Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси

Бет рақами:close

external-link copy
17 : 2

مَثَلُهُمۡ كَمَثَلِ ٱلَّذِي ٱسۡتَوۡقَدَ نَارٗا فَلَمَّآ أَضَآءَتۡ مَا حَوۡلَهُۥ ذَهَبَ ٱللَّهُ بِنُورِهِمۡ وَتَرَكَهُمۡ فِي ظُلُمَٰتٖ لَّا يُبۡصِرُونَ

17. የእነርሱ ንፍቅና ምሳሌ ልክ እንደዚያ እሳትን እንዳነደደና ከዚያ በዙሪያው ያለውን ሁሉ ባበራችለት ጊዜ አላህ ብርሃናቸውን እንደወሰደባቸው እና በጨለማዎች ውስጥ የማያዩ ሆነው እንደተዋቸው ብጤ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 2

صُمُّۢ بُكۡمٌ عُمۡيٞ فَهُمۡ لَا يَرۡجِعُونَ

18. እነርሱ (ሓቅን የማይሰሙ) ደንቆሮዎች፤ (ሓቅን የማይናገሩ) ዲዳዎች፤ (ሓቅን የማያዩ) እውሮች ናቸው:: ስለዚህ እነርሱ (ከስህተት) አይመለሱም። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 2

أَوۡ كَصَيِّبٖ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فِيهِ ظُلُمَٰتٞ وَرَعۡدٞ وَبَرۡقٞ يَجۡعَلُونَ أَصَٰبِعَهُمۡ فِيٓ ءَاذَانِهِم مِّنَ ٱلصَّوَٰعِقِ حَذَرَ ٱلۡمَوۡتِۚ وَٱللَّهُ مُحِيطُۢ بِٱلۡكَٰفِرِينَ

19. ወይም (ምሳሌያቸው) ከሰማይ እንደወረደ ዝናብ (ባለቤቶች) ነው:: በእርሱ (በደመናው) ውስጥ ጨለማዎች፤ ነጎድጓድና ብልጭታ ያሉበት ሲሆን ከመብረቆቹ ሊመጣ ከሚችል ጥቃት ሞትን በመፍራት ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ እንደሚያደርጉ ሰዎች ቢጤ ነው:: አላህ ከሓዲያንን (በእውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 2

يَكَادُ ٱلۡبَرۡقُ يَخۡطَفُ أَبۡصَٰرَهُمۡۖ كُلَّمَآ أَضَآءَ لَهُم مَّشَوۡاْ فِيهِ وَإِذَآ أَظۡلَمَ عَلَيۡهِمۡ قَامُواْۚ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَذَهَبَ بِسَمۡعِهِمۡ وَأَبۡصَٰرِهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

20 ብልጭታው ዓይኖቻቸውን ሊነጥቅ ይቀርባል:: ለእነርሱ ባበራላቸው ቁጥር በውስጡ ይሄዳሉ:: በእነርሱም ላይ ባጨለመባቸው ጊዜ ደግሞ ይቆማሉ:: አላህ በፈለገ ኖሮ መስሚያዎቻቸውንና ማያዎቻቸውን ይወስድባቸው ነበር:: አላህ በነገሮች ሁሉ ላይ ቻይ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 2

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱعۡبُدُواْ رَبَّكُمُ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ

21. እናንተ ሰዎች ሆይ! ያን እናንተንና እነዚያን ከናንተ በፊት የነበሩትን የፈጠረውን ጌታችሁን (አላህን) በብቸኝነት ተገዙት:: ቅጣትን ልትጠነቀቁ ዘንድ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 2

ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ فِرَٰشٗا وَٱلسَّمَآءَ بِنَآءٗ وَأَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجَ بِهِۦ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ رِزۡقٗا لَّكُمۡۖ فَلَا تَجۡعَلُواْ لِلَّهِ أَندَادٗا وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

22. እርሱ (አላህ) ያ ለእናንተ ምድርን ምንጣፍ፤ ሰማይን ጣራ ያደረገ ጌታ ነው::ከሰማይ ዳመና ውሃን ያወረደና ከዚያ በውሃው ከፍሬዎች ሁሉ ለእናንተ ሲሳይን ያወጣላችሁ ነው:: እናም (ብቸኛ ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትሆኑ ለአላህ (በአምልኮ) አጋሮችን አታድርጉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 2

وَإِن كُنتُمۡ فِي رَيۡبٖ مِّمَّا نَزَّلۡنَا عَلَىٰ عَبۡدِنَا فَأۡتُواْ بِسُورَةٖ مِّن مِّثۡلِهِۦ وَٱدۡعُواْ شُهَدَآءَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

23. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) በአገልጋያችን (በሙሐመድ) ላይ ባወረድነው (ቁርኣን) በመጠራጠር ላይ ከሆናችሁም ከእርሱ ጋር ሊወዳደር የሚችል አንድ ምዕራፍ እንኳን እስቲ አምጡ:: እውነተኞች እንደሆናችሁ ከአላህ ሌላ ረዳቶቻችሁንም ሁሉ ጥሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 2

فَإِن لَّمۡ تَفۡعَلُواْ وَلَن تَفۡعَلُواْ فَٱتَّقُواْ ٱلنَّارَ ٱلَّتِي وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلۡحِجَارَةُۖ أُعِدَّتۡ لِلۡكَٰفِرِينَ

24. (ይህንን) ባትሰሩ ግን በርግጥም አትሰሩትምና (አትፈጽሙትምና) ከዚያች መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች ከሆነው ከገሀነም እሳት ራሳችሁን ጠብቁ:: ለከሓዲያን ሁሉ ተደግሳለችና፡፡ info
التفاسير: