قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى

بەت نومۇرى:close

external-link copy
63 : 33

يَسۡـَٔلُكَ ٱلنَّاسُ عَنِ ٱلسَّاعَةِۖ قُلۡ إِنَّمَا عِلۡمُهَا عِندَ ٱللَّهِۚ وَمَا يُدۡرِيكَ لَعَلَّ ٱلسَّاعَةَ تَكُونُ قَرِيبًا

63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎች ከሰዓቲቱ ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው።» በላቸው:: የሚያሳውቅህም ምንድን ነው! ሰዓቲቱ በቅርብ ጊዜ ልትሆን ይከጀላል:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 33

إِنَّ ٱللَّهَ لَعَنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ وَأَعَدَّ لَهُمۡ سَعِيرًا

64. አላህ ከሓዲያንን በእርግጥ ረግሟቸዋል። ለነርሱም የተጋገመችን እሳት አዘጋጅቷል:: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 33

خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۖ لَّا يَجِدُونَ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرٗا

65. በእርሷ ውስጥ ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ወዳጅም ረዳትም አያገኙም:: info
التفاسير:

external-link copy
66 : 33

يَوۡمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمۡ فِي ٱلنَّارِ يَقُولُونَ يَٰلَيۡتَنَآ أَطَعۡنَا ٱللَّهَ وَأَطَعۡنَا ٱلرَّسُولَا۠

66. ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ በሚገለባበጡ ቀን «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 33

وَقَالُواْ رَبَّنَآ إِنَّآ أَطَعۡنَا سَادَتَنَا وَكُبَرَآءَنَا فَأَضَلُّونَا ٱلسَّبِيلَا۠

67. ይላሉም «ጌታችን ሆይ! እኛ ጌቶቻችንንና ታላላቆቻችንን ታዘዝን መንገዱንም አሳሳቱን። info
التفاسير:

external-link copy
68 : 33

رَبَّنَآ ءَاتِهِمۡ ضِعۡفَيۡنِ مِنَ ٱلۡعَذَابِ وَٱلۡعَنۡهُمۡ لَعۡنٗا كَبِيرٗا

68. «ጌታችን ሆይ! ከቅጣቱ እጥፍን ስጣቸው ታላቅን እርግማንም እርገማቸው::» info
التفاسير:

external-link copy
69 : 33

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ ءَاذَوۡاْ مُوسَىٰ فَبَرَّأَهُ ٱللَّهُ مِمَّا قَالُواْۚ وَكَانَ عِندَ ٱللَّهِ وَجِيهٗا

69. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደ እነዚያ ሙሳን እንዳሰቃዩት ሰዎች አትሁኑ ካሉትም ነገር ሁሉ አላህ አጠራው:: አላህም ዘንድ ባለሞገስ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
70 : 33

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَقُولُواْ قَوۡلٗا سَدِيدٗا

70. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ትክክለኛን ንግግርም ተናገሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
71 : 33

يُصۡلِحۡ لَكُمۡ أَعۡمَٰلَكُمۡ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡ ذُنُوبَكُمۡۗ وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَقَدۡ فَازَ فَوۡزًا عَظِيمًا

71. ስራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ:: info
التفاسير:

external-link copy
72 : 33

إِنَّا عَرَضۡنَا ٱلۡأَمَانَةَ عَلَى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَٱلۡجِبَالِ فَأَبَيۡنَ أَن يَحۡمِلۡنَهَا وَأَشۡفَقۡنَ مِنۡهَا وَحَمَلَهَا ٱلۡإِنسَٰنُۖ إِنَّهُۥ كَانَ ظَلُومٗا جَهُولٗا

72. እኛ አደራን በሰማያት በምድር እና በተራራዎች ላይ አቀረብናት:: መሸከሟንም እንቢ አሉ ከእርሷም ፈሩ። ሰው ግን ተሸከማት እርሱ በጣም በደለኛና ተሳሳች ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
73 : 33

لِّيُعَذِّبَ ٱللَّهُ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلۡمُشۡرِكِينَ وَٱلۡمُشۡرِكَٰتِ وَيَتُوبَ ٱللَّهُ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمَۢا

73. ወንዶች አስመሳዮችንና ሴቶች አስመሳዮችን ወንዶች አጋሪዎችንና ሴቶች አጋሪዎችንም አላህ ሊቀጣ በምዕምናንና በምዕመናትም ላይ አላህ ንስሃን ሊቀበል (አደራዋን ሰው ተሸከማት):: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير: