قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی

አልን ኑር

external-link copy
1 : 24

سُورَةٌ أَنزَلۡنَٰهَا وَفَرَضۡنَٰهَا وَأَنزَلۡنَا فِيهَآ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖ لَّعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ

1.(ሙስሊሞች ሆይ!) (ይህ) ያወረድነውና በእናንተ ላይ (እንድትሰሩበት) የደነገግነው ምዕራፍ ነው:: እርሱ በርሷም ውስጥ ትገሰጹ ዘንድ ግልጽ አናቅጽን አውርደናል:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 24

ٱلزَّانِيَةُ وَٱلزَّانِي فَٱجۡلِدُواْ كُلَّ وَٰحِدٖ مِّنۡهُمَا مِاْئَةَ جَلۡدَةٖۖ وَلَا تَأۡخُذۡكُم بِهِمَا رَأۡفَةٞ فِي دِينِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۖ وَلۡيَشۡهَدۡ عَذَابَهُمَا طَآئِفَةٞ مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

2. ዝሙተኛይቱ ሴትና ዝሙተኛው ወንድ ከሁለቱ እያንዳንዳቸው (ያላገቡ እንደሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፏቸው:: በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደሆናችሁ በእነርሱ ላይ በደነገገው በአላህ ፍርድ ርህራሄ አትያዛችሁ። ሙስሊሞች ሆይ! ቅጣታቸውንም በምትፈጽሙበት ጊዜ ከአማኞች የተወሰኑ ቡድኖች ይገኙበት:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 24

ٱلزَّانِي لَا يَنكِحُ إِلَّا زَانِيَةً أَوۡ مُشۡرِكَةٗ وَٱلزَّانِيَةُ لَا يَنكِحُهَآ إِلَّا زَانٍ أَوۡ مُشۡرِكٞۚ وَحُرِّمَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

3. ዝሙተኛ ወንድ ዝሙተኛን ሴት ወይም በአላህ አጋሪን ሴት እንጂ ሌላን አያገባም (አይፈልግም) :: ዝሙተኛይቱም ሴት ዝሙተኛ ወይም በአላህ አጋሪ ወንድ እንጂ ሌላ አያገባትም (አይፈልጋትም):: ይህም በአማኞች ላይ ተከልክሏል:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 24

وَٱلَّذِينَ يَرۡمُونَ ٱلۡمُحۡصَنَٰتِ ثُمَّ لَمۡ يَأۡتُواْ بِأَرۡبَعَةِ شُهَدَآءَ فَٱجۡلِدُوهُمۡ ثَمَٰنِينَ جَلۡدَةٗ وَلَا تَقۡبَلُواْ لَهُمۡ شَهَٰدَةً أَبَدٗاۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَٰسِقُونَ

4. እነዚያ ጥብቆችን ሴቶች በዝሙት የሚሰድቡ ከዚያ በሰደቡበት አራት ምስክሮች ያላመጡ ሰማንያ ግርፋት ግረፏቸው:: ከእነርሱም ምስክርነትን ለሁልጊዜ አትቀበሉ:: እነዚያም እነርሱ አመጸኞች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 24

إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ وَأَصۡلَحُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

5. እነዚያ ከዚህ በኋላ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩ ሲቀሩ:: አላህ በጣም መሓሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 24

وَٱلَّذِينَ يَرۡمُونَ أَزۡوَٰجَهُمۡ وَلَمۡ يَكُن لَّهُمۡ شُهَدَآءُ إِلَّآ أَنفُسُهُمۡ فَشَهَٰدَةُ أَحَدِهِمۡ أَرۡبَعُ شَهَٰدَٰتِۭ بِٱللَّهِ إِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

6. እነዚያ ሚስቶቻቻውን (በዝሙት) የሚሰድቡ ለነሱም ከነፍሶቻቸው በስተቀር ምስክሮች የሌሏቸው የሆኑ የአንዳቸው ምስክርነት ከእውነተኞች ለመሆናቸው በአላህ ስም አራት ጊዜ ምሎ መመስከር ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 24

وَٱلۡخَٰمِسَةُ أَنَّ لَعۡنَتَ ٱللَّهِ عَلَيۡهِ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ

7. አምስተኛይቱም ከውሸታሞች ቢሆን በእርሱ ላይ የአላህ እርግማን እንዲሰፍንበት (ምሎ መመስከር ነው)። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 24

وَيَدۡرَؤُاْ عَنۡهَا ٱلۡعَذَابَ أَن تَشۡهَدَ أَرۡبَعَ شَهَٰدَٰتِۭ بِٱللَّهِ إِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ

8. «እርሱም ከውሸታሞች ነው።» ብላ አራት ጊዜ በአላህ ስም መመስከሯ ከእርሷ ላይ ቅጣትን ይከላከልላታል:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 24

وَٱلۡخَٰمِسَةَ أَنَّ غَضَبَ ٱللَّهِ عَلَيۡهَآ إِن كَانَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

9. አምስተኛይቱም እርሱ ከእውነተኞች ቢሆን በርሷ ላይ የአላህ ቁጣ ይኑርባት ብላ መመስከሯ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 24

وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ وَرَحۡمَتُهُۥ وَأَنَّ ٱللَّهَ تَوَّابٌ حَكِيمٌ

10. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረና አላህ ጸጸትን ተቀባይና ጥበበኛ ባልሆነ ኖሮ (ውሸታሙን ሁሉ በዚሁ አለም ላይ ይገልጸው ነበር):: info
التفاسير: