Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Муҳаммад Содиқ

Бет рақами:close

external-link copy
23 : 12

وَرَٰوَدَتۡهُ ٱلَّتِي هُوَ فِي بَيۡتِهَا عَن نَّفۡسِهِۦ وَغَلَّقَتِ ٱلۡأَبۡوَٰبَ وَقَالَتۡ هَيۡتَ لَكَۚ قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِۖ إِنَّهُۥ رَبِّيٓ أَحۡسَنَ مَثۡوَايَۖ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ

ያቺም እርሱ በቤቷ የነበረባት (ሴት) ከነፍሱ አባበለችው፡፡ ደጃፎቹንም ዘጋች፤ «ላንተ ተዘጋጅቼልሃለሁና ቶሎ ናም» አለችው፡፡ «በአላህ እጠበቃለሁ እርሱ (የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና፤ (አልከዳውም)፡፡ እነሆ! በደለኞች አይድኑም» አላት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 12

وَلَقَدۡ هَمَّتۡ بِهِۦۖ وَهَمَّ بِهَا لَوۡلَآ أَن رَّءَا بُرۡهَٰنَ رَبِّهِۦۚ كَذَٰلِكَ لِنَصۡرِفَ عَنۡهُ ٱلسُّوٓءَ وَٱلۡفَحۡشَآءَۚ إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُخۡلَصِينَ

በእርሱም በእርግጥ አሰበች፡፡ በእርሷም አሰበ፤ የጌታውን ማስረጃ ባላየ ኖሮ (የተፈጥሮ ፍላጎቱን ባረካ ነበር፤)፡፡ እንደዚሁ መጥፎ ነገርንና ኀጢአትን ከእርሱ ላይ ልንመልስለት (አስረጃችንን አሳየነው)፡፡ እርሱ ከተመረጡት ባሮቻችን ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
25 : 12

وَٱسۡتَبَقَا ٱلۡبَابَ وَقَدَّتۡ قَمِيصَهُۥ مِن دُبُرٖ وَأَلۡفَيَا سَيِّدَهَا لَدَا ٱلۡبَابِۚ قَالَتۡ مَا جَزَآءُ مَنۡ أَرَادَ بِأَهۡلِكَ سُوٓءًا إِلَّآ أَن يُسۡجَنَ أَوۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

በሩንም ተሽቀዳደሙ ቀሚሱንም ከበስተኋላው ቀደደችው፡፡ ጌታዋንም (ባለቤቷን) እበሩ አጠገብ አገኙት፡፡ (ቀደም ብላ) «በባለቤትህ መጥፎን ያሰበ ሰው ቅጣቱ መታሰር ወይም አሳማሚ ስቃይ እንጂ ሌላ አይደለም» አለችው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 12

قَالَ هِيَ رَٰوَدَتۡنِي عَن نَّفۡسِيۚ وَشَهِدَ شَاهِدٞ مِّنۡ أَهۡلِهَآ إِن كَانَ قَمِيصُهُۥ قُدَّ مِن قُبُلٖ فَصَدَقَتۡ وَهُوَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ

(ዩሱፍም) «እርሷ ከነፍሴ አባበለችኝ» አለ፡፡ ከቤተሰቦቿም መስካሪ (እንዲህ ሲል) መሰከረ፡፡ «ቀሚሱ ከበስተፊት ተቀድዶ እንደሆነ እውነት ተናገረች፡፡ እርሱም ከውሸታሞቹ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 12

وَإِن كَانَ قَمِيصُهُۥ قُدَّ مِن دُبُرٖ فَكَذَبَتۡ وَهُوَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

«ቀሚሱም ከበስተኋላ ተቀድዶ እንደሆነ ዋሸች፡፡ እርሱም ከእውነተኞቹ ነው፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
28 : 12

فَلَمَّا رَءَا قَمِيصَهُۥ قُدَّ مِن دُبُرٖ قَالَ إِنَّهُۥ مِن كَيۡدِكُنَّۖ إِنَّ كَيۡدَكُنَّ عَظِيمٞ

ቀሚሱንም ከበስተኋላ ተቀድዶ ባየ ጊዜ «እርሱ (የተናገርሺው) ከተንኮላችሁ ነው (ሴቶች) ተንኮላችሁ በእርግጥ ብርቱ ነውና» አላት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 12

يُوسُفُ أَعۡرِضۡ عَنۡ هَٰذَاۚ وَٱسۡتَغۡفِرِي لِذَنۢبِكِۖ إِنَّكِ كُنتِ مِنَ ٱلۡخَاطِـِٔينَ

«ዩሱፍ ሆይ! ከዚህ (ወሬ) ተከልከል፡፡ ለኃጢአትሽም ማርታን ለምኚ፡፡ አንቺ ከስህተተኞቹ ሆነሻልና» (አለ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 12

۞ وَقَالَ نِسۡوَةٞ فِي ٱلۡمَدِينَةِ ٱمۡرَأَتُ ٱلۡعَزِيزِ تُرَٰوِدُ فَتَىٰهَا عَن نَّفۡسِهِۦۖ قَدۡ شَغَفَهَا حُبًّاۖ إِنَّا لَنَرَىٰهَا فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

በከተማው ያሉ ሴቶችም «የዐዚዝ ሚስት ብላቴናዋን ከነፍሱ ታባብለዋለች፡፡ በእውነቱ ፍቅሩ ልቧን መቷታል፡፡ እኛ በግልጽ ስህተት ውስጥ ሆና በእርግጥ እናያታለን» አሉ፡፡ info
التفاسير: