Kur'an-ı Kerim meal tercümesi - Amharca Tercüme - Muhammet Sadık

Sayfa numarası:close

external-link copy
45 : 6

فَقُطِعَ دَابِرُ ٱلۡقَوۡمِ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْۚ وَٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

የእነዚያም የበደሉት ሕዝቦች መጨረሻ ተቆረጠ፡፡ ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይገባው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
46 : 6

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِنۡ أَخَذَ ٱللَّهُ سَمۡعَكُمۡ وَأَبۡصَٰرَكُمۡ وَخَتَمَ عَلَىٰ قُلُوبِكُم مَّنۡ إِلَٰهٌ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَأۡتِيكُم بِهِۗ ٱنظُرۡ كَيۡفَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ ثُمَّ هُمۡ يَصۡدِفُونَ

ንገሩኝ አላህ መስሚያችሁንና ማያዎቻችሁን ቢወስድ በልቦቻችሁም ላይ ቢያትም ከአላህ ሌላ እሱን የሚያመጣላችሁ አምላክ ማነው በላቸው፡፡ አንቀጾችን እንዴት እንደምናብራራ ከዚያም እነሱ እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
47 : 6

قُلۡ أَرَءَيۡتَكُمۡ إِنۡ أَتَىٰكُمۡ عَذَابُ ٱللَّهِ بَغۡتَةً أَوۡ جَهۡرَةً هَلۡ يُهۡلَكُ إِلَّا ٱلۡقَوۡمُ ٱلظَّٰلِمُونَ

«ንገሩኝ የአላህ ቅጣት በድንገት ወይም በግልጽ ቢመጣባችሁ አመጠኞች ሕዝቦች እንጅ ሌላ ይጠፋልን» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
48 : 6

وَمَا نُرۡسِلُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ إِلَّا مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَۖ فَمَنۡ ءَامَنَ وَأَصۡلَحَ فَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ

መልክተኞችንም አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን እንጅ አንልክም፡፡ ያመኑና መልካምን የሠሩ ሰዎችም በእነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
49 : 6

وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَمَسُّهُمُ ٱلۡعَذَابُ بِمَا كَانُواْ يَفۡسُقُونَ

እነዚያም ባንቀጾቻችን ያስዋሹ ያምጹ በነበሩት ምክንያት ቅጣቱ ያገኛቸዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
50 : 6

قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمۡ عِندِي خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعۡلَمُ ٱلۡغَيۡبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمۡ إِنِّي مَلَكٌۖ إِنۡ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّۚ قُلۡ هَلۡ يَسۡتَوِي ٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡبَصِيرُۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ

«ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ ወደእኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው፡፡ «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን አታስተነትኑምን» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
51 : 6

وَأَنذِرۡ بِهِ ٱلَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحۡشَرُوٓاْ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ لَيۡسَ لَهُم مِّن دُونِهِۦ وَلِيّٞ وَلَا شَفِيعٞ لَّعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ

እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳትና አማላጅ የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በርሱ (በቁርኣን) አስፈራራ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
52 : 6

وَلَا تَطۡرُدِ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ رَبَّهُم بِٱلۡغَدَوٰةِ وَٱلۡعَشِيِّ يُرِيدُونَ وَجۡهَهُۥۖ مَا عَلَيۡكَ مِنۡ حِسَابِهِم مِّن شَيۡءٖ وَمَا مِنۡ حِسَابِكَ عَلَيۡهِم مِّن شَيۡءٖ فَتَطۡرُدَهُمۡ فَتَكُونَ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

እነዚያን ጌታቸውን ፊቱን (ውዴታውን) የሚሹ ኾነው በጧትና በማታ የሚጠሩትን አታባር፡፡ እነሱን መቆጣጠር ባንተ ላይ ምንም የለብህም፡፡ አንተንም መቆጣጠር በነሱ ላይ ምንም የለባቸውም፡፡ታባርራቸውና ከበደለኞችም ትኾን ዘንድ (አታባር) info
التفاسير: