قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى

بەت نومۇرى:close

external-link copy
37 : 5

يُرِيدُونَ أَن يَخۡرُجُواْ مِنَ ٱلنَّارِ وَمَا هُم بِخَٰرِجِينَ مِنۡهَاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٞ مُّقِيمٞ

37. ከእሳት ሊወጡ ይፈልጋሉ:: እነርሱ ግን ሁልጊዜም ከእርሷ ወጪዎች አይደሉም:: ለእነርሱ ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 5

وَٱلسَّارِقُ وَٱلسَّارِقَةُ فَٱقۡطَعُوٓاْ أَيۡدِيَهُمَا جَزَآءَۢ بِمَا كَسَبَا نَكَٰلٗا مِّنَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٞ

38. የወንድ ሌባንና የሴት ሌባን ለሰሩት ወንጀል ከአላህ የሆነ መቀጫ ሲሆን እጆቻቸውን ቁረጡ:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 5

فَمَن تَابَ مِنۢ بَعۡدِ ظُلۡمِهِۦ وَأَصۡلَحَ فَإِنَّ ٱللَّهَ يَتُوبُ عَلَيۡهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ

39. ከበደለ በኋላ የተጸጸተና ስራውን ያሳመረ ሁሉ አላህ ጸጸቱን ይቀበለዋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 5

أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ يُعَذِّبُ مَن يَشَآءُ وَيَغۡفِرُ لِمَن يَشَآءُۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእሱ ብቻ መሆኑን አላወክምን? የሚሻውን ሰው ይቀጣል:: ለሚሻውም ሰው ይምራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 5

۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلرَّسُولُ لَا يَحۡزُنكَ ٱلَّذِينَ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡكُفۡرِ مِنَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِأَفۡوَٰهِهِمۡ وَلَمۡ تُؤۡمِن قُلُوبُهُمۡۛ وَمِنَ ٱلَّذِينَ هَادُواْۛ سَمَّٰعُونَ لِلۡكَذِبِ سَمَّٰعُونَ لِقَوۡمٍ ءَاخَرِينَ لَمۡ يَأۡتُوكَۖ يُحَرِّفُونَ ٱلۡكَلِمَ مِنۢ بَعۡدِ مَوَاضِعِهِۦۖ يَقُولُونَ إِنۡ أُوتِيتُمۡ هَٰذَا فَخُذُوهُ وَإِن لَّمۡ تُؤۡتَوۡهُ فَٱحۡذَرُواْۚ وَمَن يُرِدِ ٱللَّهُ فِتۡنَتَهُۥ فَلَن تَمۡلِكَ لَهُۥ مِنَ ٱللَّهِ شَيۡـًٔاۚ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَمۡ يُرِدِ ٱللَّهُ أَن يُطَهِّرَ قُلُوبَهُمۡۚ لَهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا خِزۡيٞۖ وَلَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٞ

41. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እነዚያ ወደ ክህደት የሚቻኮሉ ሆነው ልቦቻቸው ሳያምኑ በአፎቻቸው ብቻ «አመንን» ካሉት አስመሳዮችና ከእነዚያም አይሁዶቹ አያሳዝኑህ:: እነርሱ ውሸትን ብቻ አድማጮች ናቸውና:: ገና ወደ አንተ ላልመጡ ለሌሎች ሕዝቦች አድማጮች ናቸው:: ንግግሮችንም ከስፍሮቻቸው ወደ ሌላ በመቀየር መልዕክት ያጣምማሉ። «ይህንን የተጣመመውን ከተሰጣችሁ ያዙት:: ካልተሰጣችሁም ተጠንቀቁ።» ይላሉ:: አላህ መፈተንን የሚሻበትን ሰው ሁሉ ለእርሱ ከአላህ ለመከላከል ፍጹም አትችልም:: እነዚያ ማለት አላህ ልቦቻቸውን ማጥራትን ያልሻላቸው ሰዎች ናቸው:: ለእነርሱም በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አለባቸው:: ለእነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለምም ሌላ ከባድ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير: