قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى

بەت نومۇرى:close

external-link copy
7 : 16

وَتَحۡمِلُ أَثۡقَالَكُمۡ إِلَىٰ بَلَدٖ لَّمۡ تَكُونُواْ بَٰلِغِيهِ إِلَّا بِشِقِّ ٱلۡأَنفُسِۚ إِنَّ رَبَّكُمۡ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٞ

7. ጓዞቻችሁንም ነፍሶቻችሁን በማስቸገር እንጂ ወደ ማትደርሱበት አገር ትሸከማለች:: ጌታችሁ በእርግጥ ሩህሩህ እና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 16

وَٱلۡخَيۡلَ وَٱلۡبِغَالَ وَٱلۡحَمِيرَ لِتَرۡكَبُوهَا وَزِينَةٗۚ وَيَخۡلُقُ مَا لَا تَعۡلَمُونَ

8. ፈረሶችን፤ በቅሎዎችንና አህዮችን ልትጋልቧቸውና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ:: የማታውቁትን ድንቅ ነገርም ወደ ፊት ይፈጥራል:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 16

وَعَلَى ٱللَّهِ قَصۡدُ ٱلسَّبِيلِ وَمِنۡهَا جَآئِرٞۚ وَلَوۡ شَآءَ لَهَدَىٰكُمۡ أَجۡمَعِينَ

9. በአላህም ላይ በችሮታው ቀጥተኛውን መንገድ መግለጽ አለበት:: ከእርሷም ጠማማ አለ:: በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 16

هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗۖ لَّكُم مِّنۡهُ شَرَابٞ وَمِنۡهُ شَجَرٞ فِيهِ تُسِيمُونَ

10. እርሱ ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው:: ከእርሱም ለእናንተ መጠጥ አለላችሁ:: ከእርሱም እንስሳዎችን በእርሱ ውስጥ የምታሰማሩበት ዛፍ ይበቅልበታል:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 16

يُنۢبِتُ لَكُم بِهِ ٱلزَّرۡعَ وَٱلزَّيۡتُونَ وَٱلنَّخِيلَ وَٱلۡأَعۡنَٰبَ وَمِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ

11. በእርሱ አዝመራን፣ የዘይት ወይራን፣ ዘምባባዎችን፣ ወይኖችንና ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል:: በዚህ ክስተት ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ሁሉ በእርግጥ ትልቅ ተዓምር አለ። info
التفاسير:

external-link copy
12 : 16

وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ وَٱلنُّجُومُ مُسَخَّرَٰتُۢ بِأَمۡرِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ

12. ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን ጸሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ:: ከዋክብትም በሙሉ በፈቃዱ ብቻ የተገሩ ናቸው:: በዚህ ክስተት ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ በእርግጥ አያሌ ተዓምራት አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 16

وَمَا ذَرَأَ لَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُخۡتَلِفًا أَلۡوَٰنُهُۥٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّقَوۡمٖ يَذَّكَّرُونَ

13. በምድርም ላይ መልኮቹ የተለያዩ ሆኖ የፈጠረላችሁን ሁሉ ገራላችሁ:: በዚህ ውስጥ ለሚገሠጹ ሕዝቦች ሁሉ ግልጽ ተዐምር አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 16

وَهُوَ ٱلَّذِي سَخَّرَ ٱلۡبَحۡرَ لِتَأۡكُلُواْ مِنۡهُ لَحۡمٗا طَرِيّٗا وَتَسۡتَخۡرِجُواْ مِنۡهُ حِلۡيَةٗ تَلۡبَسُونَهَاۖ وَتَرَى ٱلۡفُلۡكَ مَوَاخِرَ فِيهِ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

14. እርሱ ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ የገራ ነው:: መርከቦችንም በውስጡ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ:: ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑም ገራላችሁ:: info
التفاسير: