قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی

صفحہ نمبر:close

external-link copy
38 : 7

قَالَ ٱدۡخُلُواْ فِيٓ أُمَمٖ قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِكُم مِّنَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ فِي ٱلنَّارِۖ كُلَّمَا دَخَلَتۡ أُمَّةٞ لَّعَنَتۡ أُخۡتَهَاۖ حَتَّىٰٓ إِذَا ٱدَّارَكُواْ فِيهَا جَمِيعٗا قَالَتۡ أُخۡرَىٰهُمۡ لِأُولَىٰهُمۡ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ أَضَلُّونَا فَـَٔاتِهِمۡ عَذَابٗا ضِعۡفٗا مِّنَ ٱلنَّارِۖ قَالَ لِكُلّٖ ضِعۡفٞ وَلَٰكِن لَّا تَعۡلَمُونَ

38. «ከጋኔንና ከሰዉም ከናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ።» ይላቸዋል:: አንዲቱ ቡድን ህዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር ያሳሳተቻትን ብጤዋን ቡድን ትረግማለች:: መላዉም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙ ጊዜ የኋለኛይቱ (ተከታዮች) ቡድን ለመጀመሪያይቱ (ለአስከታዮች) ቡድን፡- «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው።» ትላለች:: አላህም፡- «ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም።» ይላቸዋል። info
التفاسير:

external-link copy
39 : 7

وَقَالَتۡ أُولَىٰهُمۡ لِأُخۡرَىٰهُمۡ فَمَا كَانَ لَكُمۡ عَلَيۡنَا مِن فَضۡلٖ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡسِبُونَ

39. መጀመሪያይቱ ቡድንም ለኋለኛይቱ ቡድን «ለእናንተ በእኛ ላይ ምንም ብልጫ አልነበራችሁም ትላለች:: ትሠሩትም በነበራችሁት ቅጣቱን ቅመሱ።» ይሏቸዋል። info
التفاسير:

external-link copy
40 : 7

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسۡتَكۡبَرُواْ عَنۡهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمۡ أَبۡوَٰبُ ٱلسَّمَآءِ وَلَا يَدۡخُلُونَ ٱلۡجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ ٱلۡجَمَلُ فِي سَمِّ ٱلۡخِيَاطِۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُجۡرِمِينَ

40. እነዚያ አናቅጻችንን ያስተባበሉና ከእርሷም የኮሩ ሁሉ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸዉም:: ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባ ድረስም ወደ ገነት አይገቡም:: ልክ እንደዚሁ አመጸኞችን እንቀጣለን:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 7

لَهُم مِّن جَهَنَّمَ مِهَادٞ وَمِن فَوۡقِهِمۡ غَوَاشٖۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلظَّٰلِمِينَ

41. ለእነርሱም በሥራቸው ምክንያት ከገሀነም እሳት ምንጣፍ ከበላያቸዉም የእሳት መሸፈኛዎች አሉባቸው:: ልክ እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 7

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَآ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ

42. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካሞችን የሰሩ ማንኛውንም ነፍስ የችሎታዋን እንጂ አናስገድድም:: እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 7

وَنَزَعۡنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنۡ غِلّٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمُ ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ وَقَالُواْ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي هَدَىٰنَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهۡتَدِيَ لَوۡلَآ أَنۡ هَدَىٰنَا ٱللَّهُۖ لَقَدۡ جَآءَتۡ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلۡحَقِّۖ وَنُودُوٓاْ أَن تِلۡكُمُ ٱلۡجَنَّةُ أُورِثۡتُمُوهَا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

43. በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ጥላቻም እናስወግዳለን:: ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ:: «ለዚያም ወደዚህ ላደረሰን ሥራ ለመራን ለአላህ ብቻ ምስጋና ይገባው:: አላህ ባልመራን ኖሮ ወደዚህ አንመራም ነበር:: የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት ላይ ሲሆኑ መጥተውልናል።» ይላሉ:: «ይህ ገነት ትሠሩት በነበራችሁት እንድትወርሱት የተደረጋችሁት ነው።» በማለት ይጠራሉ:: info
التفاسير: