قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی

صفحہ نمبر:close

external-link copy
84 : 3

قُلۡ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ عَلَيۡنَا وَمَآ أُنزِلَ عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡمَٰعِيلَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ وَٱلۡأَسۡبَاطِ وَمَآ أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَٱلنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمۡ لَا نُفَرِّقُ بَيۡنَ أَحَدٖ مِّنۡهُمۡ وَنَحۡنُ لَهُۥ مُسۡلِمُونَ

84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በአላህ አምነናል በእኛም ላይ በተወረደው በቁርኣን (በነብዩ) ኢብራሂም፣ (በነብዩ) ኢስማኢል፣ (በነብዩ) ኢስሀቅ፣ (በነብዩ) የዕቆብና በነገዶች ላይ በተወረደው፣ ለነብዩ ሙሳ ለነብዩ ዒሳና ለነብያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው ሁሉ አምነናል:: በእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም:: እኛ ለእርሱ ብቻ ታዛዦች ነን።» በል። info
التفاسير:

external-link copy
85 : 3

وَمَن يَبۡتَغِ غَيۡرَ ٱلۡإِسۡلَٰمِ دِينٗا فَلَن يُقۡبَلَ مِنۡهُ وَهُوَ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ

85. ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሁሉ ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይነት የለዉም:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ አንዱ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
86 : 3

كَيۡفَ يَهۡدِي ٱللَّهُ قَوۡمٗا كَفَرُواْ بَعۡدَ إِيمَٰنِهِمۡ وَشَهِدُوٓاْ أَنَّ ٱلرَّسُولَ حَقّٞ وَجَآءَهُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُۚ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

86. ከእምነታቸውና መልዕክተኛዉም እውነት መሆኑን ከመሰከሩ፤ የተብራሩ አናቅጽም ከመጡላቸው በኋላ የካዱ ሕዝቦችን አላህ እንዴት ያቀናል? አላህ በዳዮችን ሕዝቦች አያቀናምና። info
التفاسير:

external-link copy
87 : 3

أُوْلَٰٓئِكَ جَزَآؤُهُمۡ أَنَّ عَلَيۡهِمۡ لَعۡنَةَ ٱللَّهِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلنَّاسِ أَجۡمَعِينَ

87. እነዚያን መሰሎች ቅጣታቸው የአላህ፣ የመላዕክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በእነርሱ ላይ መውረዱ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
88 : 3

خَٰلِدِينَ فِيهَا لَا يُخَفَّفُ عَنۡهُمُ ٱلۡعَذَابُ وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ

88. በውስጧ ዘወታሪዎች ሲሆኑ ቅጣቱም ከእነርሱ ላይ አይቃለልላቸዉም:: ጊዜም አይሰጡም:: info
التفاسير:

external-link copy
89 : 3

إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ وَأَصۡلَحُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ

89. እነዚያ ከዚያ በኋላ ንስሀ የገቡና ስራቸውን ያሳመሩ ሁሉ ሲቀሩ፤ (አላህ እነዚህንማ ይምራቸዋል።) አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
90 : 3

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بَعۡدَ إِيمَٰنِهِمۡ ثُمَّ ٱزۡدَادُواْ كُفۡرٗا لَّن تُقۡبَلَ تَوۡبَتُهُمۡ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلضَّآلُّونَ

90. እነዚያ ከእምነታቸው በኋላ የካዱና ከዚያ ክህደትን በክህደት ላይ የጨመሩ ንሰሃቸው ፈጽሞ ተቀባይነት የለዉም:: የተሳሳቱ ማለት እነርሱው ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
91 : 3

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَمَاتُواْ وَهُمۡ كُفَّارٞ فَلَن يُقۡبَلَ مِنۡ أَحَدِهِم مِّلۡءُ ٱلۡأَرۡضِ ذَهَبٗا وَلَوِ ٱفۡتَدَىٰ بِهِۦٓۗ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ

91. እነዚያ የካዱና በክህደታቸው ላይ እንዳሉ የሞቱ፤ ከእነርሱ አንዳቸው ምድርን የሞላ ወርቅ ቤዛ ቢያቀርብም እንኳ ፈጽሞ ተቀባይነት አያገኝም:: እነዚያ ለእነርሱ የሚያሰቃይ ቅጣት አለባቸው:: ለእነርሱም (ከዚህ ቅጣት) የሚያድኗቸው ምንም ረዳቶች የሏቸዉም:: info
التفاسير: