Kur'an-ı Kerim meal tercümesi - Amharca Tercüme - Muhammet Sadık

Sayfa numarası:close

external-link copy
51 : 5

۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّخِذُواْ ٱلۡيَهُودَ وَٱلنَّصَٰرَىٰٓ أَوۡلِيَآءَۘ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلِيَآءُ بَعۡضٖۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمۡ فَإِنَّهُۥ مِنۡهُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከነርሱ ነው፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
52 : 5

فَتَرَى ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ يُسَٰرِعُونَ فِيهِمۡ يَقُولُونَ نَخۡشَىٰٓ أَن تُصِيبَنَا دَآئِرَةٞۚ فَعَسَى ٱللَّهُ أَن يَأۡتِيَ بِٱلۡفَتۡحِ أَوۡ أَمۡرٖ مِّنۡ عِندِهِۦ فَيُصۡبِحُواْ عَلَىٰ مَآ أَسَرُّواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ نَٰدِمِينَ

እነዚያንም በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሽታ ያለባቸውን ሰዎች «የጊዜ መለዋወጥ እንዳያገኘን እንፈራለን የሚሉ» ሲኾኑ በእነርሱ (ለመረዳት) ሲቻኮሉ ታያቸዋለህ፡፡ አላህም ድል መንሳትን ወይም ከእርሱ ዘንድ የኾነን ነገር (ማጋለጥን) ሊያመጣ በነፍሶቻቸው ውስጥ በደበቁትም ነገር ተጸጻቾች ሲሆኑ ተረጋገጠ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
53 : 5

وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَهَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ إِنَّهُمۡ لَمَعَكُمۡۚ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ فَأَصۡبَحُواْ خَٰسِرِينَ

እነዚያም ያመኑት ሰዎች፡- «እነዚያ እነርሱ ከእናንተ ጋር ነን ብለው የጠነከረ መሐላቸውን በአላህ የማሉት እነዚህ ናቸውን» ይላሉ፡፡ ሥራዎቻቸው ተበላሹ፡፡ ከሳሪዎችም ኾኑ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
54 : 5

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَن يَرۡتَدَّ مِنكُمۡ عَن دِينِهِۦ فَسَوۡفَ يَأۡتِي ٱللَّهُ بِقَوۡمٖ يُحِبُّهُمۡ وَيُحِبُّونَهُۥٓ أَذِلَّةٍ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ أَعِزَّةٍ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ يُجَٰهِدُونَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَا يَخَافُونَ لَوۡمَةَ لَآئِمٖۚ ذَٰلِكَ فَضۡلُ ٱللَّهِ يُؤۡتِيهِ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ የሚመለስ ሰው አላህ (በእነርሱ ስፍራ) የሚወዳቸውንና የሚወዱትን፣ በምእመናን ላይ ትሑቶች፣ በከሓዲዎች ላይ ኀያላን የኾኑን በአላህ መንገድ የሚታገሉን የወቃሽን ወቀሳ የማይፈሩን ሕዝቦች በእርግጥ ያመጣል፡፡ ይኸ የአላህ ችሮታ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፤ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
55 : 5

إِنَّمَا وَلِيُّكُمُ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُمۡ رَٰكِعُونَ

ረዳታችሁ አላህና መልክተኛው እነዚያም ያመኑት ብቻ ናቸው፡፡ (እነርሱ) እነዚያ ሶላትን በደንቡ የሚሰግዱ እነርሱም ያጎነበሱ ኾነው ምጽዋትን የሚሰጡ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
56 : 5

وَمَن يَتَوَلَّ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ فَإِنَّ حِزۡبَ ٱللَّهِ هُمُ ٱلۡغَٰلِبُونَ

አላህንና መልክተኛውን እነዚያንም ያመኑትን የሚወዳጅ ሰው (ከአላህ ጭፍሮች ይኾናል)፡፡ የአላህም ጭፍሮች እነርሱ አሸናፊዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
57 : 5

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّخِذُواْ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ دِينَكُمۡ هُزُوٗا وَلَعِبٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِكُمۡ وَٱلۡكُفَّارَ أَوۡلِيَآءَۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከበፊታችሁ መጽሐፍን ከተሰጡት እነዚያን ሃይማኖታችሁን ማላገጫና መጫወቻ አድርገው የያዙትን ከሓዲዎችንም ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ምእምናንም እንደኾናችሁ አላህን ፍሩ፡፡ info
التفاسير: