የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም - በመሐመድ ሳዲቅ

አል ሙናፊቁን

external-link copy
1 : 63

إِذَا جَآءَكَ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ قَالُواْ نَشۡهَدُ إِنَّكَ لَرَسُولُ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ إِنَّكَ لَرَسُولُهُۥ وَٱللَّهُ يَشۡهَدُ إِنَّ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ لَكَٰذِبُونَ

መናፍቃን በመጡህ ጊዜ «አንተ የአላህ መልክተኛ መኾንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን» ይላሉ፡፡ አላህም አንተ በእርግጥ መልክተኛው መኾንህን ያውቃል፡፡ አላህም መናፍቃን (ከልብ እንመሰክራለን በማለታቸው) ውሸታሞች መኾናቸውን ይመሰክራል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 63

ٱتَّخَذُوٓاْ أَيۡمَٰنَهُمۡ جُنَّةٗ فَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ إِنَّهُمۡ سَآءَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

መሓሎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ፡፡ ከአላህም መንገድ ከለከሉ፡፡ እነርሱ ይሠሩት የነበሩት ነገር ከፋ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 63

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ ءَامَنُواْ ثُمَّ كَفَرُواْ فَطُبِعَ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ فَهُمۡ لَا يَفۡقَهُونَ

ይህ እነርሱ (በምላስ) ያመኑ ከዚያም (በልብ) የካዱ በመኾናቸው ነው፡፡ በልቦቻቸውም ላይ ታተመባቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 63

۞ وَإِذَا رَأَيۡتَهُمۡ تُعۡجِبُكَ أَجۡسَامُهُمۡۖ وَإِن يَقُولُواْ تَسۡمَعۡ لِقَوۡلِهِمۡۖ كَأَنَّهُمۡ خُشُبٞ مُّسَنَّدَةٞۖ يَحۡسَبُونَ كُلَّ صَيۡحَةٍ عَلَيۡهِمۡۚ هُمُ ٱلۡعَدُوُّ فَٱحۡذَرۡهُمۡۚ قَٰتَلَهُمُ ٱللَّهُۖ أَنَّىٰ يُؤۡفَكُونَ

ባየሃቸውም ጊዜ አካሎቻቸው (ግዙፍነታቸው) ያስደንቁሃል፡፡ ቢናገሩም ለንግግራቸው ታዳምጣለህ፤ (ከዕውቀት ባዶ በመኾን)፡፡ እነርሱ ልክ በግድግዳ የተጠጉ ግንዶችን ይመስላሉ፡፡ ጩኸትን ሁሉ በእነርሱ ላይ ነው ብለው ያስባሉ፡፡ እነርሱ ጠላቶች ናቸውና ተጠንቀቃቸው፡፡ አላህ ይጋደላቸው፤ (ከእምነት) እንዴት ይመለሳሉ! info
التفاسير: