قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی

አል ሙደሲር

external-link copy
1 : 74

يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمُدَّثِّرُ

1. አንተ (ልብስ) ደራቢው ሆይ! info
التفاسير:

external-link copy
2 : 74

قُمۡ فَأَنذِرۡ

2. ተነሳና (ህዝቦችህን) አስጠንቅቅ። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 74

وَرَبَّكَ فَكَبِّرۡ

3. ጌታህንም አክብር:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 74

وَثِيَابَكَ فَطَهِّرۡ

4. ልብስህንም አጥራ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 74

وَٱلرُّجۡزَ فَٱهۡجُرۡ

5. ጣዖትንም ራቅ:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 74

وَلَا تَمۡنُن تَسۡتَكۡثِرُ

6. ማብዛትንም የምትፈልግ ሆነህ አትለግስ:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 74

وَلِرَبِّكَ فَٱصۡبِرۡ

7. (ብዙ ዒባዳን ከመስራት አትድከም):: ለጌታህም (ትዕዘዛዝ) ታገስ። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 74

فَإِذَا نُقِرَ فِي ٱلنَّاقُورِ

8. በቀንዱም በተነፋ ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 74

فَذَٰلِكَ يَوۡمَئِذٖ يَوۡمٌ عَسِيرٌ

9. ይህን ጊዜ ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 74

عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ غَيۡرُ يَسِيرٖ

10. (በተለይ) በከሓዲያን ላይ ገር ያልሆነ ቀን ነው። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 74

ذَرۡنِي وَمَنۡ خَلَقۡتُ وَحِيدٗا

11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በብቸኝነት ከፈጠርኩት ጋር ተወኝ። info
التفاسير:

external-link copy
12 : 74

وَجَعَلۡتُ لَهُۥ مَالٗا مَّمۡدُودٗا

12. ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በዓይነቱ) አደረግኩለት። info
التفاسير:

external-link copy
13 : 74

وَبَنِينَ شُهُودٗا

13. በየአደባባዩ ተገኝ የሆኑ ወንዶች ልጆችንም ሰጠሁት። info
التفاسير:

external-link copy
14 : 74

وَمَهَّدتُّ لَهُۥ تَمۡهِيدٗا

14. ለእርሱም ኑሮውን መዘርጋትን ዘረጋሁለት፤ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 74

ثُمَّ يَطۡمَعُ أَنۡ أَزِيدَ

15. ከዚያ ልጨምርለት ይከጅላል:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 74

كَلَّآۖ إِنَّهُۥ كَانَ لِأٓيَٰتِنَا عَنِيدٗا

16. ሰው ይከልከል! እርሱ ለአናቅጻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበርና። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 74

سَأُرۡهِقُهُۥ صَعُودًا

17. በእርግጥ (ገሀነም ውስጥ) ችግርን አስገድደዋለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
18 : 74

إِنَّهُۥ فَكَّرَ وَقَدَّرَ

18. እርሱ (በቁርኣን ጉዳይ) አሰበ፤ ገመተም። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 74

فَقُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ

19. እናም ተረገመ:: እንዴት ገመተ! info
التفاسير:

external-link copy
20 : 74

ثُمَّ قُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ

20. ከዚያ ተረገመ። እንዴትስ ገመተ! info
التفاسير:

external-link copy
21 : 74

ثُمَّ نَظَرَ

21. ከዚያም እንደገና (በቁርኣን ጉዳይ) ተመለከተ። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 74

ثُمَّ عَبَسَ وَبَسَرَ

22. ከዚያ ፊቱን አጨፈገገ አኮማተረም:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 74

ثُمَّ أَدۡبَرَ وَٱسۡتَكۡبَرَ

23. ከዚያ (በአላህ ከማመን) ዞረ:: ኮራም:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 74

فَقَالَ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ يُؤۡثَرُ

24. «ይህ ከሌላ (ሰው) የሚቀዳ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 74

إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا قَوۡلُ ٱلۡبَشَرِ

25. «ይህ የሰው ቃል እንጂ ሌላ አይደለም» አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 74

سَأُصۡلِيهِ سَقَرَ

26. ሰቀር (በተባለ የገሀነም ዋሻ ውስጥ) በእርግጥ አስገባዋለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 74

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سَقَرُ

27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰቀር ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ? info
التفاسير:

external-link copy
28 : 74

لَا تُبۡقِي وَلَا تَذَرُ

28. (ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም:: አትተዉምም:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 74

لَوَّاحَةٞ لِّلۡبَشَرِ

29. የሰዎችን ቆዳ በጣም አክሳይ ናት። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 74

عَلَيۡهَا تِسۡعَةَ عَشَرَ

30. በእርሷም ላይ አስራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 74

وَمَا جَعَلۡنَآ أَصۡحَٰبَ ٱلنَّارِ إِلَّا مَلَٰٓئِكَةٗۖ وَمَا جَعَلۡنَا عِدَّتَهُمۡ إِلَّا فِتۡنَةٗ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيَسۡتَيۡقِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَيَزۡدَادَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِيمَٰنٗا وَلَا يَرۡتَابَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَلِيَقُولَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ وَٱلۡكَٰفِرُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلٗاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَمَا يَعۡلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكۡرَىٰ لِلۡبَشَرِ

31. የእሳትን ዘበኞች መላዕክት እንጂ ሌላ አላደረግንም:: ቁጥራቸውንም ለእነዚያ በአላህ ለካዱት ሰዎች መፈተኛ እንጂ ለሌላ አላደረግንም:: እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች እንዲያረጋግጡ፤ እነዚያም በትክክል ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፤ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምዕመናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፤ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አስመሳዮችና ከሓዲያን «አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል?» እንዲሉ እንጂ (አላደረግንም):: ልክ እንደዚሁ አላህ የሚፈልገውን ያጠማል:: የሚፈልገውንም ያቀናል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህንም ሰራዊት ልክ ከእርሱ በስተቀር ማንም አያውቅም:: የሰቀር እሳት ለሰዎች መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 74

كَلَّا وَٱلۡقَمَرِ

32. (ከክህደት) ይከልከሉ:: በጨረቃ (እምላለሁ)፤ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 74

وَٱلَّيۡلِ إِذۡ أَدۡبَرَ

33. በሌሊቱም በሄደ ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 74

وَٱلصُّبۡحِ إِذَآ أَسۡفَرَ

34. በንጋቱም ባበራ ጊዜ እምላለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 74

إِنَّهَا لَإِحۡدَى ٱلۡكُبَرِ

35. (ሰቀር) ከታላላቆች አደጋዎች አንዱ፤ info
التفاسير:

external-link copy
36 : 74

نَذِيرٗا لِّلۡبَشَرِ

36. ለሰዎች አስፈራሪ ናት። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 74

لِمَن شَآءَ مِنكُمۡ أَن يَتَقَدَّمَ أَوۡ يَتَأَخَّرَ

37. ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለፈለገ (ሰው) ሁሉ፤ info
التفاسير:

external-link copy
38 : 74

كُلُّ نَفۡسِۭ بِمَا كَسَبَتۡ رَهِينَةٌ

38. ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ተያዥ ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 74

إِلَّآ أَصۡحَٰبَ ٱلۡيَمِينِ

39. እነዚያ መዝገባቸውን በቀኝ እጃቸው የሚሰጡት ብቻ ሲቀሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 74

فِي جَنَّٰتٖ يَتَسَآءَلُونَ

40. (እነርሱማ) በገነቶች ውስጥ ሁነው እርስ በራሳቸው ይጠያየቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 74

عَنِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ

41. ከአመጸኞች ሁኔታ (ይጠያየቃሉ) info
التفاسير:

external-link copy
42 : 74

مَا سَلَكَكُمۡ فِي سَقَرَ

42. (ከዚያ ለእነርሱ እንዲህ ይሏቸዋል።) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?» info
التفاسير:

external-link copy
43 : 74

قَالُواْ لَمۡ نَكُ مِنَ ٱلۡمُصَلِّينَ

43. «ከሰጋጆች አልነበርንም። info
التفاسير:

external-link copy
44 : 74

وَلَمۡ نَكُ نُطۡعِمُ ٱلۡمِسۡكِينَ

44. «ለድሆችም የምናበላም አልነበርንም። info
التفاسير:

external-link copy
45 : 74

وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ ٱلۡخَآئِضِينَ

45. «ከዘባራቂዎችም ጋር እንዘባርቅ ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
46 : 74

وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ

46. «በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበር፤ info
التفاسير:

external-link copy
47 : 74

حَتَّىٰٓ أَتَىٰنَا ٱلۡيَقِينُ

47. «እርግጠኛው ነገር ሞት እስከመጣብን ድረስ።» ይላሉ info
التفاسير:

external-link copy
48 : 74

فَمَا تَنفَعُهُمۡ شَفَٰعَةُ ٱلشَّٰفِعِينَ

48. እናም በዚያ ቀን የአማላጆች (ሁሉ) ምልጃ አትጠቅማቸዉም። info
التفاسير:

external-link copy
49 : 74

فَمَا لَهُمۡ عَنِ ٱلتَّذۡكِرَةِ مُعۡرِضِينَ

49. ከ(ቁርኣን) ከግሳጼም የሚያፈገፍጉበት ምን ምክኒያት አላቸው? info
التفاسير:

external-link copy
50 : 74

كَأَنَّهُمۡ حُمُرٞ مُّسۡتَنفِرَةٞ

50. እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዩች ይመስላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 74

فَرَّتۡ مِن قَسۡوَرَةِۭ

51. ከአንበሳ የሸሹ info
التفاسير:

external-link copy
52 : 74

بَلۡ يُرِيدُ كُلُّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ أَن يُؤۡتَىٰ صُحُفٗا مُّنَشَّرَةٗ

52. ይልቁንም ከእነርሱ መካከል ለእያንዳንዱ ሰው የተዘረጉ ጹሑፎችን በእጁ እንዲሰጥ ይፈልጋል:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 74

كَلَّاۖ بَل لَّا يَخَافُونَ ٱلۡأٓخِرَةَ

53. ከዚህ መሰል ተግባራቸው ይከልከሉ:: ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም ቅጣት አይፈሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
54 : 74

كَلَّآ إِنَّهُۥ تَذۡكِرَةٞ

54. ይከልከሉ፤እርሱ(ቁርአን) መገሰጫ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
55 : 74

فَمَن شَآءَ ذَكَرَهُۥ

55. ስለዚህ የፈለገ ሰው ቁርኣንን ይገሰጽበታል:: info
التفاسير:

external-link copy
56 : 74

وَمَا يَذۡكُرُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُۚ هُوَ أَهۡلُ ٱلتَّقۡوَىٰ وَأَهۡلُ ٱلۡمَغۡفِرَةِ

56. ሆኖም (ሰዎች) አላህ ካልፈለገ በስተቀር አይገሰጹም:: አላህ የመፈራት ባለቤት ነው:: (ለፈሩትም) የምህረት ባለቤት ነው:: info
التفاسير: