ශුද්ධවූ අල් කුර්ආන් අර්ථ කථනය - අම්හාරික් පරිවර්තනය - අප්‍රිකානු අකාඩමිය

පිටු අංක:close

external-link copy
8 : 17

عَسَىٰ رَبُّكُمۡ أَن يَرۡحَمَكُمۡۚ وَإِنۡ عُدتُّمۡ عُدۡنَاۚ وَجَعَلۡنَا جَهَنَّمَ لِلۡكَٰفِرِينَ حَصِيرًا

8. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ! በመጽሐፉም አልን ብትጸጸቱ) «ጌታችሁ ሊያዝንላችሁ ይከጀላል:: ወደ ማጥፋት እንደገና ብትመለሱም እኛም ወደ ቅጣቱ እንመለሳለን:: ገሀነምንም ለከሓዲያን ሁሉ ማሰሪያ አድርገናል።» info
التفاسير:

external-link copy
9 : 17

إِنَّ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ يَهۡدِي لِلَّتِي هِيَ أَقۡوَمُ وَيُبَشِّرُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٱلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمۡ أَجۡرٗا كَبِيرٗا

9. ይህ ቁርኣን ወደዚያች በሁሉ ነገር ቀጥተኛ ወደ ሆነችው መንገድ ይመራል:: እነዚያንም በጎ የሚሠሩትንም አማኞች ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መሆኑን ያበስራል:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 17

وَأَنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ أَعۡتَدۡنَا لَهُمۡ عَذَابًا أَلِيمٗا

10. እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅተንላቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 17

وَيَدۡعُ ٱلۡإِنسَٰنُ بِٱلشَّرِّ دُعَآءَهُۥ بِٱلۡخَيۡرِۖ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ عَجُولٗا

11. ሰው መልካምን ነገር እንደሚለምን ሁሉ መጥፎንም ነገር ይለምናል:: ሰዉም ቸኳይ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 17

وَجَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ ءَايَتَيۡنِۖ فَمَحَوۡنَآ ءَايَةَ ٱلَّيۡلِ وَجَعَلۡنَآ ءَايَةَ ٱلنَّهَارِ مُبۡصِرَةٗ لِّتَبۡتَغُواْ فَضۡلٗا مِّن رَّبِّكُمۡ وَلِتَعۡلَمُواْ عَدَدَ ٱلسِّنِينَ وَٱلۡحِسَابَۚ وَكُلَّ شَيۡءٖ فَصَّلۡنَٰهُ تَفۡصِيلٗا

12. ሌሊትንና ቀንን ለችሎታችን ምልክቶች አደረግን:: የሌሊትን ምልክትም አበስን:: የቀንን ምልክትም የምታሳይ አደረግን:: ይህም የሆነበት ከአላህ ትርፍን ልትፈልጉበትና የዓመታትንም ቁጥርና ሒሳብን ታውቁበት ዘንድ ነው:: ነገሩንም ሁሉ ለያይተን ዘረዘርነው:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 17

وَكُلَّ إِنسَٰنٍ أَلۡزَمۡنَٰهُ طَٰٓئِرَهُۥ فِي عُنُقِهِۦۖ وَنُخۡرِجُ لَهُۥ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ كِتَٰبٗا يَلۡقَىٰهُ مَنشُورًا

13. ሰውን ሁሉ በራሪውን (ሥራውን) በአንገቱ ላይ አስያዝነው:: ለእርሱም በትንሣኤ ቀን የተዘረጋ ሆኖ የሚያገኘው የሆነን መጽሐፍ እናወጣለታለን:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 17

ٱقۡرَأۡ كِتَٰبَكَ كَفَىٰ بِنَفۡسِكَ ٱلۡيَوۡمَ عَلَيۡكَ حَسِيبٗا

14. (ከዚያም) «መጽሐፍህን አንብብ:: ዛሬ ባንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ ብቻ በቃ።» ይባላል። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 17

مَّنِ ٱهۡتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهۡتَدِي لِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيۡهَاۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۗ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبۡعَثَ رَسُولٗا

15. በቀናው መንገድ የተመራ ሁሉ የሚመራው ለእራሱ ብቻ ነው:: ከቀናው መንገድ የተሳሳተም የመሳሳቱ ጉዳት በእርሱ ላይ ብቻ ነው:: ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም:: መልዕክተኛንም እስከምንልክ ድረስ ማንንም የምንቀጣ አይደለንም። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 17

وَإِذَآ أَرَدۡنَآ أَن نُّهۡلِكَ قَرۡيَةً أَمَرۡنَا مُتۡرَفِيهَا فَفَسَقُواْ فِيهَا فَحَقَّ عَلَيۡهَا ٱلۡقَوۡلُ فَدَمَّرۡنَٰهَا تَدۡمِيرٗا

16. ማንኛዋንም ከተማ ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ ባለ ጸጋዎችዋን እናዛቸዋለን:: በውስጧም ያምፃሉ:: በእርሷም ላይ የቅጣት ቃሉ ይፈጸምባታል:: ከዚያም ማውደምን እናወድማታለን:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 17

وَكَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِنَ ٱلۡقُرُونِ مِنۢ بَعۡدِ نُوحٖۗ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرَۢا بَصِيرٗا

17. ከኑሕም በኋላ ከየክፍለ ዘመናት ሰዎች ያጠፋናቸው ብዙዎች ናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የባሮቹንም ኃጢአቶች ውስጠ አዋቂ ተመልካች መሆን በጌታህ ብቻ በቃ:: info
التفاسير: