ශුද්ධවූ අල් කුර්ආන් අර්ථ කථනය - අම්හාරික් පරිවර්තනය - මුහම්මද් සාදික්

පිටු අංක:close

external-link copy
69 : 9

كَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ كَانُوٓاْ أَشَدَّ مِنكُمۡ قُوَّةٗ وَأَكۡثَرَ أَمۡوَٰلٗا وَأَوۡلَٰدٗا فَٱسۡتَمۡتَعُواْ بِخَلَٰقِهِمۡ فَٱسۡتَمۡتَعۡتُم بِخَلَٰقِكُمۡ كَمَا ٱسۡتَمۡتَعَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُم بِخَلَٰقِهِمۡ وَخُضۡتُمۡ كَٱلَّذِي خَاضُوٓاْۚ أُوْلَٰٓئِكَ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ

እንደነዚያ ከናንተ በፊት እንደ ነበሩት ናችሁ፡፡ ከእናንተ ይበልጥ በኃይል የበረቱ በገንዘቦችም በልጆችም ይበልጥ የበዙ ነበሩ፡፡ በዕድላቸውም ተጠቀሙ፡፡ እነዚያም ከእናንተ በፊት የነበሩት በዕድላቸው እንደተጠቀሙ በዕድላችሁ ተጠቀማችሁ፡፡ እንደነዚያም እንደዘባረቁት ዘባረቃችሁ፡፡ እነዚያ ሥራዎቻቸው በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም ተበላሹ፡፡ እነዚያም ከሳሪዎቹ እነሱ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
70 : 9

أَلَمۡ يَأۡتِهِمۡ نَبَأُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ قَوۡمِ نُوحٖ وَعَادٖ وَثَمُودَ وَقَوۡمِ إِبۡرَٰهِيمَ وَأَصۡحَٰبِ مَدۡيَنَ وَٱلۡمُؤۡتَفِكَٰتِۚ أَتَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِۖ فَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظۡلِمَهُمۡ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ

የእነዚያ ከእናንተ በፊት የነበሩት የኑሕ ሕዝቦች፣ የዓድና የሰሙድም፣ የኢብራሂምም ሕዝቦች የመድየን ባለቤቶችና የተገልባጮቹም ከተሞች ወሬ አልመጣላቸውምን መልክተኞቻቸው በተዓምራት መጧቸው፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
71 : 9

وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتُ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلِيَآءُ بَعۡضٖۚ يَأۡمُرُونَ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَيَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلۡمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَيُطِيعُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓۚ أُوْلَٰٓئِكَ سَيَرۡحَمُهُمُ ٱللَّهُۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ

ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፡፡ ሶላትንም ይሰግዳሉ፡፡ ዘካንም ይሰጣሉ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ይታዘዛሉ፡፡ እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
72 : 9

وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَمَسَٰكِنَ طَيِّبَةٗ فِي جَنَّٰتِ عَدۡنٖۚ وَرِضۡوَٰنٞ مِّنَ ٱللَّهِ أَكۡبَرُۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ

አላህ ምእምናንንና ምእምናትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በመኖሪያ ገነቶችም ውስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ ከአላህም የኾነው ውዴታ ከሁሉ የበለጠ ነው፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ እድል ነው፡፡ info
التفاسير: