আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
44 : 12

قَالُوٓاْ أَضۡغَٰثُ أَحۡلَٰمٖۖ وَمَا نَحۡنُ بِتَأۡوِيلِ ٱلۡأَحۡلَٰمِ بِعَٰلِمِينَ

44. «ሕልሞችህ ቅዠቶች ናቸው:: እኛም የሕልሞችን ፍች አዋቂዎች አይደለንም።» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
45 : 12

وَقَالَ ٱلَّذِي نَجَا مِنۡهُمَا وَٱدَّكَرَ بَعۡدَ أُمَّةٍ أَنَا۠ أُنَبِّئُكُم بِتَأۡوِيلِهِۦ فَأَرۡسِلُونِ

45. ያም ከሁለቱ መካከል የዳነውና ከብዙ ጊዜ በኋላ ዩሱፍን ያስታወሰው ሰው «እኔ ፍቹን እነግራችኋለሁና ላኩኝ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
46 : 12

يُوسُفُ أَيُّهَا ٱلصِّدِّيقُ أَفۡتِنَا فِي سَبۡعِ بَقَرَٰتٖ سِمَانٖ يَأۡكُلُهُنَّ سَبۡعٌ عِجَافٞ وَسَبۡعِ سُنۢبُلَٰتٍ خُضۡرٖ وَأُخَرَ يَابِسَٰتٖ لَّعَلِّيٓ أَرۡجِعُ إِلَى ٱلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَعۡلَمُونَ

46. «አንተ እውነተኛው ዩሱፍ ሆይ! ሰባትን የሰቡ ላሞች ሰባት ከሲታዎች ላሞች ሲበሏቸው፤ ሰባትን ለምለም ዘለላዎችም ሌሎች ሰባት ደረቆች በእነርሱ ላይ ስብርብር ሲያደርጉ ያየን ሰው ሕልም ፍች እስቲ ተችልን:: ያውቁ ዘንድ ወደ ሰዎቹ ልመለስ እከጅላለሁና።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
47 : 12

قَالَ تَزۡرَعُونَ سَبۡعَ سِنِينَ دَأَبٗا فَمَا حَصَدتُّمۡ فَذَرُوهُ فِي سُنۢبُلِهِۦٓ إِلَّا قَلِيلٗا مِّمَّا تَأۡكُلُونَ

47. እርሱም አለ: «ሰባትን የተከታተሉ ዓመታት ትዘራላችሁ ያጨዳችሁትንም ሁሉ ከምትበሉት ጥቂት በስተቀር በዘለላው ውስጥ ተውት። info
التفاسير:

external-link copy
48 : 12

ثُمَّ يَأۡتِي مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ سَبۡعٞ شِدَادٞ يَأۡكُلۡنَ مَا قَدَّمۡتُمۡ لَهُنَّ إِلَّا قَلِيلٗا مِّمَّا تُحۡصِنُونَ

48. «ከዚያም ከነዚያ በኋላ ካደለባችሁት ጥቂት ሲቀር ለእነርሱ ያደለባችሁትን ሁሉ የሚበሉ ሰባት የችግር ዓመታት ይመጣሉ። info
التفاسير:

external-link copy
49 : 12

ثُمَّ يَأۡتِي مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ عَامٞ فِيهِ يُغَاثُ ٱلنَّاسُ وَفِيهِ يَعۡصِرُونَ

49. «ከዚያ ከእነዚያ በኋላ ሰዎቹ በእርሱ ዝናብ የሚያገኙበትና በእርሱም ወይንን የሚጨምቁበት ዓመት ይመጣል።» info
التفاسير:

external-link copy
50 : 12

وَقَالَ ٱلۡمَلِكُ ٱئۡتُونِي بِهِۦۖ فَلَمَّا جَآءَهُ ٱلرَّسُولُ قَالَ ٱرۡجِعۡ إِلَىٰ رَبِّكَ فَسۡـَٔلۡهُ مَا بَالُ ٱلنِّسۡوَةِ ٱلَّٰتِي قَطَّعۡنَ أَيۡدِيَهُنَّۚ إِنَّ رَبِّي بِكَيۡدِهِنَّ عَلِيمٞ

50. ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ።» አለ። መልእክተኛዉም ወደ ዩሱፍ በመጣ ጊዜ ዩሱፍ: «ወደ ጌታህ ተመለስና የእነዚያን እጆቻቸውን የቆረጡትን ሴቶች ሁኔታ ጠይቀው ጌታዬ ተንኮላቸውን አዋቂ ነውና።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
51 : 12

قَالَ مَا خَطۡبُكُنَّ إِذۡ رَٰوَدتُّنَّ يُوسُفَ عَن نَّفۡسِهِۦۚ قُلۡنَ حَٰشَ لِلَّهِ مَا عَلِمۡنَا عَلَيۡهِ مِن سُوٓءٖۚ قَالَتِ ٱمۡرَأَتُ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡـَٰٔنَ حَصۡحَصَ ٱلۡحَقُّ أَنَا۠ رَٰوَدتُّهُۥ عَن نَّفۡسِهِۦ وَإِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

51. ንጉሡም «ዩሱፍን ከነፍሱ ባባበላችሁት ጊዜ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው። «ለአላህ ጥራት ይገባው በእርሱ ላይ ምንም መጥፎን ነገር አላወቅንም (አላየንም)።» አሉት። የዐዚዝ ሚስትም አለች: «አሁን እውነቱ ተገለጸ እኔ አባበልኩት እርሱም ከእውነተኞቹ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
52 : 12

ذَٰلِكَ لِيَعۡلَمَ أَنِّي لَمۡ أَخُنۡهُ بِٱلۡغَيۡبِ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي كَيۡدَ ٱلۡخَآئِنِينَ

52. «ይህ ጌታዬ ሩቅ ሆኖ ሳለ ያልከዳሁት መሆኔንና አላህም የከዳተኞችን ተንኮል የማያቃና መሆኑን እንዲያውቅ ነው።» info
التفاسير: