Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси

Бет рақами:close

external-link copy
25 : 37

مَا لَكُمۡ لَا تَنَاصَرُونَ

25. ለነርሱም «ምን ሆናችሁ ነው የማትረዳዱት?» ይባላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
26 : 37

بَلۡ هُمُ ٱلۡيَوۡمَ مُسۡتَسۡلِمُونَ

26. በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ማምለጫ የሌላቸው ወራዳዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 37

وَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ

27. እርስ በራሳቸውም የሚወቃቀሱም ሆነው ይመጣሉ። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 37

قَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَأۡتُونَنَا عَنِ ٱلۡيَمِينِ

28. (ተከታዮቹ ለአስከታዮቻቸው) «እናንተ በጉልበት ትመጡብን ነበር» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 37

قَالُواْ بَل لَّمۡ تَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ

29. (አስከታዮቹም) ይላሉ፡- «አይደለም ፈጽሞ አማኞች አልነበራችሁም። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 37

وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيۡكُم مِّن سُلۡطَٰنِۭۖ بَلۡ كُنتُمۡ قَوۡمٗا طَٰغِينَ

30. «ለእኛም በናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም። በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ህዝቦች ነበራችሁና ነው እንጂ። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 37

فَحَقَّ عَلَيۡنَا قَوۡلُ رَبِّنَآۖ إِنَّا لَذَآئِقُونَ

31. «በእኛም ላይ የጌታችን ቃል የተረጋገጠብንና ሁላችንም ቅጣቱን ቀማሽ ነን። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 37

فَأَغۡوَيۡنَٰكُمۡ إِنَّا كُنَّا غَٰوِينَ

32. «እኛ ጠማሞች ስለ ነበርን ወደ ጥመት ጠራናችሁም።» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 37

فَإِنَّهُمۡ يَوۡمَئِذٖ فِي ٱلۡعَذَابِ مُشۡتَرِكُونَ

33. ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ተጋሪዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 37

إِنَّا كَذَٰلِكَ نَفۡعَلُ بِٱلۡمُجۡرِمِينَ

34. እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሰራለን። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 37

إِنَّهُمۡ كَانُوٓاْ إِذَا قِيلَ لَهُمۡ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ يَسۡتَكۡبِرُونَ

35. እነርሱ «ከአላህ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም» በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 37

وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوٓاْ ءَالِهَتِنَا لِشَاعِرٖ مَّجۡنُونِۭ

36. «እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን እንዴ?» ይሉ ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 37

بَلۡ جَآءَ بِٱلۡحَقِّ وَصَدَّقَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

37. አይደለም እውነቱን ሃይማኖት አመጣ፤ መልዕክተኞቹንም እውነተኝነታቸውን አረጋገጠ። info
التفاسير:

external-link copy
38 : 37

إِنَّكُمۡ لَذَآئِقُواْ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَلِيمِ

38. እናንተ አሳማሚውን ቅጣት እርግጥ ቀማሾች ናችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 37

وَمَا تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

39. ትሰሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 37

إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ

40. ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ቅጣትን አይቀምሱም:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 37

أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ رِزۡقٞ مَّعۡلُومٞ

41. እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አለላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 37

فَوَٰكِهُ وَهُم مُّكۡرَمُونَ

42. ፍራፋሬዎች (አሉላቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 37

فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ

43. በድሎት ገነቶች ውስጥ:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 37

عَلَىٰ سُرُرٖ مُّتَقَٰبِلِينَ

44. ፊት ለፊት የሚተያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ ይንፈላሰሳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 37

يُطَافُ عَلَيۡهِم بِكَأۡسٖ مِّن مَّعِينِۭ

45. ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዙ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 37

بَيۡضَآءَ لَذَّةٖ لِّلشَّٰرِبِينَ

46. ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከሆነች፤ info
التفاسير:

external-link copy
47 : 37

لَا فِيهَا غَوۡلٞ وَلَا هُمۡ عَنۡهَا يُنزَفُونَ

47. በእርሷ ውስጥም የራስ ምታት የለባትም:: እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 37

وَعِندَهُمۡ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ عِينٞ

48. እነርሱ ዘንድ ዓይናቸውን በባሎቻቸው ላይ ብቻ አሳጣሪዎች የሆኑ ዓይናማ ሴቶች አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 37

كَأَنَّهُنَّ بَيۡضٞ مَّكۡنُونٞ

49. እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) እንቁላል ይመስላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 37

فَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ

50. የሚጠያያቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 37

قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٞ

51. ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ (እንዲህ) ይላል: «እኔ ጓደኛ ነበረኝ። info
التفاسير: