የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

የገፅ ቁጥር:close

external-link copy
15 : 52

أَفَسِحۡرٌ هَٰذَآ أَمۡ أَنتُمۡ لَا تُبۡصِرُونَ

15. «ይህ (ፊት ትሉን እንደነበራችሁት) ድግምት ነውን? ወይስ እናንተ አታዩምን? info
التفاسير:

external-link copy
16 : 52

ٱصۡلَوۡهَا فَٱصۡبِرُوٓاْ أَوۡ لَا تَصۡبِرُواْ سَوَآءٌ عَلَيۡكُمۡۖ إِنَّمَا تُجۡزَوۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

16. «ግቧት ታገሱም ወይም አትታገሱ በእናንተ ላይ እኩል ነው:: የምትመነዱት ትሰሩት የነበራችሁትን ፍዳ ብቻ ነው» ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 52

إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي جَنَّٰتٖ وَنَعِيمٖ

17. አላህን ፈሪዎቹ በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 52

فَٰكِهِينَ بِمَآ ءَاتَىٰهُمۡ رَبُّهُمۡ وَوَقَىٰهُمۡ رَبُّهُمۡ عَذَابَ ٱلۡجَحِيمِ

18. ጌታቸው በሰጣቸው ጸጋ ተደሳቾች ሆነው በገነት ውስጥ ናቸው:: የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 52

كُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ هَنِيٓـَٔۢا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

19. «ትሰሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ሆናችሁ ብሉ ጠጡም» (ይባላሉ።) info
التفاسير:

external-link copy
20 : 52

مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ سُرُرٖ مَّصۡفُوفَةٖۖ وَزَوَّجۡنَٰهُم بِحُورٍ عِينٖ

20. በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ሆነው በገነት ይኖራሉ:: አይናማዎች በሆኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 52

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَٱتَّبَعَتۡهُمۡ ذُرِّيَّتُهُم بِإِيمَٰنٍ أَلۡحَقۡنَا بِهِمۡ ذُرِّيَّتَهُمۡ وَمَآ أَلَتۡنَٰهُم مِّنۡ عَمَلِهِم مِّن شَيۡءٖۚ كُلُّ ٱمۡرِيِٕۭ بِمَا كَسَبَ رَهِينٞ

21. እነዚያም በአላህ ያመኑና ዝርያቸዉም በእውነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን ከእነርሱ ጋር እናስጠጋቸዋለን:: ከስራዎቻቸዉም ምንንም አናጎድልባቸዉም:: ሰው ሁሉ በሰራው ስራ ተጠያቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 52

وَأَمۡدَدۡنَٰهُم بِفَٰكِهَةٖ وَلَحۡمٖ مِّمَّا يَشۡتَهُونَ

22. ከሚሹትም ሁሉ እሸትንና ስጋን እንጨምርላቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 52

يَتَنَٰزَعُونَ فِيهَا كَأۡسٗا لَّا لَغۡوٞ فِيهَا وَلَا تَأۡثِيمٞ

23. በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ:: በውስጧ ውድቅ ንግግርና መወንጀልም የለም:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 52

۞ وَيَطُوفُ عَلَيۡهِمۡ غِلۡمَانٞ لَّهُمۡ كَأَنَّهُمۡ لُؤۡلُؤٞ مَّكۡنُونٞ

24. ለእነርሱም የሆኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ ለማሰላፍ ይዘዋወራሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 52

وَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ

25. የሚጠያየቁ ሆነዉም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይዞራል:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 52

قَالُوٓاْ إِنَّا كُنَّا قَبۡلُ فِيٓ أَهۡلِنَا مُشۡفِقِينَ

26. ይላሉም: «እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ ከቅጣት ፈሪዎች ነበርን። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 52

فَمَنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡنَا وَوَقَىٰنَا عَذَابَ ٱلسَّمُومِ

27. «አላህ በእኛ ላይ ለገሰ:: የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 52

إِنَّا كُنَّا مِن قَبۡلُ نَدۡعُوهُۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡبَرُّ ٱلرَّحِيمُ

28. «እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበርን:: እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውና» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 52

فَذَكِّرۡ فَمَآ أَنتَ بِنِعۡمَتِ رَبِّكَ بِكَاهِنٖ وَلَا مَجۡنُونٍ

29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ሰዎችን) አስታውስ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም እብድም አይደለህም:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 52

أَمۡ يَقُولُونَ شَاعِرٞ نَّتَرَبَّصُ بِهِۦ رَيۡبَ ٱلۡمَنُونِ

30. «ይልቁንም የሞትን አደጋ በእርሱ የምንጠባበቅበት የሆነ ባለ ቅኔ ነው» ይላሉን? info
التفاسير:

external-link copy
31 : 52

قُلۡ تَرَبَّصُواْ فَإِنِّي مَعَكُم مِّنَ ٱلۡمُتَرَبِّصِينَ

31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ተጠባበቁ እኔም ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው:: info
التفاسير: