لَّا يَسۡتَوِي ٱلۡقَٰعِدُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ غَيۡرُ أُوْلِي ٱلضَّرَرِ وَٱلۡمُجَٰهِدُونَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡۚ فَضَّلَ ٱللَّهُ ٱلۡمُجَٰهِدِينَ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ عَلَى ٱلۡقَٰعِدِينَ دَرَجَةٗۚ وَكُلّٗا وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ وَفَضَّلَ ٱللَّهُ ٱلۡمُجَٰهِدِينَ عَلَى ٱلۡقَٰعِدِينَ أَجۡرًا عَظِيمٗا
95. ከአማኞች የጉዳት ባለቤት ከሆኑት በስተቀር ተቀማጮቹ እና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉት አይስተካከሉም:: በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉትን አላህ በተቀማጮቹ ላይ በደረጃ አበለጠ:: ለሁሉም አላህ መልካሚቱን (ገነት) ተስፋ ሰጠ (ቃል ኪዳን ገባ):: ታጋዮቹንም በተቀማጮቹ ላይ አላህ በታላቅ ምንዳ አበለጠ::
التفاسير: