአት (በውሸት ምስክርነት) የተገቡ መሆናቸው ቢታወቅ ከእነዚያ ከሟቹ ቅርብ ዘመዶች ውርስ ከተገባቸው ሁለት ሌሎች ሰዎች በስፍራቸው በምስክሮች ስፍራ ይቆሙና «ምስክርነታችን ከእነርሱ ምስክርነት ይልቅ እውነት ነው ወሰንም አላለፍንም። ያን ጊዜ እኛ ከበዳዩቹ ነን።» ሲሉ በአላህ ይምላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
108 : 5

ذَٰلِكَ أَدۡنَىٰٓ أَن يَأۡتُواْ بِٱلشَّهَٰدَةِ عَلَىٰ وَجۡهِهَآ أَوۡ يَخَافُوٓاْ أَن تُرَدَّ أَيۡمَٰنُۢ بَعۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡۗ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱسۡمَعُواْۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡفَٰسِقِينَ

108. ይህ (አሰራር) ምስክርነት በተገቢው ላይ ለማምጣታቸው ወይም ከመሀላዎቻቸው በኋላ የመሀላዎቹ ወደ ወራሾች መመለስን ለመፍራት በጣም የቀረበ ነው:: አላህን ብቻ ፍሩ:: እሱን ብቻ ስሙትም:: አላህ አመጸኛ ሕዝቦችን አይመራምና:: info
التفاسير: