Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси

Бет рақами:close

external-link copy
23 : 43

وَكَذَٰلِكَ مَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ فِي قَرۡيَةٖ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتۡرَفُوهَآ إِنَّا وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا عَلَىٰٓ أُمَّةٖ وَإِنَّا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم مُّقۡتَدُونَ

23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነገሩ ልክ እንደዚህ ነው:: ከበፊትም በማንኛይቱም ከተማ ውስጥ አስፈራሪን አላክንም ቅምጥሎቿ «እኛ አባቶቻችንን (በዚሁ) ሃይማኖት ላይ አገኘን:: እኛም ፈለጎቻቸውን ተከታዩች ነን» ያሉ ቢሆኑ እንጂ:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 43

۞ قَٰلَ أَوَلَوۡ جِئۡتُكُم بِأَهۡدَىٰ مِمَّا وَجَدتُّمۡ عَلَيۡهِ ءَابَآءَكُمۡۖ قَالُوٓاْ إِنَّا بِمَآ أُرۡسِلۡتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ

24. አስፈራሪው «አባቶቻችሁን በእርሱ ላይ ካገኛችሁበት ይበልጥ ቀጥተኛው ሃይማኖት ባመጣላችሁም?» ቢላቸው «እኛ በተላካችሁበት ነገር (ሀይማኖት) ከሓዲያን ነን» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 43

فَٱنتَقَمۡنَا مِنۡهُمۡۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ

25. ከእነርሱም ተበቀልን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያስተባባዮች መጨረሻ እንዴት እንደነበር ተመልከት:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 43

وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِيمُ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦٓ إِنَّنِي بَرَآءٞ مِّمَّا تَعۡبُدُونَ

26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂምም ለአባቱና ለህዝቦቹ «እኔ ከምትገዙት ጣኦታት ሁሉ ንጹህ ነኝ:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 43

إِلَّا ٱلَّذِي فَطَرَنِي فَإِنَّهُۥ سَيَهۡدِينِ

27. «ከዚያ ከፈጠረኝ በስተቀር ማንንም አልገዛም:: አላህንማ በእርግጥ ይመራኛልና ብቻውን አመልከዋለሁ» ባለ ጊዜ የነበረውን አስታውስ:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 43

وَجَعَلَهَا كَلِمَةَۢ بَاقِيَةٗ فِي عَقِبِهِۦ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ

28. በዝርዮቹም ውስጥ ወደ አላህ ይመለሱ ዘንድ (በአንድ አምላክ) ማመንን ቀሪ ቃል አደረጋት:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 43

بَلۡ مَتَّعۡتُ هَٰٓؤُلَآءِ وَءَابَآءَهُمۡ حَتَّىٰ جَآءَهُمُ ٱلۡحَقُّ وَرَسُولٞ مُّبِينٞ

29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁን እነዚህን ቁረይሾችንም አባቶቻቸውንም ቁርኣንንና ገላጭ መልዕክተኛ እስካመጣላቸው ድረስ አጣቀምኳቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 43

وَلَمَّا جَآءَهُمُ ٱلۡحَقُّ قَالُواْ هَٰذَا سِحۡرٞ وَإِنَّا بِهِۦ كَٰفِرُونَ

30. እውነት በመጣላቸው ጊዜም «ይህ ያመጣሀው ድግምት ነው። እኛም በእርሱ ከሓዲያን ነን።» አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 43

وَقَالُواْ لَوۡلَا نُزِّلَ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانُ عَلَىٰ رَجُلٖ مِّنَ ٱلۡقَرۡيَتَيۡنِ عَظِيمٍ

31. ይህም «ቁርኣን በሁለቱ ከተሞች በአንዱ በሚኖር ታላቅ ሰው ላይ አይወርድም ኖሯልን?» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 43

أَهُمۡ يَقۡسِمُونَ رَحۡمَتَ رَبِّكَۚ نَحۡنُ قَسَمۡنَا بَيۡنَهُم مَّعِيشَتَهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَرَفَعۡنَا بَعۡضَهُمۡ فَوۡقَ بَعۡضٖ دَرَجَٰتٖ لِّيَتَّخِذَ بَعۡضُهُم بَعۡضٗا سُخۡرِيّٗاۗ وَرَحۡمَتُ رَبِّكَ خَيۡرٞ مِّمَّا يَجۡمَعُونَ

32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ የጌታህን ስጦታ ያከፋፍላሉን? እኛ በቅርቢቱ ሕይወት እንኳን ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል:: ከፊላቸዉም ከፊሉን አገልጋይ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ (በሀብት) አበለጥን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህም ጸጋ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
33 : 43

وَلَوۡلَآ أَن يَكُونَ ٱلنَّاسُ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ لَّجَعَلۡنَا لِمَن يَكۡفُرُ بِٱلرَّحۡمَٰنِ لِبُيُوتِهِمۡ سُقُفٗا مِّن فِضَّةٖ وَمَعَارِجَ عَلَيۡهَا يَظۡهَرُونَ

33. ሰዎችም (በክህደት) ላይ አንድ ህዝብ የሚሆኑ ባልነበሩ ኖሮ በአል-ረህማን ለሚክዱ ሰዎች ሁሉ (በዚህች ዓለም) ለቤቶቻቸው የብር ጣራዎች፤ የሚወጣጡባቸውም የብር መሰላሎች፤ ባደረግንላቸው ነበር። info
التفاسير: