የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም - በመሐመድ ሳዲቅ

የገፅ ቁጥር:close

external-link copy
62 : 18

فَلَمَّا جَاوَزَا قَالَ لِفَتَىٰهُ ءَاتِنَا غَدَآءَنَا لَقَدۡ لَقِينَا مِن سَفَرِنَا هَٰذَا نَصَبٗا

ባለፉም ጊዜ ለወጣቱ «ምሳችንን ስጠን፡፡ ከዚህ ጉዟችን በእርግጥ ድካምን አግኝተናልና» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
63 : 18

قَالَ أَرَءَيۡتَ إِذۡ أَوَيۡنَآ إِلَى ٱلصَّخۡرَةِ فَإِنِّي نَسِيتُ ٱلۡحُوتَ وَمَآ أَنسَىٰنِيهُ إِلَّا ٱلشَّيۡطَٰنُ أَنۡ أَذۡكُرَهُۥۚ وَٱتَّخَذَ سَبِيلَهُۥ فِي ٱلۡبَحۡرِ عَجَبٗا

«አየህን ወደ ቋጥኝዋ በተጠጋን ጊዜ እኔ ዐሣውን ረሳሁ፡፡ ማስታወሱንም ሰይጣን እንጂ ሌላ አላስረሳኝም፡፡ በባሕሩም ውስጥ መንገዱን አስደናቂ (መንገድ) አድርጎ ያዘ» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
64 : 18

قَالَ ذَٰلِكَ مَا كُنَّا نَبۡغِۚ فَٱرۡتَدَّا عَلَىٰٓ ءَاثَارِهِمَا قَصَصٗا

(ሙሳም) ይህ እንፈልገው የነበርነው ነው አለው፡፡ በፈለጎቻቸውም ላይ እየተከተሉ ተመለሱ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
65 : 18

فَوَجَدَا عَبۡدٗا مِّنۡ عِبَادِنَآ ءَاتَيۡنَٰهُ رَحۡمَةٗ مِّنۡ عِندِنَا وَعَلَّمۡنَٰهُ مِن لَّدُنَّا عِلۡمٗا

ከባሮቻችንም ከእኛ ዘንድ ችሮታን የሰጠነውን ከእኛም ዘንድ ዕውቀትን ያስተማርነውን አንድን ባሪያ (ኸደርን) አገኙ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
66 : 18

قَالَ لَهُۥ مُوسَىٰ هَلۡ أَتَّبِعُكَ عَلَىٰٓ أَن تُعَلِّمَنِ مِمَّا عُلِّمۡتَ رُشۡدٗا

ሙሳ ለእርሱ «ከተማርከው ነገር ቀጥተኛን (ዕውቀት) ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህን?» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
67 : 18

قَالَ إِنَّكَ لَن تَسۡتَطِيعَ مَعِيَ صَبۡرٗا

(ባሪያውም) አለ «አንተ ከእኔ ጋር መታገስን በጭራሽ አትችልም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
68 : 18

وَكَيۡفَ تَصۡبِرُ عَلَىٰ مَا لَمۡ تُحِطۡ بِهِۦ خُبۡرٗا

«በዕውቀትም በእርሱ ባላዳረስከው ነገር ላይ እንዴት ትታገሳለህ?» info
التفاسير:

external-link copy
69 : 18

قَالَ سَتَجِدُنِيٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ صَابِرٗا وَلَآ أَعۡصِي لَكَ أَمۡرٗا

(ሙሳ) «አላህ የሻ እንደ ኾነ ታጋሽና ላንተ ትዕዛዝን የማልጥስ ኾኜ ታገኘኛለህ» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
70 : 18

قَالَ فَإِنِ ٱتَّبَعۡتَنِي فَلَا تَسۡـَٔلۡنِي عَن شَيۡءٍ حَتَّىٰٓ أُحۡدِثَ لَكَ مِنۡهُ ذِكۡرٗا

«ብትከተለኝም ለአንተ ከእርሱ ማውሳትን እስከምጀምርልህ ድረስ ከምንም ነገር አትጠይቀኝ» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
71 : 18

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَا رَكِبَا فِي ٱلسَّفِينَةِ خَرَقَهَاۖ قَالَ أَخَرَقۡتَهَا لِتُغۡرِقَ أَهۡلَهَا لَقَدۡ جِئۡتَ شَيۡـًٔا إِمۡرٗا

ኼዱም፡፡ በመርከቢቱም በተሳፈሩ ጊዜ ቀደዳት፡፡ «ባለ ቤቶቿን ልታሰጥም ቀደድካትን ትልቅ ነገርን በእርግጥ ሠራህ» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
72 : 18

قَالَ أَلَمۡ أَقُلۡ إِنَّكَ لَن تَسۡتَطِيعَ مَعِيَ صَبۡرٗا

«አንተ ከኔ ጋር ትእግሥትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩምን?» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
73 : 18

قَالَ لَا تُؤَاخِذۡنِي بِمَا نَسِيتُ وَلَا تُرۡهِقۡنِي مِنۡ أَمۡرِي عُسۡرٗا

«በረሳሁት ነገር አትያዘኝ፡፡ ከነገሬም ችግርን አታሸክመኝ» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
74 : 18

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَا لَقِيَا غُلَٰمٗا فَقَتَلَهُۥ قَالَ أَقَتَلۡتَ نَفۡسٗا زَكِيَّةَۢ بِغَيۡرِ نَفۡسٖ لَّقَدۡ جِئۡتَ شَيۡـٔٗا نُّكۡرٗا

(ወርደው) ተጓዙም፡፡ ወጣትንም ልጅ ባገኙና በገደለው ጊዜ ፤«ያለ ነፍስ (መግደል) ንጹሕን ነፍስ ገደልክን? በእርግጥ መጥፎን ነገር ሠራህ» አለው፡፡ info
التفاسير: