Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Муҳаммад Содиқ

Бет рақами:close

external-link copy
41 : 39

إِنَّآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ لِلنَّاسِ بِٱلۡحَقِّۖ فَمَنِ ٱهۡتَدَىٰ فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيۡهَاۖ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡهِم بِوَكِيلٍ

እኛ መጽሐፉን ባንተ ላይ ለሰዎች (ጥቅም) በእውነት አወረድነው፡፡ የተመራም ሰው ለነፍሱ ነው፡፡ የጠመመም ሰው የሚጠምመው (ጉዳቱ) በእርሷ ላይ ነው፡፡ አንተም (ታስገድዳቸው ዘንድ) በእነርሱ ላይ ጠባቂ አይደለህም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
42 : 39

ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلۡأَنفُسَ حِينَ مَوۡتِهَا وَٱلَّتِي لَمۡ تَمُتۡ فِي مَنَامِهَاۖ فَيُمۡسِكُ ٱلَّتِي قَضَىٰ عَلَيۡهَا ٱلۡمَوۡتَ وَيُرۡسِلُ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمًّىۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ

አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፡፡ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ (ይወስዳታል)፡፡ ታዲያ ያችን ሞትን የፈረደባትን ይይዛታል፡፡ ሌላይቱንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ይለቅቃታል፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ምልክቶች አልሉበት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
43 : 39

أَمِ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ شُفَعَآءَۚ قُلۡ أَوَلَوۡ كَانُواْ لَا يَمۡلِكُونَ شَيۡـٔٗا وَلَا يَعۡقِلُونَ

ይልቁንም ከአላህ ሌላ አማላጆችን ያዙ፡፡ «እነርሱ ምንንም የማይችሉና የማያውቁ ቢኾኑም?» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
44 : 39

قُل لِّلَّهِ ٱلشَّفَٰعَةُ جَمِيعٗاۖ لَّهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ ثُمَّ إِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ

«ምልጃ መላውም የአላህ ብቻ ነው፡፡ የሰማያትና የምድር ሥልጣን የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ወደእርሱ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
45 : 39

وَإِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَحۡدَهُ ٱشۡمَأَزَّتۡ قُلُوبُ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِۖ وَإِذَا ذُكِرَ ٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦٓ إِذَا هُمۡ يَسۡتَبۡشِرُونَ

አላህም ብቻውን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይሸማቀቃሉ፤ (ይደነብራሉ)፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የኾኑት (ጣዖታት) በተወሱ ጊዜ እነርሱ ወዲያውኑ ይደሰታሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
46 : 39

قُلِ ٱللَّهُمَّ فَاطِرَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ عَٰلِمَ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ أَنتَ تَحۡكُمُ بَيۡنَ عِبَادِكَ فِي مَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ

«ሰማያትንና ምድርን የፈጠርክ ሩቁንም ቅርቡንም ዐዋቂ የኾንክ አላህ ሆይ! አንተ በባሮችህ መካከል በእዚያ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ትፈርዳለህ» በል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
47 : 39

وَلَوۡ أَنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ مَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا وَمِثۡلَهُۥ مَعَهُۥ لَٱفۡتَدَوۡاْ بِهِۦ مِن سُوٓءِ ٱلۡعَذَابِ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ وَبَدَا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مَا لَمۡ يَكُونُواْ يَحۡتَسِبُونَ

ለእነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላውም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተበዡበት ነበር፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ዘንድ ያስቡት ያልነበሩት ሁሉ ይገለጽላቸዋል፡፡ info
التفاسير: