قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى

بەت نومۇرى:close

external-link copy
114 : 4

۞ لَّا خَيۡرَ فِي كَثِيرٖ مِّن نَّجۡوَىٰهُمۡ إِلَّا مَنۡ أَمَرَ بِصَدَقَةٍ أَوۡ مَعۡرُوفٍ أَوۡ إِصۡلَٰحِۭ بَيۡنَ ٱلنَّاسِۚ وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ ٱبۡتِغَآءَ مَرۡضَاتِ ٱللَّهِ فَسَوۡفَ نُؤۡتِيهِ أَجۡرًا عَظِيمٗا

114. ከውይይቶቻቸው መካከል በምጽዋት ወይም በበጎ ስራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውይይት ውስጥ ደግ ነገር የለበትም:: ይህንንም የተባለውን የአላህን ውዴታ በመፈለግ ለሚሰራ ሁሉ ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
115 : 4

وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلۡهُدَىٰ وَيَتَّبِعۡ غَيۡرَ سَبِيلِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصۡلِهِۦ جَهَنَّمَۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرًا

115. ቅኑ መንገድ ለእርሱ ከተገለጸት በኋላ መልዕክተኛውን የሚቃረንና ከምዕመናኖቹ መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሁሉ በመረጠው ጥመት ላይ እንተወዋለን። ወደ ገሀነምም እናስገባዋለን:: መመለሻይቱም ገሀነም ከፋች። info
التفاسير:

external-link copy
116 : 4

إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَغۡفِرُ أَن يُشۡرَكَ بِهِۦ وَيَغۡفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَآءُۚ وَمَن يُشۡرِكۡ بِٱللَّهِ فَقَدۡ ضَلَّ ضَلَٰلَۢا بَعِيدًا

116. አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም:: ከሽርክ በታች (ሌላ) ያለውን ጥፋት ግን ለሚሻው ይምራል:: በአላህ የሚያጋራም ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ:: info
التفاسير:

external-link copy
117 : 4

إِن يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦٓ إِلَّآ إِنَٰثٗا وَإِن يَدۡعُونَ إِلَّا شَيۡطَٰنٗا مَّرِيدٗا

117. ከእርሱ ሌላ እንስት ጣኦታትን እንጂ አይገዙም:: አመጸኞች ሰይጣንንም እንጂ ሌላን አይገዙም:: info
التفاسير:

external-link copy
118 : 4

لَّعَنَهُ ٱللَّهُۘ وَقَالَ لَأَتَّخِذَنَّ مِنۡ عِبَادِكَ نَصِيبٗا مَّفۡرُوضٗا

118. አላህም የረገመውን (እንዲህ) ያለውንም ሰይጣን እንጂ አይከተሉም: «ከባሮችህ የተወሰነን ድርሻ በእርግጥ እይዛለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
119 : 4

وَلَأُضِلَّنَّهُمۡ وَلَأُمَنِّيَنَّهُمۡ وَلَأٓمُرَنَّهُمۡ فَلَيُبَتِّكُنَّ ءَاذَانَ ٱلۡأَنۡعَٰمِ وَلَأٓمُرَنَّهُمۡ فَلَيُغَيِّرُنَّ خَلۡقَ ٱللَّهِۚ وَمَن يَتَّخِذِ ٱلشَّيۡطَٰنَ وَلِيّٗا مِّن دُونِ ٱللَّهِ فَقَدۡ خَسِرَ خُسۡرَانٗا مُّبِينٗا

119. «በእርግጥ አጠማቸዋለሁ:: ከንቱን ምኞትም አስመኛቸዋለሁ:: አዛቸዉምና የእንስሶችን ጀሮዎች ይተለትላሉ:: አዛቸዉምና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ።» (ያለውን ይከተላሉ።) ከአላህ ሌላ ሰይጣንን ረዳት አድርጎ የሚይዝ ግልጽ ኪሳራን በእርግጥ ከሰረ። info
التفاسير:

external-link copy
120 : 4

يَعِدُهُمۡ وَيُمَنِّيهِمۡۖ وَمَا يَعِدُهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ إِلَّا غُرُورًا

120. የማይፈጽመውን ከንቱ ተስፋ ይሰጣቸዋል:: ያስመኛቸዋልም:: ሰይጣን ለማታለል እንጂ ቃል አይገባላቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
121 : 4

أُوْلَٰٓئِكَ مَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُ وَلَا يَجِدُونَ عَنۡهَا مَحِيصٗا

121. እነዚያ የመጨረሻ መኖሪያቸው ገሀነም ናት:: ከእርሷም መሸሻን አያገኙም:: info
التفاسير: