Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси

ያሲን

external-link copy
1 : 36

يسٓ

1. ያሲን:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 36

وَٱلۡقُرۡءَانِ ٱلۡحَكِيمِ

2-ጥበብ በተሞላበት ቁርኣን እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 36

إِنَّكَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቹ መካከል አንዱ ነህ። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 36

عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

4. አንተ በእርግጥ በቀጥታው መንገድ ላይ ነህ :: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 36

تَنزِيلَ ٱلۡعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ

5.ቁርኣን አሸናፊውና አዛኙ ከሆነው አምላክ ከአላህ ተወረደ:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 36

لِتُنذِرَ قَوۡمٗا مَّآ أُنذِرَ ءَابَآؤُهُمۡ فَهُمۡ غَٰفِلُونَ

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አባቶቻቸው ያልተስፈራሩትን ህዝቦች ልታስጠነቅቅበት ቁርኣን ተወረደ። እነርሱ ዘንጊዎች ናቸውና። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 36

لَقَدۡ حَقَّ ٱلۡقَوۡلُ عَلَىٰٓ أَكۡثَرِهِمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ

7. በአብዛኞቻቸቸው ላይ ቃሉ በእውነት ተረጋገጠ:: ስለዚህ እነርሱ አያምኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 36

إِنَّا جَعَلۡنَا فِيٓ أَعۡنَٰقِهِمۡ أَغۡلَٰلٗا فَهِيَ إِلَى ٱلۡأَذۡقَانِ فَهُم مُّقۡمَحُونَ

8. እኛ በአንገቶቻቸው ላይ እንዛዝላዎችን አደረግን። (እንዛዝላይቱም) ወደ አገጮቻቸው ደራሽ ናት። እናም ከዚያም እነርሱ ራሶቻቸውን ያንጋጠጡ ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 36

وَجَعَلۡنَا مِنۢ بَيۡنِ أَيۡدِيهِمۡ سَدّٗا وَمِنۡ خَلۡفِهِمۡ سَدّٗا فَأَغۡشَيۡنَٰهُمۡ فَهُمۡ لَا يُبۡصِرُونَ

9. ከበስተፊታቸዉም ግርዶን ከበስተኋላቸዉም ግርዶን አደረግንና ሸፈንናቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያዩም:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 36

وَسَوَآءٌ عَلَيۡهِمۡ ءَأَنذَرۡتَهُمۡ أَمۡ لَمۡ تُنذِرۡهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ

10. ብታስጠነቅቃቸዉም ባታስጠነቅቃቸዉም ለእነርሱ ሁሉም እኩል ነው:: (ምንም ለውጥ አያመጣም) አያምኑምና:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 36

إِنَّمَا تُنذِرُ مَنِ ٱتَّبَعَ ٱلذِّكۡرَ وَخَشِيَ ٱلرَّحۡمَٰنَ بِٱلۡغَيۡبِۖ فَبَشِّرۡهُ بِمَغۡفِرَةٖ وَأَجۡرٖ كَرِيمٍ

11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው ግሳጼን የተከተለንና አር-ረህማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው:: እናም በምህረትና በመልካም ምንዳ አብስረው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 36

إِنَّا نَحۡنُ نُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَنَكۡتُبُ مَا قَدَّمُواْ وَءَاثَٰرَهُمۡۚ وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ فِيٓ إِمَامٖ مُّبِينٖ

12. እኛ ሙታንን በእርግጥ ህያው እናደርጋለን:: ያስቀደሙትንም ስራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን:: ሁሉን ነገርም ገላጭና መሪ በሆነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው:: info
التفاسير: