قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - قۇرئان كەرىمنىڭ ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى- مۇھەممەت سادىق

አን ነጅም

external-link copy
1 : 53

وَٱلنَّجۡمِ إِذَا هَوَىٰ

በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 53

مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمۡ وَمَا غَوَىٰ

ባልደረባችሁ (ነቢያችን ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 53

وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلۡهَوَىٰٓ

ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 53

إِنۡ هُوَ إِلَّا وَحۡيٞ يُوحَىٰ

እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 53

عَلَّمَهُۥ شَدِيدُ ٱلۡقُوَىٰ

ኀይሎቹ ብርቱው አስተማረው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 53

ذُو مِرَّةٖ فَٱسۡتَوَىٰ

የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 53

وَهُوَ بِٱلۡأُفُقِ ٱلۡأَعۡلَىٰ

እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 53

ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ

ከዚያም ቀረበ፤ ወረደም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 53

فَكَانَ قَابَ قَوۡسَيۡنِ أَوۡ أَدۡنَىٰ

(ከእርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ኾነም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 53

فَأَوۡحَىٰٓ إِلَىٰ عَبۡدِهِۦ مَآ أَوۡحَىٰ

ወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 53

مَا كَذَبَ ٱلۡفُؤَادُ مَا رَأَىٰٓ

(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 53

أَفَتُمَٰرُونَهُۥ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ

ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
13 : 53

وَلَقَدۡ رَءَاهُ نَزۡلَةً أُخۡرَىٰ

በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 53

عِندَ سِدۡرَةِ ٱلۡمُنتَهَىٰ

በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 53

عِندَهَا جَنَّةُ ٱلۡمَأۡوَىٰٓ

እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 53

إِذۡ يَغۡشَى ٱلسِّدۡرَةَ مَا يَغۡشَىٰ

ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 53

مَا زَاغَ ٱلۡبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ

ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 53

لَقَدۡ رَأَىٰ مِنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِ ٱلۡكُبۡرَىٰٓ

ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 53

أَفَرَءَيۡتُمُ ٱللَّٰتَ وَٱلۡعُزَّىٰ

አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
20 : 53

وَمَنَوٰةَ ٱلثَّالِثَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ

ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?) (የላቸውም)። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 53

أَلَكُمُ ٱلذَّكَرُ وَلَهُ ٱلۡأُنثَىٰ

ለእናንተ ወንድ ለእርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን? info
التفاسير:

external-link copy
22 : 53

تِلۡكَ إِذٗا قِسۡمَةٞ ضِيزَىٰٓ

ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍፍል ናት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 53

إِنۡ هِيَ إِلَّآ أَسۡمَآءٞ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَمَا تَهۡوَى ٱلۡأَنفُسُۖ وَلَقَدۡ جَآءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ ٱلۡهُدَىٰٓ

እነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲኾኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚዘነበሉበትን እንጅ ሌላ አይከተሉም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 53

أَمۡ لِلۡإِنسَٰنِ مَا تَمَنَّىٰ

ለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን? info
التفاسير:

external-link copy
25 : 53

فَلِلَّهِ ٱلۡأٓخِرَةُ وَٱلۡأُولَىٰ

መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 53

۞ وَكَم مِّن مَّلَكٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ لَا تُغۡنِي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـًٔا إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ أَن يَأۡذَنَ ٱللَّهُ لِمَن يَشَآءُ وَيَرۡضَىٰٓ

በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ info
التفاسير: