ශුද්ධවූ අල් කුර්ආන් අර්ථ කථනය - අම්හාරික් පරිවර්තනය - අප්‍රිකානු අකාඩමිය

පිටු අංක:close

external-link copy
89 : 11

وَيَٰقَوۡمِ لَا يَجۡرِمَنَّكُمۡ شِقَاقِيٓ أَن يُصِيبَكُم مِّثۡلُ مَآ أَصَابَ قَوۡمَ نُوحٍ أَوۡ قَوۡمَ هُودٍ أَوۡ قَوۡمَ صَٰلِحٖۚ وَمَا قَوۡمُ لُوطٖ مِّنكُم بِبَعِيدٖ

89. «ወገኖቼ ሆይ! እኔን መከራከራችሁ የኑህን ህዝቦች ወይም የሁድን ህዝቦች ወይም የሷሊህን ህዝቦች ያገኛቸው ቅጣት ብጤ አይነት እንዲያገኛችሁ አይገፋፋችሁ:: የሉጥም ህዝቦች ከናንተ ሩቅ አይደሉም። info
التفاسير:

external-link copy
90 : 11

وَٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِۚ إِنَّ رَبِّي رَحِيمٞ وَدُودٞ

90. «ጌታችሁንም ምህረት ለምኑት ከዚያ ወደ እርሱ ተመለሱ። ጌታዬ አዛኝና ወዳድ ነውና።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
91 : 11

قَالُواْ يَٰشُعَيۡبُ مَا نَفۡقَهُ كَثِيرٗا مِّمَّا تَقُولُ وَإِنَّا لَنَرَىٰكَ فِينَا ضَعِيفٗاۖ وَلَوۡلَا رَهۡطُكَ لَرَجَمۡنَٰكَۖ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡنَا بِعَزِيزٖ

91. «ሹዐይብ ሆይ! ከምትለው ነገር ብዙውን አናውቀዉም (አይገባንም):: እኛም አንተን በኛ ውስጥ ደከማ ሆነህ እናይሃለን:: ጎሶችህም ባልኖሩ ኖሮ በወገርንህ ነበር:: አንተም በእኛ ላይ የተከበርክ አይደለህም።» አሉት:: info
التفاسير:

external-link copy
92 : 11

قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَهۡطِيٓ أَعَزُّ عَلَيۡكُم مِّنَ ٱللَّهِ وَٱتَّخَذۡتُمُوهُ وَرَآءَكُمۡ ظِهۡرِيًّاۖ إِنَّ رَبِّي بِمَا تَعۡمَلُونَ مُحِيطٞ

92. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ? ጎሳዎቼ በእናንተ ላይ ከአላህ ይልቅ የከበሩ ናቸውን? አላህን ከኋላችሁ ወደ ጀርባ አደረጋችሁት:: ጌታዬ በምትሠሩት ሁሉ ከባቢ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
93 : 11

وَيَٰقَوۡمِ ٱعۡمَلُواْ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمۡ إِنِّي عَٰمِلٞۖ سَوۡفَ تَعۡلَمُونَ مَن يَأۡتِيهِ عَذَابٞ يُخۡزِيهِ وَمَنۡ هُوَ كَٰذِبٞۖ وَٱرۡتَقِبُوٓاْ إِنِّي مَعَكُمۡ رَقِيبٞ

93. «ህዝቦቼ ሆይ! በችሎታችሁ ልክ ሥሩ እኔ ሠሪ ነኝ። የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትንና እርሱ ውሸታም የሆነው ማን እንደ ሆነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ:: ጠብቁም እኔም ከናንተ ጋር ተጠባባቂ ነኝና።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
94 : 11

وَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا نَجَّيۡنَا شُعَيۡبٗا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَأَخَذَتِ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ ٱلصَّيۡحَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دِيَٰرِهِمۡ جَٰثِمِينَ

94. ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሹዐይብንና እነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን:: እነዚያን የበደሉትንም (የጂብሪል) ጩኸት ያዘቻቸው። በየቤቶቻቸዉም ውስጥ ተንከፍርረው አደሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
95 : 11

كَأَن لَّمۡ يَغۡنَوۡاْ فِيهَآۗ أَلَا بُعۡدٗا لِّمَدۡيَنَ كَمَا بَعِدَتۡ ثَمُودُ

95. በእርሷ ውስጥ እንዳልነበሩ ሆኑ:: አስተዉሉ! ሠሙድ ከአላህ እዝነት እንደራቀች መድየንም ትራቅ:: info
التفاسير:

external-link copy
96 : 11

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٍ

96. ሙሳንም በታዐምራቶቻችንና በግልጽ ብርሃን በእርግጥ ላክነው:: info
التفاسير:

external-link copy
97 : 11

إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَٱتَّبَعُوٓاْ أَمۡرَ فِرۡعَوۡنَۖ وَمَآ أَمۡرُ فِرۡعَوۡنَ بِرَشِيدٖ

ወደ ፈርዖንና ወደስዎቹ ላክነው፡፡የፈርዖንን ነገር ህዝቦቹ ተከተሉ፡፡ የፈርዖን ነገር ቀጥተኛ አል ነበረም፡፡ info
التفاسير: