ශුද්ධවූ අල් කුර්ආන් අර්ථ කථනය - අම්හාරික් පරිවර්තනය - අප්‍රිකානු අකාඩමිය

පිටු අංක:close

external-link copy
45 : 27

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَآ إِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمۡ صَٰلِحًا أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ فَإِذَا هُمۡ فَرِيقَانِ يَخۡتَصِمُونَ

45. ወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊህን አላህን ተገዙ በማለት በእርግጥ ላክነው:: ወዲያዉም እነርሱ የሚነታረኩ ሁለት ቡድኖች ሆኑ:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 27

قَالَ يَٰقَوۡمِ لِمَ تَسۡتَعۡجِلُونَ بِٱلسَّيِّئَةِ قَبۡلَ ٱلۡحَسَنَةِۖ لَوۡلَا تَسۡتَغۡفِرُونَ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ

46. «ሕዝቦቼ ሆይ! ከመልካሙ በፊት በክፉው ቅጣትን አምጣብን በማለት ለምን ታስቸኩላላችሁ ይታዘንላችሁ ዘንድ አላህን ምህረትን አትለምኑምን?» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
47 : 27

قَالُواْ ٱطَّيَّرۡنَا بِكَ وَبِمَن مَّعَكَۚ قَالَ طَٰٓئِرُكُمۡ عِندَ ٱللَّهِۖ بَلۡ أَنتُمۡ قَوۡمٞ تُفۡتَنُونَ

47. «ባንተና ካንተም ጋር ባሉት ሰዎች ምክንያት ገደ ቢሶች ሆንን።» አሉት:: «ገደ ቢስነታችሁ አላህ ዘንድ ነው:: ይልቁንም እናንተ የምትፈተኑ ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
48 : 27

وَكَانَ فِي ٱلۡمَدِينَةِ تِسۡعَةُ رَهۡطٖ يُفۡسِدُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا يُصۡلِحُونَ

48. በከተማይቱም ውስጥ ምድርን የሚያበላሹና የማያሳምሩ ዘጠኝ ሰዎች ነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 27

قَالُواْ تَقَاسَمُواْ بِٱللَّهِ لَنُبَيِّتَنَّهُۥ وَأَهۡلَهُۥ ثُمَّ لَنَقُولَنَّ لِوَلِيِّهِۦ مَا شَهِدۡنَا مَهۡلِكَ أَهۡلِهِۦ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ

49. ዘጠኞቹም «እርሱንና ቤተሰቦቹን ሌሊት እንግደልና ከዚያም ለዘመዱ የቤተሰቦቹን መገደል አላየንም:: እኛም እውነተኞች ነን ልንል በአላህ እንማማል።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
50 : 27

وَمَكَرُواْ مَكۡرٗا وَمَكَرۡنَا مَكۡرٗا وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ

50. ተንኮልንም መከሩ:: እነርሱም የማያውቁ ሲሆኑ በተንኮላቸው ምክኒያት አጠፋናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 27

فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ مَكۡرِهِمۡ أَنَّا دَمَّرۡنَٰهُمۡ وَقَوۡمَهُمۡ أَجۡمَعِينَ

51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተንኮላቸዉም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ እኛ እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም በሙሉ እንዴት እንዳጠፋናቸው ተመልከት:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 27

فَتِلۡكَ بُيُوتُهُمۡ خَاوِيَةَۢ بِمَا ظَلَمُوٓاْۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ

52. እንዚህም በበደላቸው ምክንያት ባዶዎች ሲሆኑ እነዚህም ቤቶቻቸው ናቸው:: በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አስደናቂ ተዐምር አለበት:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 27

وَأَنجَيۡنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَكَانُواْ يَتَّقُونَ

53. እነዚያንም ያመኑትንና ከክህደት ይጠነቀቁ የነበሩትን አዳንን:: info
التفاسير:

external-link copy
54 : 27

وَلُوطًا إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦٓ أَتَأۡتُونَ ٱلۡفَٰحِشَةَ وَأَنتُمۡ تُبۡصِرُونَ

54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉጥንም ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ):: «እናንተ የምታዩ ስትሆኑ መጥፎን ነገር ትሠራላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
55 : 27

أَئِنَّكُمۡ لَتَأۡتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهۡوَةٗ مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِۚ بَلۡ أَنتُمۡ قَوۡمٞ تَجۡهَلُونَ

55. «እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን? በእውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ።» info
التفاسير: