Ibisobanuro bya qoran ntagatifu - Ibisobanuro bya Qur'an Ntagatifu mu rurimi rw'iki Amharike - Akademiya y'Afurika.

numero y'urupapuro:close

external-link copy
12 : 58

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا نَٰجَيۡتُمُ ٱلرَّسُولَ فَقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيۡ نَجۡوَىٰكُمۡ صَدَقَةٗۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٞ لَّكُمۡ وَأَطۡهَرُۚ فَإِن لَّمۡ تَجِدُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ

12. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከመልዕክተኛው ጋር በተወያያችሁ ጊዜ ከመወያየታችሁ በፊት ምጽዋትን አስቀድሙ:: (ሰደቃ ስጡ):: ይህ (ምጸዋትን አስቀድሞ መስጠት) ለእናንተ መልካምና አጥሪ ነው:: ባታገኙም ምንንም (ሳትከፈሉ) ሳትሰጡ ብትወያዩ ችግር የለባችሁም:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 58

ءَأَشۡفَقۡتُمۡ أَن تُقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيۡ نَجۡوَىٰكُمۡ صَدَقَٰتٖۚ فَإِذۡ لَمۡ تَفۡعَلُواْ وَتَابَ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمۡ فَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُواْ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥۚ وَٱللَّهُ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ

13. ከውይይታችሁ በፊት ምጽዋቶችን በማስቀደም ድህነትን ፈራችሁን? የታዘዛችሁትን ባልሰራችሁ ጊዜ አላህ ከናንተ ጸጸትን የተቀበለ ሲሆን ሶላትን ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፤ አላህንና መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ውስጠ አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 58

۞ أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ تَوَلَّوۡاْ قَوۡمًا غَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِم مَّا هُم مِّنكُمۡ وَلَا مِنۡهُمۡ وَيَحۡلِفُونَ عَلَى ٱلۡكَذِبِ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ

14. ወደ እነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ህዝቦች (አይሁዶች) ወደ ተወዳጁት አስመሳዮች አላየህምን? እነርሱ ከናንተ አይደሉም:: ከእነርሱም አይደሉም። እያወቁ በውሸት ይምላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 58

أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُمۡ عَذَابٗا شَدِيدًاۖ إِنَّهُمۡ سَآءَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

15. አላህ ለእነርሱ (በዚህ መወዳጃና የሀሰት መሀላ) ብርቱ ቅጣትን አዘጋጀ:: እነርሱ ይሰሩት የነበሩት መጥፎ ስራ ምንኛ ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
16 : 58

ٱتَّخَذُوٓاْ أَيۡمَٰنَهُمۡ جُنَّةٗ فَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ فَلَهُمۡ عَذَابٞ مُّهِينٞ

16. መሓሎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ:: ሰዎችንም ከአላህ መንገድ አገዱ:: ስለዚህ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 58

لَّن تُغۡنِيَ عَنۡهُمۡ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُهُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيۡـًٔاۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ

17. ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸውም ከአላህ (ቅጣት) ምንም አያድኗቸዉም:: እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘወታሪዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 58

يَوۡمَ يَبۡعَثُهُمُ ٱللَّهُ جَمِيعٗا فَيَحۡلِفُونَ لَهُۥ كَمَا يَحۡلِفُونَ لَكُمۡ وَيَحۡسَبُونَ أَنَّهُمۡ عَلَىٰ شَيۡءٍۚ أَلَآ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡكَٰذِبُونَ

18. አላህ የተሰበሰቡ ሆነው በሚያስነሳቸውም ቂያማ ቀን ለእናንተ እንደ ሚምሉላችሁ በሚጠቅም ነገር ላይ መሆናቸውን የሚያስቡ ሆነው ለእርሱም (ለአላህም) ይምላሉ:: ሙስሊሞች አስተዉሉ:: ውሸታሞች እነርሱ ብቻ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 58

ٱسۡتَحۡوَذَ عَلَيۡهِمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ فَأَنسَىٰهُمۡ ذِكۡرَ ٱللَّهِۚ أُوْلَٰٓئِكَ حِزۡبُ ٱلشَّيۡطَٰنِۚ أَلَآ إِنَّ حِزۡبَ ٱلشَّيۡطَٰنِ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ

19. በእነርሱም ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው (ተመቻቸባቸው) እናም አላህን ማስታወስን አስረሳቸው( ትዕዛዛቱን ተው):: እነዚያ የሰይጣን ቡድኖች ( ሰራዊቶች) ናቸው:: ሙስሊሞች አስተዉሉ:: የሰይጣን ቡድኖች ከሳሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 58

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُحَآدُّونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ أُوْلَٰٓئِكَ فِي ٱلۡأَذَلِّينَ

20. እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩ ሁሉ እነዚያ በዱንያም ሆነ በአኺራ በጣም ከተዋረዱ ወገኖች ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 58

كَتَبَ ٱللَّهُ لَأَغۡلِبَنَّ أَنَا۠ وَرُسُلِيٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ قَوِيٌّ عَزِيزٞ

21. አላህ እኔ አሸንፋለሁ መልዕክተኞቼም እንዲሁ ያሸንፋሉ ሲል ድሮውኑ ጽፏል:: አላህ ብርቱና አሸናፊ ነውና:: info
التفاسير: