আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
5 : 12

قَالَ يَٰبُنَيَّ لَا تَقۡصُصۡ رُءۡيَاكَ عَلَىٰٓ إِخۡوَتِكَ فَيَكِيدُواْ لَكَ كَيۡدًاۖ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ لِلۡإِنسَٰنِ عَدُوّٞ مُّبِينٞ

5. አባቱም አለ: «ልጄ ሆይ! ይህን ህልምህን ለወንድሞችህ አትንገር። ባንተ ላይ ተንኮል እንዳያሴሩ። ምክንያቱም ሰይጣን ለሰው ልጅ ሁልጊዜም ግልጽ ጠላት ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 12

وَكَذَٰلِكَ يَجۡتَبِيكَ رَبُّكَ وَيُعَلِّمُكَ مِن تَأۡوِيلِ ٱلۡأَحَادِيثِ وَيُتِمُّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكَ وَعَلَىٰٓ ءَالِ يَعۡقُوبَ كَمَآ أَتَمَّهَا عَلَىٰٓ أَبَوَيۡكَ مِن قَبۡلُ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡحَٰقَۚ إِنَّ رَبَّكَ عَلِيمٌ حَكِيمٞ

6. «ጌታህ ልክ ይህን ህልም እንዳሳየህ ሁሉ ለነብይነትም ይመርጥሃል:: የንንግግሮችን ፍፃሜ ያስተምርሃል:: ጸጋውንም ቀደም ሲል ለአባቶችህ ለኢብራሂምና ለኢስሃቅ እንደሞላ ሁሉ ላንተና ለያዕቁብ ቤተሰቦችም ይሞላል:: ጌታህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።» info
التفاسير:

external-link copy
7 : 12

۞ لَّقَدۡ كَانَ فِي يُوسُفَ وَإِخۡوَتِهِۦٓ ءَايَٰتٞ لِّلسَّآئِلِينَ

7. በዩሱፍና በወንድሞቹ ታሪክ ዉስጥ እውቀትን በመሻት ለሚጠይቁ ሁሉ እያሌ ተዓምራት አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 12

إِذۡ قَالُواْ لَيُوسُفُ وَأَخُوهُ أَحَبُّ إِلَىٰٓ أَبِينَا مِنَّا وَنَحۡنُ عُصۡبَةٌ إِنَّ أَبَانَا لَفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ

8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) ባሉ ጊዜ: «እኛ በቁጥር ብዙዎች ሁነን እያለ ዩሱፍና ወንድሙ (ብንያም) ከአባታችን ዘንድ ከእኛ ይበልጥ ተወዳጆች ናቸው:: በእውነቱ አባታችን ግልጽ ስህተት ውስጥ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 12

ٱقۡتُلُواْ يُوسُفَ أَوِ ٱطۡرَحُوهُ أَرۡضٗا يَخۡلُ لَكُمۡ وَجۡهُ أَبِيكُمۡ وَتَكُونُواْ مِنۢ بَعۡدِهِۦ قَوۡمٗا صَٰلِحِينَ

9. «ዩሱፍን ግደሉት ወይም እሩቅ ቦታ ጣሉት:: ይህን ካረጋችሁ የአባታችሁን ፊት ትኩረትና ውዴታ የራሳችሁ ብቻ ታደርጋላችሁ:: ከዚህ በኋላ ከኃጥያታችሁ በመመለስ መልካም ሰዎች ትሆናለችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 12

قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ لَا تَقۡتُلُواْ يُوسُفَ وَأَلۡقُوهُ فِي غَيَٰبَتِ ٱلۡجُبِّ يَلۡتَقِطۡهُ بَعۡضُ ٱلسَّيَّارَةِ إِن كُنتُمۡ فَٰعِلِينَ

10. ከእነሱ አንድ ተናጋሪ «ዩሱፍን አትግደሉ ግን በጉድጓድ አዘቅት ጨለማ ውስጥ ጣሉት፤ ከተጓዢዎች አንዱ ያነሳዋልና፡፡ ሠሪዎች ብትኾኑ (በዚሁ ተብቃቁ) አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 12

قَالُواْ يَٰٓأَبَانَا مَا لَكَ لَا تَأۡمَ۬نَّا عَلَىٰ يُوسُفَ وَإِنَّا لَهُۥ لَنَٰصِحُونَ

11. አሉም: «አባታችን ሆይ! በዩሱፍ ጉዳይ እኛ ለእርሱ ቅን አሳቢዎች ሁነን ሳለ ለምን አታምነንም? info
التفاسير:

external-link copy
12 : 12

أَرۡسِلۡهُ مَعَنَا غَدٗا يَرۡتَعۡ وَيَلۡعَبۡ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ

12. «እስቲ ይዝናና ይጫወት ዘንድ ነገ ከእኛ ጋር አብረህ ላከው::እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን።» info
التفاسير:

external-link copy
13 : 12

قَالَ إِنِّي لَيَحۡزُنُنِيٓ أَن تَذۡهَبُواْ بِهِۦ وَأَخَافُ أَن يَأۡكُلَهُ ٱلذِّئۡبُ وَأَنتُمۡ عَنۡهُ غَٰفِلُونَ

13. አባቱም «እርሱን መውሰዳችሁ ያሳዝነኛል። ዘንግታችሁት ተኩላ እንዳይበላዉም እፈራለሁ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
14 : 12

قَالُواْ لَئِنۡ أَكَلَهُ ٱلذِّئۡبُ وَنَحۡنُ عُصۡبَةٌ إِنَّآ إِذٗا لَّخَٰسِرُونَ

14. እነርሱም «እኛ እንዲህ ጭፍሮች ሆነን ተኩላ ከበላውማ ከሳሪዎቹ እኛ ነን።» አሉ። info
التفاسير: