ශුද්ධවූ අල් කුර්ආන් අර්ථ කථනය - අම්හාරික් පරිවර්තනය - අප්‍රිකානු අකාඩමිය

አል ቡሩጅ

external-link copy
1 : 85

وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلۡبُرُوجِ

1. የህብረ ከዋክብት ባለቤት በሆነችው ሰማይ፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 85

وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡمَوۡعُودِ

2. በተቀጠረዉም ቀን፤ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 85

وَشَاهِدٖ وَمَشۡهُودٖ

3. በመስካሪና በሚመሰከርበትም እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 85

قُتِلَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡأُخۡدُودِ

4. የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 85

ٱلنَّارِ ذَاتِ ٱلۡوَقُودِ

5. የባለማገዶዋ እሳት ባለቤቶች። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 85

إِذۡ هُمۡ عَلَيۡهَا قُعُودٞ

6. እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በሆኑ ጊዜ (ተረገሙ)። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 85

وَهُمۡ عَلَىٰ مَا يَفۡعَلُونَ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ شُهُودٞ

7. እነርሱም በምዕመኖች ላይ ለሚሰሩት (ማሰቃየት) መስካሪዎች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 85

وَمَا نَقَمُواْ مِنۡهُمۡ إِلَّآ أَن يُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَمِيدِ

8. ከእነርሱም በአሸናፊውና በምስጉኑ ጌታ ማመናቸውን እንጂ ሌላን ምንንም አልጠሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 85

ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ

9. ያ የሰማይና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነውን (ነው ያመኑበት)። አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው (አዋቂ ነው)። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 85

إِنَّ ٱلَّذِينَ فَتَنُواْ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ ثُمَّ لَمۡ يَتُوبُواْ فَلَهُمۡ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمۡ عَذَابُ ٱلۡحَرِيقِ

10. እነዚያ አማኞችና ምዕመናትን ያሰቃዩና ከዚያ ያልተጸጸቱ ሁሉ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አለላቸው:: ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 85

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ جَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡكَبِيرُ

11. እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው:: ይህ ታላቅ ስኬት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 85

إِنَّ بَطۡشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ

12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ በኃይል መያዝ ብርቱ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
13 : 85

إِنَّهُۥ هُوَ يُبۡدِئُ وَيُعِيدُ

13. እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 85

وَهُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلۡوَدُودُ

14. እርሱም ምህረቱ የበዛ ወዳድ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 85

ذُو ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡمَجِيدُ

15. የላቀው የዙፋኑ ባለቤት ነው። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 85

فَعَّالٞ لِّمَا يُرِيدُ

16. የሚሻውን ሁሉ ሰሪ (ፈፃሚ) ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 85

هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلۡجُنُودِ

17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! የእነዚያ ነብያትን ያስተባበሉ) ሰራዊቶች ወሬ መጣልህን? info
التفاسير:

external-link copy
18 : 85

فِرۡعَوۡنَ وَثَمُودَ

18. የፊርዓውንና የሰሙድ (ወሬ ደርሶሃልን)? info
التفاسير:

external-link copy
19 : 85

بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي تَكۡذِيبٖ

19. በእውነት እነዚያ (በአላህ) የካዱት (ሰዎች ሁሉ) እውነትን በማስተባበል ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 85

وَٱللَّهُ مِن وَرَآئِهِم مُّحِيطُۢ

20. አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 85

بَلۡ هُوَ قُرۡءَانٞ مَّجِيدٞ

21. ይልቁንም እርሱ የተከበረ ቁርኣን ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 85

فِي لَوۡحٖ مَّحۡفُوظِۭ

22. የተጠበቀ በሆነ ሰሌዳ (ሎህ) ውስጥ ነው:: info
التفاسير: