قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى

بەت نومۇرى:close

external-link copy
61 : 43

وَإِنَّهُۥ لَعِلۡمٞ لِّلسَّاعَةِ فَلَا تَمۡتَرُنَّ بِهَا وَٱتَّبِعُونِۚ هَٰذَا صِرَٰطٞ مُّسۡتَقِيمٞ

61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱም (ዒሳ) ለስዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው:: በእርሷም አትጠራጠሩ:: ተከተሉኝም:: ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
62 : 43

وَلَا يَصُدَّنَّكُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُۖ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوّٞ مُّبِينٞ

62. ሰይጣንም አያግዳችሁ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 43

وَلَمَّا جَآءَ عِيسَىٰ بِٱلۡبَيِّنَٰتِ قَالَ قَدۡ جِئۡتُكُم بِٱلۡحِكۡمَةِ وَلِأُبَيِّنَ لَكُم بَعۡضَ ٱلَّذِي تَخۡتَلِفُونَ فِيهِۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

63. ዒሳ ግልፅ ተዓምራታችንን ይዞ በመጣ ጊዜ «በእርግጥ በጥበብ መጣሁላችሁ:: የዚያንም የምትለያዩበትን ጉዳይ ከፊሉን ለእናንተ ላብራራላችሁ መጣሁ:: እናም አላህን ፍሩ:: ታዘዙኝም:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 43

إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ رَبِّي وَرَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُوهُۚ هَٰذَا صِرَٰطٞ مُّسۡتَقِيمٞ

64. «አላህ ጌታዬ ጌታችሁም ነውና በብቸኝነት ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው::» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
65 : 43

فَٱخۡتَلَفَ ٱلۡأَحۡزَابُ مِنۢ بَيۡنِهِمۡۖ فَوَيۡلٞ لِّلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡ عَذَابِ يَوۡمٍ أَلِيمٍ

65. ከመካከላቸዉም አህዛቦቹ ተለያዩ:: ለእነዚያም ለበደሉት ህዝቦች ከአሳማሚ ቀን ቅጣት ወዮላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
66 : 43

هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّا ٱلسَّاعَةَ أَن تَأۡتِيَهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ

66. ሰዓቲቱን እነርሱ የማያውቁ ሆነው በድንገት ልትመጣባቸው እንጂ (ሌላ) ይጠባበቃሉን?:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 43

ٱلۡأَخِلَّآءُ يَوۡمَئِذِۭ بَعۡضُهُمۡ لِبَعۡضٍ عَدُوٌّ إِلَّا ٱلۡمُتَّقِينَ

67. አላህን የሚፈሩ ሰዎች ብቻ ሲቀሩ ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
68 : 43

يَٰعِبَادِ لَا خَوۡفٌ عَلَيۡكُمُ ٱلۡيَوۡمَ وَلَآ أَنتُمۡ تَحۡزَنُونَ

68. (አላህም ለነርሱ) «ባሮቼ ሆይ! ዛሬ ቀን በእናንተ ላይ ምንም ፍርሀት የለባችሁም:: እናንተም የምታዝኑ አይደላችሁም። info
التفاسير:

external-link copy
69 : 43

ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُواْ مُسۡلِمِينَ

69. «እነዚያ በአናቅጻችን ያመኑና ፍጹም ታዛዦች የነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
70 : 43

ٱدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ أَنتُمۡ وَأَزۡوَٰجُكُمۡ تُحۡبَرُونَ

70. (ባሮቼ ሆይ!) « እናንተም ሚስቶቻችሁም ገነትን ግቡ ትደሰታላችሁ (ትከበራላችሁ)።» ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
71 : 43

يُطَافُ عَلَيۡهِم بِصِحَافٖ مِّن ذَهَبٖ وَأَكۡوَابٖۖ وَفِيهَا مَا تَشۡتَهِيهِ ٱلۡأَنفُسُ وَتَلَذُّ ٱلۡأَعۡيُنُۖ وَأَنتُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ

71. ከወርቅ የሆኑ ሰፋፊ ዝርግ ሳህኖችና ኩባያዎች በእነርሱ ላይ እንዲዞሩ ይደረጋሉ። በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት ዓይኖችም የሚደስቱበት ሁሉ አለ:: እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
72 : 43

وَتِلۡكَ ٱلۡجَنَّةُ ٱلَّتِيٓ أُورِثۡتُمُوهَا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

72. ይህም ያ ስትሰሩት በነበራችሁት ዋጋ የተሰጣችኋት ገነት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
73 : 43

لَكُمۡ فِيهَا فَٰكِهَةٞ كَثِيرَةٞ مِّنۡهَا تَأۡكُلُونَ

73. ለእናንተ በውስጧ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁና ከእርሷም እንደልባችሁ ትበላላችሁ ይባላሉ:: info
التفاسير: