قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی

አል ሓቃህ

external-link copy
1 : 69

ٱلۡحَآقَّةُ

1. እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሳኤ):: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 69

مَا ٱلۡحَآقَّةُ

2. አረጋጋጪቱ (እርሷ) ምንድን ናት! info
التفاسير:

external-link copy
3 : 69

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡحَآقَّةُ

3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አረጋግጪቱም ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ? info
التفاسير:

external-link copy
4 : 69

كَذَّبَتۡ ثَمُودُ وَعَادُۢ بِٱلۡقَارِعَةِ

4. የሰሙድና የዓድ ህዝቦች በቆርቋሪይቱ (ትንሳኤ) ቀን አስተባበሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 69

فَأَمَّا ثَمُودُ فَأُهۡلِكُواْ بِٱلطَّاغِيَةِ

5. የሰሙድ ህዝቦችማ ወሰን በሌላት ነፋስ ጩኸት ተጠፉ:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 69

وَأَمَّا عَادٞ فَأُهۡلِكُواْ بِرِيحٖ صَرۡصَرٍ عَاتِيَةٖ

6. የዓድ ህዝቦችማ በኃይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 69

سَخَّرَهَا عَلَيۡهِمۡ سَبۡعَ لَيَالٖ وَثَمَٰنِيَةَ أَيَّامٍ حُسُومٗاۖ فَتَرَى ٱلۡقَوۡمَ فِيهَا صَرۡعَىٰ كَأَنَّهُمۡ أَعۡجَازُ نَخۡلٍ خَاوِيَةٖ

7. ተከታታይ በሆነ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት ቀናቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት:: ህዝቦችንም፤ በውስጧ የተጣሉ ሆነው ልክ ክፍት እደሆኑ የበሰበሱ የዘንባባ ግንዶች ታያቸዋለህ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 69

فَهَلۡ تَرَىٰ لَهُم مِّنۢ بَاقِيَةٖ

8. ከእነርሱ መካከል ቀሪን ታያለህን? info
التفاسير:

external-link copy
9 : 69

وَجَآءَ فِرۡعَوۡنُ وَمَن قَبۡلَهُۥ وَٱلۡمُؤۡتَفِكَٰتُ بِٱلۡخَاطِئَةِ

9. ፈርዖን፤ ከበፊቱ የነበሩትን ሰዎችም፤ ተገልባጮችም (የሉጥ ሰዎች ከተሞች) ኃጢአት ፈጸሙ። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 69

فَعَصَوۡاْ رَسُولَ رَبِّهِمۡ فَأَخَذَهُمۡ أَخۡذَةٗ رَّابِيَةً

10. የጌታቸውንም መልዕክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፤ የበረታችንም ቅጣት ቀጣቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 69

إِنَّا لَمَّا طَغَا ٱلۡمَآءُ حَمَلۡنَٰكُمۡ فِي ٱلۡجَارِيَةِ

11. እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሳፋፊይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 69

لِنَجۡعَلَهَا لَكُمۡ تَذۡكِرَةٗ وَتَعِيَهَآ أُذُنٞ وَٰعِيَةٞ

12. ይህንም ያደረግነው ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋትና አጥኚ የሆነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 69

فَإِذَا نُفِخَ فِي ٱلصُّورِ نَفۡخَةٞ وَٰحِدَةٞ

13. በቀንዱ አንዲት መነፋት በተነፋች ጊዜ:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 69

وَحُمِلَتِ ٱلۡأَرۡضُ وَٱلۡجِبَالُ فَدُكَّتَا دَكَّةٗ وَٰحِدَةٗ

14. ምድርና ጋራዎች (ከየስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 69

فَيَوۡمَئِذٖ وَقَعَتِ ٱلۡوَاقِعَةُ

15. በዚያ ቀን (ትንሳኤ) ትከሰታለች:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 69

وَٱنشَقَّتِ ٱلسَّمَآءُ فَهِيَ يَوۡمَئِذٖ وَاهِيَةٞ

16. ሰማይም ትቀደዳለች:: በመሆኑም እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፤ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 69

وَٱلۡمَلَكُ عَلَىٰٓ أَرۡجَآئِهَاۚ وَيَحۡمِلُ عَرۡشَ رَبِّكَ فَوۡقَهُمۡ يَوۡمَئِذٖ ثَمَٰنِيَةٞ

17. መላዕክትም በየጫፎቿ ላይ ይሆናሉ:: የጌታህንም ዓርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላዕክት ከበላያቸው ይሸከማሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 69

يَوۡمَئِذٖ تُعۡرَضُونَ لَا تَخۡفَىٰ مِنكُمۡ خَافِيَةٞ

18. በዚያ ቀን ከናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲሆኑ ትቀረባላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 69

فَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ فَيَقُولُ هَآؤُمُ ٱقۡرَءُواْ كِتَٰبِيَهۡ

19. ያ መጽሀፉን በቀኝ እጁ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ እንዲህ) ይላል: «እንኩ መጽሐፌን አንብቡ፤ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 69

إِنِّي ظَنَنتُ أَنِّي مُلَٰقٍ حِسَابِيَهۡ

20. «እኔ ምርመራየን የምገናኝ መሆኔን አረጋገጥኩ።» (ይላል) info
التفاسير:

external-link copy
21 : 69

فَهُوَ فِي عِيشَةٖ رَّاضِيَةٖ

21. እርሱም በተወደደች ኑሮ ውስጥ ይሆናል:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 69

فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٖ

22. በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፤ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 69

قُطُوفُهَا دَانِيَةٞ

23. ፍሬዎቿ ቅርቦች የሆኑ:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 69

كُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ هَنِيٓـَٔۢا بِمَآ أَسۡلَفۡتُمۡ فِي ٱلۡأَيَّامِ ٱلۡخَالِيَةِ

24. በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 69

وَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِشِمَالِهِۦ فَيَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي لَمۡ أُوتَ كِتَٰبِيَهۡ

25. ያ መጽሐፉን በግራው የተሰጠ ሰው ደግሞ (እንዲህ) ይላል: «ዋ ጥፋቴ ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ፤ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 69

وَلَمۡ أَدۡرِ مَا حِسَابِيَهۡ

26. «ምርመራዬም ምን እንደሆነ ባላወቅሁ፤ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 69

يَٰلَيۡتَهَا كَانَتِ ٱلۡقَاضِيَةَ

27. «ሞት ምነው የህይወቴ የመጨረሻ ፍፃሜ በሆነች፤ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 69

مَآ أَغۡنَىٰ عَنِّي مَالِيَهۡۜ

28. «ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አልጠቀመኝም፤ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 69

هَلَكَ عَنِّي سُلۡطَٰنِيَهۡ

29. «ስልጣኔ ከእኔ ላይ ጠፋ» ይላል:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 69

خُذُوهُ فَغُلُّوهُ

30. ያዙት ከዚያ እጁን ከአንገቱ ጋር እሰሩት፤ info
التفاسير:

external-link copy
31 : 69

ثُمَّ ٱلۡجَحِيمَ صَلُّوهُ

31. ከዚያ በእሳት ውስጥ አስገቡት፤ info
التفاسير:

external-link copy
32 : 69

ثُمَّ فِي سِلۡسِلَةٖ ذَرۡعُهَا سَبۡعُونَ ذِرَاعٗا فَٱسۡلُكُوهُ

32. ከዚም እርዝመቷ ሰባ ክንድ በሆነች ሰንሰለት ውስጥ አስገቡት። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 69

إِنَّهُۥ كَانَ لَا يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ ٱلۡعَظِيمِ

33. እርሱ ታላቅ በሆነው አላህ አያምንም ነበርና፤ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 69

وَلَا يَحُضُّ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلۡمِسۡكِينِ

34. ድሆችንም በማብላት ላይ አያነሳሳም ነበርና:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 69

فَلَيۡسَ لَهُ ٱلۡيَوۡمَ هَٰهُنَا حَمِيمٞ

35. ለእርሱ ዛሬ እዚህ ቦታ ዘመድ ማንም የለዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 69

وَلَا طَعَامٌ إِلَّا مِنۡ غِسۡلِينٖ

36. ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ እዥ በስተቀር የለዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 69

لَّا يَأۡكُلُهُۥٓ إِلَّا ٱلۡخَٰطِـُٔونَ

37. ይህን ምግብ ኃጢአተኞች እንጂ ሌላ አይበላዉም ይባላል:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 69

فَلَآ أُقۡسِمُ بِمَا تُبۡصِرُونَ

38. በምታዩት ነገር ሁሉ እምላለሁ :: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 69

وَمَا لَا تُبۡصِرُونَ

39. በማታዩትም ነገር ሁሉ እምላለሁ :: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 69

إِنَّهُۥ لَقَوۡلُ رَسُولٖ كَرِيمٖ

40. ቁርኣን የተከበረው መልዕክተኛ ቃል ነው። info
التفاسير:

external-link copy
41 : 69

وَمَا هُوَ بِقَوۡلِ شَاعِرٖۚ قَلِيلٗا مَّا تُؤۡمِنُونَ

41. እርሱም የባለ ቅኔ ገጣሚ ቃል አይደለም:: ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 69

وَلَا بِقَوۡلِ كَاهِنٖۚ قَلِيلٗا مَّا تَذَكَّرُونَ

42. የጠንቋይም ቃል አይደለም:: ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 69

تَنزِيلٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

43. ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 69

وَلَوۡ تَقَوَّلَ عَلَيۡنَا بَعۡضَ ٱلۡأَقَاوِيلِ

44. በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት እንኳን (ያላልነው) በቀጠፈ ኖሮ፤ info
التفاسير:

external-link copy
45 : 69

لَأَخَذۡنَا مِنۡهُ بِٱلۡيَمِينِ

45. በኃይል በቀጣነው ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 69

ثُمَّ لَقَطَعۡنَا مِنۡهُ ٱلۡوَتِينَ

46. ከዚያ ከእርሱ የልቡን ስር የተንጠላጠለበትን (ጅማት) በቆረጥን ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 69

فَمَا مِنكُم مِّنۡ أَحَدٍ عَنۡهُ حَٰجِزِينَ

47. ከናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም። info
التفاسير:

external-link copy
48 : 69

وَإِنَّهُۥ لَتَذۡكِرَةٞ لِّلۡمُتَّقِينَ

48. እርሱ (ቁርኣን) ለጥንቅቆቹ ብቻ መገሰጫ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 69

وَإِنَّا لَنَعۡلَمُ أَنَّ مِنكُم مُّكَذِّبِينَ

49. እኛም ከናንተ ውስጥ አስተባባዩች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 69

وَإِنَّهُۥ لَحَسۡرَةٌ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ

50. እርሱ (ቁርኣንም) በከሓዲያን ላይ ጸጸት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 69

وَإِنَّهُۥ لَحَقُّ ٱلۡيَقِينِ

51. እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 69

فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ

52. እናም የታላቁን ጌታህን ስም (ታላቁን ጌታህን) አጥራው:: info
التفاسير: