Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси

Бет рақами:close

external-link copy
21 : 24

۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّبِعُواْ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيۡطَٰنِۚ وَمَن يَتَّبِعۡ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيۡطَٰنِ فَإِنَّهُۥ يَأۡمُرُ بِٱلۡفَحۡشَآءِ وَٱلۡمُنكَرِۚ وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ وَرَحۡمَتُهُۥ مَا زَكَىٰ مِنكُم مِّنۡ أَحَدٍ أَبَدٗا وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يُزَكِّي مَن يَشَآءُۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٞ

21. እናንተ ያመናችሁሆይ! የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ:: የሰይጣንን እርምጃዎች የሚከተል ሰው ሁሉ ኃጢአትን ተሸከመ:: እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዛልና፤ በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከናንተ አንድም ፈጽሞ (ከወንጀል) ባልጠራ ነበር:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠራል:: አላህ ሁሉንም ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 24

وَلَا يَأۡتَلِ أُوْلُواْ ٱلۡفَضۡلِ مِنكُمۡ وَٱلسَّعَةِ أَن يُؤۡتُوٓاْ أُوْلِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينَ وَٱلۡمُهَٰجِرِينَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۖ وَلۡيَعۡفُواْ وَلۡيَصۡفَحُوٓاْۗ أَلَا تُحِبُّونَ أَن يَغۡفِرَ ٱللَّهُ لَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٌ

22. ከናንተም መካከል የችሮታና የክብረት ባለቤቶች የሆኑት ክፍሎች ለቅርብ ዘመዶችና ለድሆችና በአላህም መንገድ ለተሰደዱ ሰዎች ምንንም ነገር ላይሰጡ አይማሉ:: ይቅርታም ያድርጉ:: ጥፋተኞቹንም ይለፉ። አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን ? አላህ መሓሪና አዛኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 24

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَرۡمُونَ ٱلۡمُحۡصَنَٰتِ ٱلۡغَٰفِلَٰتِ ٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ لُعِنُواْ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ

23. እነዚያ ጥብቆቹንና ከዝሙት ዘንጊዎቹን ምዕምናት የሚሰድቡ ሰዎች ሁሉ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተረገሙ:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 24

يَوۡمَ تَشۡهَدُ عَلَيۡهِمۡ أَلۡسِنَتُهُمۡ وَأَيۡدِيهِمۡ وَأَرۡجُلُهُم بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

24. በእነርሱ ላይ ምላሶቻቸው እጆቻቸውና እግሮቻቸው ይሰሩት በነበሩት ነገር ሁሉ በሚመሰክሩባቸው ቀን ከባድ ቅጣት አለላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 24

يَوۡمَئِذٖ يُوَفِّيهِمُ ٱللَّهُ دِينَهُمُ ٱلۡحَقَّ وَيَعۡلَمُونَ أَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡحَقُّ ٱلۡمُبِينُ

25. በዚያም ቀን አላህ ተገቢ ዋጋቸውን ይሞላላቸዋል:: አላህም ፍፁም ግልፅ እውነት መሆኑን ያውቃሉ። info
التفاسير:

external-link copy
26 : 24

ٱلۡخَبِيثَٰتُ لِلۡخَبِيثِينَ وَٱلۡخَبِيثُونَ لِلۡخَبِيثَٰتِۖ وَٱلطَّيِّبَٰتُ لِلطَّيِّبِينَ وَٱلطَّيِّبُونَ لِلطَّيِّبَٰتِۚ أُوْلَٰٓئِكَ مُبَرَّءُونَ مِمَّا يَقُولُونَۖ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ

26. መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎቹ ወንዶች፤መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች ብቻ የተገቡ ናቸው:: ጥሩዎቹ ሴቶችም ለጥሩዎቹ ወንዶች፤ ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች ብቻ የሚገቡ ናቸው:: እነዚህ ጥሩዎቹም መጥፎዎቹ ከሚሉት ነገር ንጹህ የተደረጉ ናቸው:: ለእነርሱ በገነት ምህረትና መልካም ሲሳይ አለላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 24

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَدۡخُلُواْ بُيُوتًا غَيۡرَ بُيُوتِكُمۡ حَتَّىٰ تَسۡتَأۡنِسُواْ وَتُسَلِّمُواْ عَلَىٰٓ أَهۡلِهَاۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ

27. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቹ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ በሌላ ሰዎች ቤቶች አትግቡ:: ይህ ጉዳይ ለእናንተም መልካም ነው:: እናንተ ትገነዘቡ ዘንድ በዚህ ታዘዛችሁ:: info
التفاسير: