قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی

صفحہ نمبر:close

external-link copy
119 : 6

وَمَا لَكُمۡ أَلَّا تَأۡكُلُواْ مِمَّا ذُكِرَ ٱسۡمُ ٱللَّهِ عَلَيۡهِ وَقَدۡ فَصَّلَ لَكُم مَّا حَرَّمَ عَلَيۡكُمۡ إِلَّا مَا ٱضۡطُرِرۡتُمۡ إِلَيۡهِۗ وَإِنَّ كَثِيرٗا لَّيُضِلُّونَ بِأَهۡوَآئِهِم بِغَيۡرِ عِلۡمٍۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُعۡتَدِينَ

119. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱን መብላት ካልተገደዳችሁበት በስተቀር በእናንተ እርም የተደረገውን ለእናተ አላህ በእርግጥ የዘረዘረ ሲሆን ከዚያ በእርሱ ላይ የአላህ ስም ከተጠራበት የማትበሉት ምን ምክንያት አላችሁ? ብዙዎቹም ያለ እውቀት በዝንባሌዎቻቸው ብቻ ያሳስታሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ወሰን አላፊዎቹን አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
120 : 6

وَذَرُواْ ظَٰهِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَبَاطِنَهُۥٓۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡسِبُونَ ٱلۡإِثۡمَ سَيُجۡزَوۡنَ بِمَا كَانُواْ يَقۡتَرِفُونَ

120. የኃጢአትን ግልጹንም ድብቁንም ተው:: እነዚያ ኃጢአትን የሚሰሩ ሁሉ ይሰሩት በነበሩበት ነገር በእያንዳንዱ በእርግጥ ይመነዳሉ። info
التفاسير:

external-link copy
121 : 6

وَلَا تَأۡكُلُواْ مِمَّا لَمۡ يُذۡكَرِ ٱسۡمُ ٱللَّهِ عَلَيۡهِ وَإِنَّهُۥ لَفِسۡقٞۗ وَإِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ لَيُوحُونَ إِلَىٰٓ أَوۡلِيَآئِهِمۡ لِيُجَٰدِلُوكُمۡۖ وَإِنۡ أَطَعۡتُمُوهُمۡ إِنَّكُمۡ لَمُشۡرِكُونَ

121. (ሙስሊሞች ሆይ!) በእርሱ ላይ የአላህ ስም ያልተወሳበትን አትብሉ:: እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው:: ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ ያሾከሹካሉ:: ታዲያ ብትታዘዟቸው በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
122 : 6

أَوَمَن كَانَ مَيۡتٗا فَأَحۡيَيۡنَٰهُ وَجَعَلۡنَا لَهُۥ نُورٗا يَمۡشِي بِهِۦ فِي ٱلنَّاسِ كَمَن مَّثَلُهُۥ فِي ٱلظُّلُمَٰتِ لَيۡسَ بِخَارِجٖ مِّنۡهَاۚ كَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِلۡكَٰفِرِينَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

122. ሙት የነበረና ከዚያም ህያው አድርገነው ለርሱም በሰዎች መካከል የሚሄድበትን ብርሃን ያደረግንለት በጨለማዎች ውስጥ ምንጊዜም የማይወጣ ሆኖ እንዳለው ብጤ ነውን? ልክ እንደዚሁ ለከሓዲያን ሁሉ ይሰሩት የነበሩት ነገር ተዋበላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
123 : 6

وَكَذَٰلِكَ جَعَلۡنَا فِي كُلِّ قَرۡيَةٍ أَكَٰبِرَ مُجۡرِمِيهَا لِيَمۡكُرُواْ فِيهَاۖ وَمَا يَمۡكُرُونَ إِلَّا بِأَنفُسِهِمۡ وَمَا يَشۡعُرُونَ

123. ልክ እንደዚሁ በየከተማይቱ ውስጥ ታላላቅ ወንጀለኞቿ በውስጧ እንዲያሴሩ አደረግን። በነፍሶቻቸው ላይ እንጂ በሌላ ላይ አያሴሩም:: ግን ይህን እውነታ አያውቁም። info
التفاسير:

external-link copy
124 : 6

وَإِذَا جَآءَتۡهُمۡ ءَايَةٞ قَالُواْ لَن نُّؤۡمِنَ حَتَّىٰ نُؤۡتَىٰ مِثۡلَ مَآ أُوتِيَ رُسُلُ ٱللَّهِۘ ٱللَّهُ أَعۡلَمُ حَيۡثُ يَجۡعَلُ رِسَالَتَهُۥۗ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ أَجۡرَمُواْ صَغَارٌ عِندَ ٱللَّهِ وَعَذَابٞ شَدِيدُۢ بِمَا كَانُواْ يَمۡكُرُونَ

124. ተዓምር በመጣላቸውም ጊዜ «የአላህ መልዕክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ:: አላህ መልዕክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ አዋቂ ነው:: እነዚያን በአላህ ያመጹ ሰዎች ይዶልቱት በነበሩት ነገር አላህ ዘንድ ውርደትና ብርቱ ቅጣት ያገኛቸዋል:: info
التفاسير: