ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا

رقم الصفحة: 95:77 close

external-link copy
106 : 4

وَٱسۡتَغۡفِرِ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورٗا رَّحِيمٗا

106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህን ምህረት ለምነው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
107 : 4

وَلَا تُجَٰدِلۡ عَنِ ٱلَّذِينَ يَخۡتَانُونَ أَنفُسَهُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ خَوَّانًا أَثِيمٗا

107. ለእነዚያ ነፍሶቻቸውን ስለሚያታልሉት ሰዎች አትከራከር:: አላህ ከዳተኛንና ኃጢአተኛን ሰው አይወድምና:: info
التفاسير:

external-link copy
108 : 4

يَسۡتَخۡفُونَ مِنَ ٱلنَّاسِ وَلَا يَسۡتَخۡفُونَ مِنَ ٱللَّهِ وَهُوَ مَعَهُمۡ إِذۡ يُبَيِّتُونَ مَا لَا يَرۡضَىٰ مِنَ ٱلۡقَوۡلِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ بِمَا يَعۡمَلُونَ مُحِيطًا

108. ከሰው ይደበቃሉ:: አላህ በዕውቀቱ ከእነርሱ ጋር ሲሆን ከንግግር የማይወደውን ነገር በልቦቻቸው በሚያሳድሩ ጊዜ ከእርሱ አይደበቁም:: አላህ በሚሰሩት ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
109 : 4

هَٰٓأَنتُمۡ هَٰٓؤُلَآءِ جَٰدَلۡتُمۡ عَنۡهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا فَمَن يُجَٰدِلُ ٱللَّهَ عَنۡهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ أَم مَّن يَكُونُ عَلَيۡهِمۡ وَكِيلٗا

109. እነሆ እናንተ እነዚያ በቅርቢቱ ሕይወት ውስጥ ከእነርሱ ተከራከራችሁ:: በትንሳኤ ቀን አላህን ስለ እነርሱ የሚከራከርላቸው ማን ነው? ወይስ ለእነርሱ ሀላፊ የሚሆን ማን ነው? info
التفاسير:

external-link copy
110 : 4

وَمَن يَعۡمَلۡ سُوٓءًا أَوۡ يَظۡلِمۡ نَفۡسَهُۥ ثُمَّ يَسۡتَغۡفِرِ ٱللَّهَ يَجِدِ ٱللَّهَ غَفُورٗا رَّحِيمٗا

110. መጥፎ ነገር የሚሰራ ወይም ነፍሱን የሚበድልና ከዚያም ተጸጽቶ አላህን ምህረት የሚለምን ሁሉ አላህን መሀሪና አዛኝ ሆኖ ያገኘዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
111 : 4

وَمَن يَكۡسِبۡ إِثۡمٗا فَإِنَّمَا يَكۡسِبُهُۥ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا

111. ኃጢአት የሚሰራም የሚሰራው ጥፋት ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
112 : 4

وَمَن يَكۡسِبۡ خَطِيٓـَٔةً أَوۡ إِثۡمٗا ثُمَّ يَرۡمِ بِهِۦ بَرِيٓـٔٗا فَقَدِ ٱحۡتَمَلَ بُهۡتَٰنٗا وَإِثۡمٗا مُّبِينٗا

112. ኃጢአትን ወይም ወንጀልን የሚሰራና ከዚያም በእርሱ ንጹህን የሚሰድብ ቅጥፈትንና ግልጽ ኃጢአትን በቁርጥ ተሸከመ:: info
التفاسير:

external-link copy
113 : 4

وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكَ وَرَحۡمَتُهُۥ لَهَمَّت طَّآئِفَةٞ مِّنۡهُمۡ أَن يُضِلُّوكَ وَمَا يُضِلُّونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمۡۖ وَمَا يَضُرُّونَكَ مِن شَيۡءٖۚ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمۡ تَكُن تَعۡلَمُۚ وَكَانَ فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكَ عَظِيمٗا

113. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባንተ ላይ ባልነበረ ኖሮ ከእነርሱ የሆነ ቡድኖች ሊያሳስቱህ ባሰቡ ነበር:: ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላ አያሳስቱም:: በምንም አይጎዱህም:: አላህ ባንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ:: የማታውቀውን ሁሉ አስተማረህ:: የአላህ ችሮታ ባንተ ላይ ታላቅ ነው:: info
التفاسير: