Kur'an-ı Kerim meal tercümesi - Amharca Tercüme - Afrika Akademisi

Sayfa numarası:close

external-link copy
20 : 11

أُوْلَٰٓئِكَ لَمۡ يَكُونُواْ مُعۡجِزِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا كَانَ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِنۡ أَوۡلِيَآءَۘ يُضَٰعَفُ لَهُمُ ٱلۡعَذَابُۚ مَا كَانُواْ يَسۡتَطِيعُونَ ٱلسَّمۡعَ وَمَا كَانُواْ يُبۡصِرُونَ

20. እነዚያም በምድር ውስጥ ከአላህ የሚያመልጡ አልነበሩም:: ከአላህ ሌላ ለእነርሱ ረዳቶች አልነበሯቸዉም:: ለእነርሱ ቅጣቱ ይደራረብላቸዋል:: እውነትን መስማትን የሚችሉ አልነበሩም:: የሚያዩም አልነበሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 11

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ

21. እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩና ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር የጠፋባቸው ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 11

لَا جَرَمَ أَنَّهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ هُمُ ٱلۡأَخۡسَرُونَ

22. እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም በጣም ከሳሪዎቹ ለመሆናቸው ጥርጥር የለዉም። info
التفاسير:

external-link copy
23 : 11

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَأَخۡبَتُوٓاْ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ

23. እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸዉም የተዋረዱት እነዚያ የገነት ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 11

۞ مَثَلُ ٱلۡفَرِيقَيۡنِ كَٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡأَصَمِّ وَٱلۡبَصِيرِ وَٱلسَّمِيعِۚ هَلۡ يَسۡتَوِيَانِ مَثَلًاۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

24. የሁለቱ ክፍሎች ምሳሌ አይኑ የማያይ አይነ ስውር፤ ጆሮው የማይሰማ ደንቆሮ ሰውና አይኑ የሚያይ ጆሮው የሚሰማ ሰው ብጤ ነው:: ሁለቱ በምሳሌነት ይስተካከላሉን? አትገሰጹንም? info
التفاسير:

external-link copy
25 : 11

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦٓ إِنِّي لَكُمۡ نَذِيرٞ مُّبِينٌ

25. ኑሕን ወደ ህዝቦቹ ላክንና አላቸዉም: «እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
26 : 11

أَن لَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَۖ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ أَلِيمٖ

26. «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ። እኔ ለእናንተ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።» info
التفاسير:

external-link copy
27 : 11

فَقَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ مَا نَرَىٰكَ إِلَّا بَشَرٗا مِّثۡلَنَا وَمَا نَرَىٰكَ ٱتَّبَعَكَ إِلَّا ٱلَّذِينَ هُمۡ أَرَاذِلُنَا بَادِيَ ٱلرَّأۡيِ وَمَا نَرَىٰ لَكُمۡ عَلَيۡنَا مِن فَضۡلِۭ بَلۡ نَظُنُّكُمۡ كَٰذِبِينَ

27. ከህዝቦቹም መካከል እነዚያ የካዱት መሪዎች «ብጤያችን ሰው ሆነህ እንጂ አናይህም:: እነዚያም እነርሱ ሐሳበ ጥሬዎች የሆኑት ወራዶቻችን እንጂ ሌላ ተከትሎህ አናይህም:: ለእናንተም በእኛ ላይ ምንም ብልጫን አናይም:: ከቶውንም ውሸታሞች መሆናችሁን እንጠረጥራችኋለን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 11

قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَءَاتَىٰنِي رَحۡمَةٗ مِّنۡ عِندِهِۦ فَعُمِّيَتۡ عَلَيۡكُمۡ أَنُلۡزِمُكُمُوهَا وَأَنتُمۡ لَهَا كَٰرِهُونَ

28. እርሱም አላቸው: «ህዝቦቼ ሆይ! እስቲ ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ሆኜ ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝና በእናንተ ላይ ግን ይህች እውነታ ብትደበቅባችሁ እናንተ ለእርሷ ጠይዎች ስትሆኑ እርሷን በመቀበል እናስገድዳችኋለንን? info
التفاسير: