Kur'an-ı Kerim meal tercümesi - Amharca Tercüme - Afrika Akademisi

Sayfa numarası:close

external-link copy
62 : 24

إِنَّمَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَإِذَا كَانُواْ مَعَهُۥ عَلَىٰٓ أَمۡرٖ جَامِعٖ لَّمۡ يَذۡهَبُواْ حَتَّىٰ يَسۡتَـٔۡذِنُوهُۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسۡتَـٔۡذِنُونَكَ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۚ فَإِذَا ٱسۡتَـٔۡذَنُوكَ لِبَعۡضِ شَأۡنِهِمۡ فَأۡذَن لِّمَن شِئۡتَ مِنۡهُمۡ وَٱسۡتَغۡفِرۡ لَهُمُ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

62. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትክክለኛ አማኞች ማለት እነዚያ በአላህና በመልዕክተኛው ያመኑት:: ከመልዕክተኛው ጋር በሚሰበሰብ ጉዳይ ላይ በሆኑ ጊዜ እስከሚያስፈቅዱት ድረስ የማይሄዱት ብቻ ናቸው:: እነዚያ የሚያስፈቅዱህ እርሱ እነዚያ በትክክል በአላህና በመልዕክተኛው የሚያምኑት ናቸው:: ለግል ጉዳያቸዉም ፈቃድ በጠየቁህ ጊዜ ከእነርሱ ላሻኸው ሰው ፍቀድለት:: ለእነርሱም ከአላህ ምህረትን ለምንላቸው:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 24

لَّا تَجۡعَلُواْ دُعَآءَ ٱلرَّسُولِ بَيۡنَكُمۡ كَدُعَآءِ بَعۡضِكُم بَعۡضٗاۚ قَدۡ يَعۡلَمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ يَتَسَلَّلُونَ مِنكُمۡ لِوَاذٗاۚ فَلۡيَحۡذَرِ ٱلَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنۡ أَمۡرِهِۦٓ أَن تُصِيبَهُمۡ فِتۡنَةٌ أَوۡ يُصِيبَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ

63. አማኞች ሆይ በመካከላችሁ የመልዕክተኛውን ጥሪ ከፊላችሁ ከፊሉን እንደመጥራት አታድርጉት:: ከናንተ ውስጥ እነዚያን እየተከለሉ በመሽሎክሎክ የሚወጡትን አላህ በእርግጥ ያውቃቸዋል:: እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ ሁሉ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 24

أَلَآ إِنَّ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ قَدۡ يَعۡلَمُ مَآ أَنتُمۡ عَلَيۡهِ وَيَوۡمَ يُرۡجَعُونَ إِلَيۡهِ فَيُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُواْۗ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمُۢ

64. (ሙስሊሞች ሆይ! አስተዉሉ) በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: እናንተ በእርሱ ላይ ያላችሁበትን ሁኔታ በእርግጥ ያውቃል:: ወደ እርሱ የሚመለሱበትን ቀንም ያውቃል:: ከዚያ የሰሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል:: አላህም ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነውና:: info
التفاسير: