আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
87 : 12

يَٰبَنِيَّ ٱذۡهَبُواْ فَتَحَسَّسُواْ مِن يُوسُفَ وَأَخِيهِ وَلَا تَاْيۡـَٔسُواْ مِن رَّوۡحِ ٱللَّهِۖ إِنَّهُۥ لَا يَاْيۡـَٔسُ مِن رَّوۡحِ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡقَوۡمُ ٱلۡكَٰفِرُونَ

87. «ልጆቼ ሆይ! ሂዱ ከዩሱፍና ከወንድሙም ወሬ ተመራመሩ:: ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ:: እነሆ ከአላህ እዝነት ከሓዲያን ህዝቦች እንጂ ማንም ተስፋ አይቆርጥም።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
88 : 12

فَلَمَّا دَخَلُواْ عَلَيۡهِ قَالُواْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡعَزِيزُ مَسَّنَا وَأَهۡلَنَا ٱلضُّرُّ وَجِئۡنَا بِبِضَٰعَةٖ مُّزۡجَىٰةٖ فَأَوۡفِ لَنَا ٱلۡكَيۡلَ وَتَصَدَّقۡ عَلَيۡنَآۖ إِنَّ ٱللَّهَ يَجۡزِي ٱلۡمُتَصَدِّقِينَ

88. በእርሱም ላይ በገቡ ጊዜ: «አንተ የተከበርከው ሆይ! እኛንም ቤተሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን። እርካሽ ሸቀጥም ይዘን መጥተናል:: ስፍርንም ለእኛ ሙላልን:: በእኛም ላይ መጽውት:: አላህ መጽዋቾችን ይመነዳልና።» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
89 : 12

قَالَ هَلۡ عَلِمۡتُم مَّا فَعَلۡتُم بِيُوسُفَ وَأَخِيهِ إِذۡ أَنتُمۡ جَٰهِلُونَ

89. «እናንተ የማታውቁ በነበራችሁ ጊዜ በዩሱፍና በወንድሙ ላይ የሠራችሁትን ግፍ አወቃችሁን?» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
90 : 12

قَالُوٓاْ أَءِنَّكَ لَأَنتَ يُوسُفُۖ قَالَ أَنَا۠ يُوسُفُ وَهَٰذَآ أَخِيۖ قَدۡ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡنَآۖ إِنَّهُۥ مَن يَتَّقِ وَيَصۡبِرۡ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ

90. «አንተ በእርግጥ አንተ ዩሱፍ ነህን?» አሉት። «አዎ እኔ በትክክል ዩሱፍ ነኝ:: ይህም ወንድሜ ነው:: አላህ በእኛ ላይ በእርግጥ ለገሰልን:: እነሆ የሚጠነቀቅና የሚታገስ ሰው አላህ ይክሰዋል:: አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ አያጠፋምና።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
91 : 12

قَالُواْ تَٱللَّهِ لَقَدۡ ءَاثَرَكَ ٱللَّهُ عَلَيۡنَا وَإِن كُنَّا لَخَٰطِـِٔينَ

91. «በአላህ እንምላለን! አላህ በእኛ ላይ በእርግጥ አበለጠህ፤ እኛም በእርግጥ አጥፊዎች ነበርን።» አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
92 : 12

قَالَ لَا تَثۡرِيبَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡيَوۡمَۖ يَغۡفِرُ ٱللَّهُ لَكُمۡۖ وَهُوَ أَرۡحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ

92. እርሱም አላቸው: «ዛሬ በእናንተ ላይ ምንም ወቀሳ የለባችሁም። አላህ ለእናንተ ይምራል። እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነውና።» info
التفاسير:

external-link copy
93 : 12

ٱذۡهَبُواْ بِقَمِيصِي هَٰذَا فَأَلۡقُوهُ عَلَىٰ وَجۡهِ أَبِي يَأۡتِ بَصِيرٗا وَأۡتُونِي بِأَهۡلِكُمۡ أَجۡمَعِينَ

93. «ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ ሂዱ:: በአባቴ ፊትም ጣሉት:: የሚያይ ሆኖ ይመጣልና:: ቤተሰቦቻችሁንም በሙሉ ሰብስባችሁ አምጡልኝ።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
94 : 12

وَلَمَّا فَصَلَتِ ٱلۡعِيرُ قَالَ أَبُوهُمۡ إِنِّي لَأَجِدُ رِيحَ يُوسُفَۖ لَوۡلَآ أَن تُفَنِّدُونِ

94. ግመል ጫኞችም ከግብጽ በወጡ ጊዜ አባታቸው «እኔ የዩሱፍን ሽታ በእርግጥ አገኛለሁ:: ባታቄሉኝ ኖሮ ታምኑኝ ነበር።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
95 : 12

قَالُواْ تَٱللَّهِ إِنَّكَ لَفِي ضَلَٰلِكَ ٱلۡقَدِيمِ

95. «በአላህ እንምላለን! አንተ በእርግጥ እስካሁንም በዚያው በቀድሞው ስህተትህ ውስጥ ነህ።» አሉት። info
التفاسير: