قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی

صفحہ نمبر:close

external-link copy
123 : 9

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ قَٰتِلُواْ ٱلَّذِينَ يَلُونَكُم مِّنَ ٱلۡكُفَّارِ وَلۡيَجِدُواْ فِيكُمۡ غِلۡظَةٗۚ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلۡمُتَّقِينَ

123. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአቅራቢያችሁ ያሉትን ከሓዲያን ተዋጉ:: በናንተ ውስጥ ብርታትን ያግኙ:: አላህም ከሚጠነቀቁት ጋር መሆኑን እወቁ:: info
التفاسير:

external-link copy
124 : 9

وَإِذَا مَآ أُنزِلَتۡ سُورَةٞ فَمِنۡهُم مَّن يَقُولُ أَيُّكُمۡ زَادَتۡهُ هَٰذِهِۦٓ إِيمَٰنٗاۚ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ فَزَادَتۡهُمۡ إِيمَٰنٗا وَهُمۡ يَسۡتَبۡشِرُونَ

124. ምዕራፍ በተወረደ ጊዜ ከአስመሳዮች ውስጥ «ማንኛችሁ ነው ይህ ምዕራፍ እምነትን የጨመረለት?» የሚል ሰው አለ:: እነዚያ ያመኑት ሰዎች የሚደሰቱ ሲሆኑ እምነትን ጨመረላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
125 : 9

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ فَزَادَتۡهُمۡ رِجۡسًا إِلَىٰ رِجۡسِهِمۡ وَمَاتُواْ وَهُمۡ كَٰفِرُونَ

125. እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ክፍሎች ግን በርክሰታቸው ላይ እርክሰትን ጨመረላቸው:: እነርሱም ከሓዲያን ሆነው ሞቱ:: info
التفاسير:

external-link copy
126 : 9

أَوَلَا يَرَوۡنَ أَنَّهُمۡ يُفۡتَنُونَ فِي كُلِّ عَامٖ مَّرَّةً أَوۡ مَرَّتَيۡنِ ثُمَّ لَا يَتُوبُونَ وَلَا هُمۡ يَذَّكَّرُونَ

126. በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መሆናቸውን አያዩምን? ከዚያ አይጸጸቱምን?እነርሱም አይገሰጹምን? info
التفاسير:

external-link copy
127 : 9

وَإِذَا مَآ أُنزِلَتۡ سُورَةٞ نَّظَرَ بَعۡضُهُمۡ إِلَىٰ بَعۡضٍ هَلۡ يَرَىٰكُم مِّنۡ أَحَدٖ ثُمَّ ٱنصَرَفُواْۚ صَرَفَ ٱللَّهُ قُلُوبَهُم بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَفۡقَهُونَ

127. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን የሚያወሳ ምዕራፍም በተወረደ ጊዜ «የሚያያችሁ (ሰው) አለን?» እያሉ ከፊሎቻቸው ወደ ከፊሉ ይመለከታሉ:: ከዚያ ተደብቀው ይሄዳሉ:: እነርሱ የማያውቁ ህዝቦች በመሆናቸው አላህ ልቦቻቸውን አዞረ:: info
التفاسير:

external-link copy
128 : 9

لَقَدۡ جَآءَكُمۡ رَسُولٞ مِّنۡ أَنفُسِكُمۡ عَزِيزٌ عَلَيۡهِ مَا عَنِتُّمۡ حَرِيصٌ عَلَيۡكُم بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ رَءُوفٞ رَّحِيمٞ

128. (ሰዎች ሆይ!) ከጎሳችሁ ውስጥ የሆነ መቸገራችሁ በእርሱ ላይ ከባድ ጉዳይ የሆነበት፤ እናንተ እምነት እንዲኖራችሁ በጣም የሚጓጓና ለትክክለኛ አማኞችም ሩህሩህና አዛኝ የሆነ መልዕክተኛ (ሙሐመድ) መጣላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
129 : 9

فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقُلۡ حَسۡبِيَ ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ عَلَيۡهِ تَوَكَّلۡتُۖ وَهُوَ رَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ

129. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ቢያፈገፍጉ አላህ በቂዬ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው።» በላቸው:: info
التفاسير: