የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

አል ሐዲድ

external-link copy
1 : 57

سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

1. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉ ሁሉ አላህን አጠሩ። እርሱም ኃያሉና ጥበበኛው ነው። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 57

لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

2. የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱው ብቻ ነው:: ሕይወትን የሚሰጥና ሕይወትን የሚነሳ እሱው ብቻ ነው:: እርሱ ሁሉንም ነገር ቻይ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 57

هُوَ ٱلۡأَوَّلُ وَٱلۡأٓخِرُ وَٱلظَّٰهِرُ وَٱلۡبَاطِنُۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٌ

3. እርሱ ( ከበፊቱ ምንም ያልቀደመው) የመጀመሪያ! (ፊት ያለ) (ከኋላው ምንም የሌለ የመጨረሻ) ብቻዉን ቀሪ፤ ከበላዩ ማንም የሌለ (ግልጽና የበላይ) ስውርም (ድብቅ) ነው:: እርሱ (በምድርም ሆነ በሰማይ ያለን) ሁሉ ነገር አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 57

هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يَعۡلَمُ مَا يَلِجُ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا يَخۡرُجُ مِنۡهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا يَعۡرُجُ فِيهَاۖ وَهُوَ مَعَكُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ

4. እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ብቻ የፈጠረ ነው:: ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ አለ። ወደ ምድር የሚገባውንና ከእርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: ከሰማይ የሚወረደውንና ወደ እርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: እርሱ የትም ብትሆኑ (በእውቀቱ) ከናንተው ጋር ነው:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 57

لَّهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ

5. የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 57

يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِۚ وَهُوَ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

6. ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል:: ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል:: እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ሁሉ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 57

ءَامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَأَنفِقُواْ مِمَّا جَعَلَكُم مُّسۡتَخۡلَفِينَ فِيهِۖ فَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡ وَأَنفَقُواْ لَهُمۡ أَجۡرٞ كَبِيرٞ

7. (ሰዎች ሆይ!) በአላህና በመልዕክተኛው እመኑ:: አላህ በእርሱ ላይ ተተካኪዎች ካደረጋችሁ ገንዘብ ዉስጥም ለግሱ:: እነዚያ ከእናንተ መካከል በአላህ ያመኑትና የለገሱት ሁሉ ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ አለላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 57

وَمَا لَكُمۡ لَا تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلرَّسُولُ يَدۡعُوكُمۡ لِتُؤۡمِنُواْ بِرَبِّكُمۡ وَقَدۡ أَخَذَ مِيثَٰقَكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

8. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁም ቃልኪዳናችሁን የያዘባችሁ ሲሆን መልዕክተኛውም በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲሆን በአላህ የማታምኑበት ምን ምክኒያት አላችሁ? እናንተ በትክክል የምታምኑ ከሆናችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
9 : 57

هُوَ ٱلَّذِي يُنَزِّلُ عَلَىٰ عَبۡدِهِۦٓ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖ لِّيُخۡرِجَكُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ بِكُمۡ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٞ

9. እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሀን ሊያወጣችሁ ግልፆች የሆኑን አናቅጽ በባሪያው ላይ የሚያወርድ ነው:: አላህ ለእናንተ በእርግጥ ሩህሩህ አዛኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 57

وَمَا لَكُمۡ أَلَّا تُنفِقُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلِلَّهِ مِيرَٰثُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ لَا يَسۡتَوِي مِنكُم مَّنۡ أَنفَقَ مِن قَبۡلِ ٱلۡفَتۡحِ وَقَٰتَلَۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَعۡظَمُ دَرَجَةٗ مِّنَ ٱلَّذِينَ أَنفَقُواْ مِنۢ بَعۡدُ وَقَٰتَلُواْۚ وَكُلّٗا وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ

10. የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ሲሆን በአላህ መንገድ የማትለግሱበት ምን ምክንያት አላችሁ? ከናንተ መካከል ከመካ መከፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው ከተከፈተ በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ሰው ጋር አይስተከከልም:: ከእነዚያ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸውና:: ሁሉንም አላህ የመልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 57

مَّن ذَا ٱلَّذِي يُقۡرِضُ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنٗا فَيُضَٰعِفَهُۥ لَهُۥ وَلَهُۥٓ أَجۡرٞ كَرِيمٞ

11. ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ አላህ ምንዳውን የሚያነባብርለት ሰው ማን ነው? ለእርሱም መልካም ምንዳ አለው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 57

يَوۡمَ تَرَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ يَسۡعَىٰ نُورُهُم بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَبِأَيۡمَٰنِهِمۖ بُشۡرَىٰكُمُ ٱلۡيَوۡمَ جَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ

12. ወንድ ትክክለኛ አማኞችንና ሴት ትክክለኛ አማኞችን በስተፊቶቻቸው በቀኞቻቸዉም ብርሀናቸው የሚሮጥ ሲሆን በምታያቸው ቀን (ታላቅ ምንዳ አለላቸው።) "ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትኾኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ናቸው (ይባላሉ)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ እድል ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 57

يَوۡمَ يَقُولُ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتُ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱنظُرُونَا نَقۡتَبِسۡ مِن نُّورِكُمۡ قِيلَ ٱرۡجِعُواْ وَرَآءَكُمۡ فَٱلۡتَمِسُواْ نُورٗاۖ فَضُرِبَ بَيۡنَهُم بِسُورٖ لَّهُۥ بَابُۢ بَاطِنُهُۥ فِيهِ ٱلرَّحۡمَةُ وَظَٰهِرُهُۥ مِن قِبَلِهِ ٱلۡعَذَابُ

13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የወንድ አስመሳዮችና የሴት አስመሳዮች ለእነዚያ በአላህ ላመኑት "ጠብቁን ከብርሀናችሁ እናበራለንና" የሚሉበትን ቀን አስታውስ:: "ወደ ኋላችሁ ተመለሱ:: ብርሀንንም እዚያው ፈልጉ" ይባላሉ:: በመካከላቸዉም ለእርሱ ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል:: ግቢው በውስጡ ገነት ያለበት ከውጪዉም በኩሉ ደግሞ የእሳት (ስቃይ) ያለበት የሆነ (ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል)። info
التفاسير:

external-link copy
14 : 57

يُنَادُونَهُمۡ أَلَمۡ نَكُن مَّعَكُمۡۖ قَالُواْ بَلَىٰ وَلَٰكِنَّكُمۡ فَتَنتُمۡ أَنفُسَكُمۡ وَتَرَبَّصۡتُمۡ وَٱرۡتَبۡتُمۡ وَغَرَّتۡكُمُ ٱلۡأَمَانِيُّ حَتَّىٰ جَآءَ أَمۡرُ ٱللَّهِ وَغَرَّكُم بِٱللَّهِ ٱلۡغَرُورُ

14. "ከናንተ ጋር አልነበርንምን?" በማለት ይጠሯቸዋል:: "እውነት ነው እኛ ጋር ነበራችሁ:: ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ:: በነብዩ አደጋዎችን ተጠባበቃችሁ ትጠራጠራላችሁም:: የአላህ ትዕዛዝ እስከ መጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ። አታላዩም ሰይጣን በአላህ መታገስ ሸነገላችሁ ይሏቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 57

فَٱلۡيَوۡمَ لَا يُؤۡخَذُ مِنكُمۡ فِدۡيَةٞ وَلَا مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۚ مَأۡوَىٰكُمُ ٱلنَّارُۖ هِيَ مَوۡلَىٰكُمۡۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ

15. በመሆኑም ዛሬ ከናንተም ሆነ በአላህ ከካዱት ሰዎች የገንዘብ ክፍያ (ቤዛ) አይወሰድም:: መኖሪያችሁ የገሀነም እሳት ብቻ ናት:: እርሷ ተገቢያችሁ ናትና:: የገሀነም እሳት መመለሻነቷ ምን ትከፋም" (ይሏቸዋል):: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 57

۞ أَلَمۡ يَأۡنِ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَن تَخۡشَعَ قُلُوبُهُمۡ لِذِكۡرِ ٱللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ ٱلۡحَقِّ وَلَا يَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلُ فَطَالَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡأَمَدُ فَقَسَتۡ قُلُوبُهُمۡۖ وَكَثِيرٞ مِّنۡهُمۡ فَٰسِقُونَ

16. ለእነዚያ (በአላህ) ላመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው እውነታ ልቦቻቸው ሊፈሩ፤ እንደነዚያ በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ ስለ ረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁባቸው ህዝቦች የማይሆኑበት ጊዜ አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 57

ٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يُحۡيِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَاۚ قَدۡ بَيَّنَّا لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ

17. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው የሚደርጋት መሆኑን እወቁ። ታውቁም ዘንድ አናቅጽን ለእናንተ በእርግጥ አብራራንላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
18 : 57

إِنَّ ٱلۡمُصَّدِّقِينَ وَٱلۡمُصَّدِّقَٰتِ وَأَقۡرَضُواْ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنٗا يُضَٰعَفُ لَهُمۡ وَلَهُمۡ أَجۡرٞ كَرِيمٞ

18. የመጸወቱ ወንዶችና የመጸወቱ ሴቶች ለአላህ መልካምን ብድር ያበደሩ ሁሉ ለእነርሱም ምንዳ ይደራረብላቸዋል:: ለእነርሱም መልካም የተከበረ ምንዳ አለላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 57

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦٓ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصِّدِّيقُونَۖ وَٱلشُّهَدَآءُ عِندَ رَبِّهِمۡ لَهُمۡ أَجۡرُهُمۡ وَنُورُهُمۡۖ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَآ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَحِيمِ

19. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ ያመኑ ሰዎች እነዚያ እነርሱ በጣም እውነቶኞች በጌታቸዉም ዘንድ መስካሪዎች ናቸው:: ለእነርሱ ምንዳቸውም ብርሀናቸዉም አለላቸው:: እነዚያ (በአላህ) የካዱትና በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሰዎች ደግሞ የእሳት ጓዶች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 57

ٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَا ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا لَعِبٞ وَلَهۡوٞ وَزِينَةٞ وَتَفَاخُرُۢ بَيۡنَكُمۡ وَتَكَاثُرٞ فِي ٱلۡأَمۡوَٰلِ وَٱلۡأَوۡلَٰدِۖ كَمَثَلِ غَيۡثٍ أَعۡجَبَ ٱلۡكُفَّارَ نَبَاتُهُۥ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَىٰهُ مُصۡفَرّٗا ثُمَّ يَكُونُ حُطَٰمٗاۖ وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِ عَذَابٞ شَدِيدٞ وَمَغۡفِرَةٞ مِّنَ ٱللَّهِ وَرِضۡوَٰنٞۚ وَمَا ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَآ إِلَّا مَتَٰعُ ٱلۡغُرُورِ

20. (ሰዎች ሆይ!) ቅርቢቱን ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፤ ማጌጫም፤ በመካከችሁም መፎካከሪያ፤ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መሆኗን እወቁ:: እርሷ በቃዩ ገበሬዎችን ቡቃያው እንደሚያስደስት ዝናብና ከዚያ በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደሚታየው ከዚም የተሰባበረ እንደሚሆን ብጤ ነው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ለአጥፊዎች ብርቱ ቅጣት፤ ለትክክለኛ አማኞች ከአላህ ምህረትና ውዴታ አለ:: የቅርቢቱ ሕይወት እኮ የመታለያ ጥቅም እንጂ ሌላ አይደለችም:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 57

سَابِقُوٓاْ إِلَىٰ مَغۡفِرَةٖ مِّن رَّبِّكُمۡ وَجَنَّةٍ عَرۡضُهَا كَعَرۡضِ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ أُعِدَّتۡ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦۚ ذَٰلِكَ فَضۡلُ ٱللَّهِ يُؤۡتِيهِ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ ذُو ٱلۡفَضۡلِ ٱلۡعَظِيمِ

21. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህና በመልዕክተኞች ላመኑት ወደ ተዘጋጀችውና የወርዷ ስፋት እንደ ሰማይና ምድር ወደ ሆነችም ገነት ተሸቀዳደሙ:: ይህ የአላህ ችሮታ ነው:: ለሚፈልገው ሰው ብቻ ይሰጠዋል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 57

مَآ أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فِيٓ أَنفُسِكُمۡ إِلَّا فِي كِتَٰبٖ مِّن قَبۡلِ أَن نَّبۡرَأَهَآۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ

22. በምድርም ሆነ በነፍሶቻችሁ መከራ ማንንም አታጋጥምም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትሆን እንጂ:: ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 57

لِّكَيۡلَا تَأۡسَوۡاْ عَلَىٰ مَا فَاتَكُمۡ وَلَا تَفۡرَحُواْ بِمَآ ءَاتَىٰكُمۡۗ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخۡتَالٖ فَخُورٍ

23. (ይህን ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑና አላህ በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው:: አላህ ኩራተኛንና ጉረኛን ሁሉ አይወድምና:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 57

ٱلَّذِينَ يَبۡخَلُونَ وَيَأۡمُرُونَ ٱلنَّاسَ بِٱلۡبُخۡلِۗ وَمَن يَتَوَلَّ فَإِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ

24. እነርሱም እነዚያ የሚሰስቱና ሰዎችንም በስስት ላይ የሚያዙ ናቸው:: ከእውነት የሚሸሽ (ሰው) ሁሉ ጉዳቱ ለራሱ ብቻ ነው:: አላህ ተብቃቂ ና ምስጉን ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 57

لَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا رُسُلَنَا بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلۡنَا مَعَهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَأَنزَلۡنَا ٱلۡحَدِيدَ فِيهِ بَأۡسٞ شَدِيدٞ وَمَنَٰفِعُ لِلنَّاسِ وَلِيَعۡلَمَ ٱللَّهُ مَن يَنصُرُهُۥ وَرُسُلَهُۥ بِٱلۡغَيۡبِۚ إِنَّ ٱللَّهَ قَوِيٌّ عَزِيزٞ

25. መልዕክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች አጠናክረን በእርግጥ ላክን:: ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን:: ብረትንም ከውስጡ ብርቱ ኃይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲሆን አወረድን:: አላህ ሃይማኖትንና መልዕክተኞችን በሩቁ ሆኖ የሚረዳውን (ሰው) ሊያውቅ (ሊገልጽ) አወረደው:: አላህ ብርቱና አሸናፊ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 57

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحٗا وَإِبۡرَٰهِيمَ وَجَعَلۡنَا فِي ذُرِّيَّتِهِمَا ٱلنُّبُوَّةَ وَٱلۡكِتَٰبَۖ فَمِنۡهُم مُّهۡتَدٖۖ وَكَثِيرٞ مِّنۡهُمۡ فَٰسِقُونَ

26. ኑህንና ኢብራሂምን በእርግጥ ላክን:: በዘሮቻቸዉም ውስጥ ነብይነትንና መጽሐፍትን አደረግን:: ከእነርሱም መካከል ቅን ሰው አለ:: ከእነርሱም መካከል ብዙዎቹ ግን አመጸኞች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 57

ثُمَّ قَفَّيۡنَا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيۡنَا بِعِيسَى ٱبۡنِ مَرۡيَمَ وَءَاتَيۡنَٰهُ ٱلۡإِنجِيلَۖ وَجَعَلۡنَا فِي قُلُوبِ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُ رَأۡفَةٗ وَرَحۡمَةٗۚ وَرَهۡبَانِيَّةً ٱبۡتَدَعُوهَا مَا كَتَبۡنَٰهَا عَلَيۡهِمۡ إِلَّا ٱبۡتِغَآءَ رِضۡوَٰنِ ٱللَّهِ فَمَا رَعَوۡهَا حَقَّ رِعَايَتِهَاۖ فَـَٔاتَيۡنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنۡهُمۡ أَجۡرَهُمۡۖ وَكَثِيرٞ مِّنۡهُمۡ فَٰسِقُونَ

27. ከዚያም በእነርሱ ፈለጋቸው ላይ መልዕክተኞችን አከታተልን:: የመርየም ልጅን ዒሳንም አስከተልን:: ኢንጂልንም ሰጠነው:: በእነዚያም በተከተሉት ሰዎች ልቦች ውስጥ መለዘብንና እዝነትን አደረግን፤ አዲስ የፈጠሯትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልደነገግንም:: ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ከራሳቸው ፈጠሯት:: ተገቢ አጠባበቅንም አልጠበቋትም:: ከእነርሱም መካከል በአላህ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው:: ከእነርሱ ብዙዎቹ ግን አመጸኞች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 57

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَءَامِنُواْ بِرَسُولِهِۦ يُؤۡتِكُمۡ كِفۡلَيۡنِ مِن رَّحۡمَتِهِۦ وَيَجۡعَل لَّكُمۡ نُورٗا تَمۡشُونَ بِهِۦ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

28. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: በመልክተኛዉም እመኑ:: ከችሮታው ሁለትን ክፍሎች ይሰጣችኋልና:: ለእናተም የምትሄዱበትን ብርሃን ያደርግላችኋል:: ለእናንተም ወንጀላችሁን ይምራል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 57

لِّئَلَّا يَعۡلَمَ أَهۡلُ ٱلۡكِتَٰبِ أَلَّا يَقۡدِرُونَ عَلَىٰ شَيۡءٖ مِّن فَضۡلِ ٱللَّهِ وَأَنَّ ٱلۡفَضۡلَ بِيَدِ ٱللَّهِ يُؤۡتِيهِ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ ذُو ٱلۡفَضۡلِ ٱلۡعَظِيمِ

29. (ይህም) የመጽሐፍ ሰዎች ከአላህ ችሮታ በምንም ላይ የማይችሉ መሆናቸውንና ችሮታዉም አላህ ለሚሻው ሰው ብቻ የሚሰጠው በእርሱ እጅ ብቻ መሆኑን እንዲያውቁ ነው:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው:: info
التفاسير: