قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - قۇرئان كەرىمنىڭ ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى- مۇھەممەت سادىق

አል ሐሽር

external-link copy
1 : 59

سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 59

هُوَ ٱلَّذِيٓ أَخۡرَجَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ مِن دِيَٰرِهِمۡ لِأَوَّلِ ٱلۡحَشۡرِۚ مَا ظَنَنتُمۡ أَن يَخۡرُجُواْۖ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُم مَّانِعَتُهُمۡ حُصُونُهُم مِّنَ ٱللَّهِ فَأَتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِنۡ حَيۡثُ لَمۡ يَحۡتَسِبُواْۖ وَقَذَفَ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلرُّعۡبَۚ يُخۡرِبُونَ بُيُوتَهُم بِأَيۡدِيهِمۡ وَأَيۡدِي ٱلۡمُؤۡمِنِينَ فَٱعۡتَبِرُواْ يَٰٓأُوْلِي ٱلۡأَبۡصَٰرِ

እርሱ ያ ከመጽሐፉ ሰዎች እነዚያን የካዱትን ከቤቶቻቸው ለመጀመሪያው ማውጣት ያወጣቸው ነው፡፡ መውጣታቸውን አላሰባችሁም፡፡ እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ (ኀይል) የሚከላከሉላቸው መኾናቸውን አሰቡ፡፡ አላህም ካላሰቡት ስፍራ መጣባቸው፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ መርበድበድን ጣለባቸው፡፡ ቤቶቻቸውን በእጆቻቸውና በምእምናኖቹ እጆች ያፈርሳሉ፡፡ አስተውሉም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! info
التفاسير:

external-link copy
3 : 59

وَلَوۡلَآ أَن كَتَبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمُ ٱلۡجَلَآءَ لَعَذَّبَهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ عَذَابُ ٱلنَّارِ

በእነርሱም ላይ አላህ ከአገር መውጣትን ባልጻፈ ኖሮ በቅርቢቱ ዓለም በቀጣቸው ነበር፡፡ ለእነርሱም በመጨረሻይቱ (ዓለም) የእሳት ቅጣት አልላቸው፡፡ info
التفاسير: