የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

አል ሁመዛህ

external-link copy
1 : 104

وَيۡلٞ لِّكُلِّ هُمَزَةٖ لُّمَزَةٍ

1. ለሐሜተኛ፤ ለዘላፊ፤ (ለአሽሟጣጭ ሁሉ) ወዮለት:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 104

ٱلَّذِي جَمَعَ مَالٗا وَعَدَّدَهُۥ

2. ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበዉም) ለሆነ ሁሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 104

يَحۡسَبُ أَنَّ مَالَهُۥٓ أَخۡلَدَهُۥ

3. ገንዘቡ በዚህች ዓለም ዘውታሪ እንደሚያደርገው ያስባል። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 104

كَلَّاۖ لَيُنۢبَذَنَّ فِي ٱلۡحُطَمَةِ

4. በጭራሽ፤ አውዳሚና የምትፈጭ በሆነችው እሳት ውስጥ በእርግጥ ይጣላል። info
التفاسير:

external-link copy
5 : 104

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡحُطَمَةُ

5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምትፈጨዋም ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ? info
التفاسير:

external-link copy
6 : 104

نَارُ ٱللَّهِ ٱلۡمُوقَدَةُ

6. የተቀጣጠለችው የአላህ እሳት ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 104

ٱلَّتِي تَطَّلِعُ عَلَى ٱلۡأَفۡـِٔدَةِ

7. ያቺ በልቦች ላይ እንኳን ሳይቀር የምትዘልቅ የሆነች:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 104

إِنَّهَا عَلَيۡهِم مُّؤۡصَدَةٞ

8. እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋች ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 104

فِي عَمَدٖ مُّمَدَّدَةِۭ

9. በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ የተዘጋች ናት:: info
التفاسير: